የኢትዮጵያን ፓን-አፍሪካዊ የኤልጂቢቲኪው+ መጽሔትን ይደግፉ
በመላው አፍሪካ፣ በጣም ብዙ የኤልጂቢቲኪው+ ሰዎች ሕይወት ለዕይታ የሚበቃው በችግር ጊዜ ብቻ ነው፤ ወይም ፈጽሞ ለዕይታ አይበቃም። እ.ኤ.አ ከ ነሐሴ 2025 ጀምሮ፣ በራሳችን ማህበረሰቦች ውስጥ የሚነገሩ ታሪኮችን በቅንነት፣ በክብር፣ በፈጠራ ስራ እና በተስፋ የሚያቀርብ በአማርኛና በእንግሊዝኛ የሚታተም መድረክ እየገነባን ነው።
ድጋፍዎ ለምን አስፈላጊ ነው
በመላው አፍሪካ፣ የኤልጂቢቲኪው+ ሰዎች ከአህጉሪቱ በከፍተኛ ደረጃ ከተገለሉ ማህበረሰብ መካከል ናቸው። በ33 ሀገራት፣ ሕጎች በተለያየ መልኩ የኤልጂቢቲኪው+ ሰዎችን ወንጀለኛ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል። ሆኖም ማህበረሰባችን ሕያው፣ በፈጠራ የታደለ እና ትጉህ ነው፤ ሕይወታችንም በስደትና በመከራ ታሪኮች ብቻ ሊገለጽ አይገባም።
ገለልተኛ የኤልጂቢቲኪው+ ሚዲያ ከሌለ፣ ጥቃቶች ሳይጋለጡ፣ ታሪኮች ሳይመዘገቡ ሊቀሩ እና ማህበረሰቦች ታሪካቸውን በራሳቸው ቃል የመናገር እድል ሊያጡ ይችላሉ። ፋጤ ሰዎች ራሳቸውን በሙሉ የሚያዩበትና በእውነተኛ መንገድ የሚወከሉበት ቦታ ይፈጥራል።
ፋጤን ዘላቂ እንዲሆን ያግዙን
ሙሉ በሙሉ በራስ ገንዘብ ድጋፍ የተጀመረውና፤ በቁርጠኝነት፣ በልዩ ትኩረት፤ እንክብካቤና ያለ ክፍያ እዚህ ደረጃ ልንደረስ ችለናል። ልገሳዎ ለሁለተኛ ዓመታችን ዘላቂ መሠረት እንድንገነባ ይረዳናል።
ፋጤ በመስመር ላይ እንዲቆይ
ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ተደራሽ እና አስተማማኝ ድህረ ገጽ።
አበርካቾቻችንን እንዲከፈሉ
ጸሐፊዎች፣ ዓርታኢዎች፣ ፎቶግራፍ አንሺዎች እና ሌሎች ፈጠራ ባለሙያዎች።
ታሪኮቻችንን እንዲተረጎሙ
በሰው የተገመገ ዘገባ በእንግሊዝኛ እና በአማርኛ።
ልዩ ዘገባዎች እንዲዘጋጁ
ቃለ መጠይቆች፣ ጥልቅ ጽሑፎች፣ ማብራሪያዎች እና ምርመራዎች።
ለተጨማሪ አንባቢዎች እንዲዳረስ
በተለያዩ መድረኮች ላይ ህትመትና ከማህበረሰቡ ጋር ተሳትፎ።
ለሁለተኛ ዓመታችን ይቀላቀሉን
ፋጤ፤ ታሪኮቻችን በራሳችን ቋንቋዎች፣ በራሳችን መንገድ እና በራሳችን ሊነገሩ ይገባል በሚል እምነት ተጀምሯል። ድጋፍዎ ማህበረሰቦቻችንን በችግር ጊዜ ብቻ ሳይሆን፣ በፈጠራ፣ በስኬት፣ በጽናት እና በተስፋ ታሪኮች መመዝገባችንን እንድንቀጥል ያግዘናል።
ቤዛ ለዓለም
መስራች እና ዋና አርታዓ
ስለ Fatteh ድጋፍ ጥያቄ አለዎት? info@fattehmagazine.com
