የኬፕ ታውን የፕራይድ ተሳታፊዎች በደቡብ አፍሪካ ሁለተኛ ታላቅ ከተማ በመጋቢት 2026 ተሰበሰቡ። ምስል በናታሊ ጄን ፎቶግራፊ ለኬፕ ታውን ፕራይድ ከ ኢንስታግራም የተወሰደ።
የመጋቢት ወር ማጠቃለያ ላይ መነበብ የሚገባቸው ኤልጂቢቲኪው+ ዜና ቅንብሮች፣ የቦትስዋናን የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ ክርክር፣ ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ጠሎችን ከሴኔጋል፣ ሴት ገፅታ ተላባሽ የናይጄሪያ ወንዶችን ሚስጥራዊ ድግሶችን እና ከዛምቢያ፣ ከጋና እንዲሁም ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተውጣጡ ታሪኮችን ዳሷል።
በቤዛ ለዓለም
ከአፍሪካ ኤልጂቢቲው መልክዓ ምድር በአንድ ወር ውስጥ ሶስት መልካም ዜናዎች ብቅ ማለት ብርቅ ነው። መጋቢት ግን እንደዚህ ያሉ ክስተቶችን አስተናግዷል። በቦትስዋና ሁለት ሴቶች ጋብቻ የመፈፀም መብታቸውን ለማስከበር በማሰብ መንግስትን ፍርድ ቤት ያቆሙበት እና የኬንያ ፍርድ ቤት ተመሳሳይ-ፆታ ወንድ አፍቃሪ ወንዶችን በማስገደድ ገንዘብ የዘረፉ ወንጀለኞችን በመጨረሻ ተጠያቂ ተጠያቂ ያደረገበት ወር ሆኖ አልፏል። በሌላ ቦታ፣ የአህጉሪቱ አንጋፋውና ጥንታዊ የኩራት ክብረ-በዓል ከ10,000 ሰዎች በላይ በማሰባሰብ፣ በደቡብ አፍሪካ በደማቅ ትዕይንት፣ ደስታ እና ማህበረሰቡን ባሳተፈ ትርኢት ተካሂዷል።
የኬፕታውን ፕራይድ ለአንድ ወር ያህል በዘለቀው ተቃውሞ አዘል ዝግጅቶች በኋላ፣ በመጋቢት ወር ባዘጋጀው ድግስ ላይ ተጋባዦችን በደስታ ተቀብሏል። ከተማዋ በርካታ የኤልጂቢቲኪው ፈጠራ ስራ ባለሙያዎችን፣ ድራግ አርቲስቶችን እና ዲጄዎችን በሰፊው ፕሮግራም ላይ በማሳተፍ፣ "እኔ ነኝ ምክንያቱም እኛ ነን"የሚለውን የኡቡንቱን ጭብጥ በሚያንፀባርቅ መልኩም በድምቀት አክብረዋል። ጂሚ ኔቪስ እና ቤሊንዳ ዴቪድስን ጨምሮ የደቡብ አፍሪካ ሙዚቀኞች ትርኢቶች፣ ከዋናው ሰልፍ በኋላ የማርዲ ግራ መድረክ አስደምመዋል። ምንም እንኳን ዝግጅቱ አሁን ያለበትን ይዘት የያዘው እ.ኤ.አ በ2001 ቢሆንም፣ የኬፕ ታውን የመጀመሪያ ፕራይድ ጉዞ የተካሄደው እ.ኤ.አ በ1993ዓ.ም፣ የመጀመርያው ኤልጂቢቲኪው ሰልፍ በጆሃንስበርግ ከተካሄደ ከሶስት ዓመታት በኋላ ነው።
በዚህ ዓመት ደማቅ ዝግጅት ላይ፣ ንኮሲናቲ ሳንግዌኒ ዋካ ትሻሊ ለተሰብሳቢዎቹ፣ 2026 ደቡብ አፍሪካ ሁለት አስፈላጊ ክብረ በዓላት የምታከብርበት ዓመት እንደሆነ አስታውሰዋል። “በዚህ ዓመት የሕገ መንግሥታችንን 30 ዓመታት እና የ20 ዓመታት የጋብቻ እኩልነት እናከብራለን፤ ይህም በድፍረት፣ በትግል እና በድል የተቀረጸ ጉዞን ያስታውሰናል። ማህበረሰባችን እውነተኛ ፈተናዎችን መጋፈጥ ቢቀጥልም፣ ድምፃችን ይጨምራል፣ ታሪኮቻችን በይፋ መነገር ሲጀምር እና በሰዎች መካካል መገኘታችንም የማይካድ ዕውነታ ይሆናል። ፕራይድ (ኩራት) ብርሃናችንን እንደማይደበዝዝ፣ በብርቱ ለመዋደድ እንደምንቀጥል እና እያንዳንዳችን ሙሉ በሙሉ በነፃነት የምንታይበትን የወደፊት ሁኔታ እንደምንቀርጽ የምናሳውቅበት ነው” ሲሉ የኬፕታውን የኩራት አምባሳደር ተናግረዋል።
ይህ ዝግጅት ከደቡብ አፍሪካ ባሻገር ላሉ አፍሪካውያን፣ በተለይም ኤልጂቢቲኪው የሆኑ ሰዎች ጥላቻ እየጨመረባቸው ወይም የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪሪ መሆን ወንጀል በሆኑባቸው አገሮች ውስጥ የሩቅ ሊመስል ቢችልም፣ ነገር ግን አሁንም በአህጉሪቱ ውስጥ ተጨባጭ የተስፋ ምልክት የሚሰጥም ነው። የሴኔጋል ፕሬዝዳንት፣ የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ኃላፊከውሳኔው እንዲቆጠቡ ጥሪ እያቀርበም፣ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነቶች የሚያስቀጡትን ቅጣት በእጥፍ ለማሳደግ አንቲ ጌይ ቢልን (ፀረ-ተመሳሳይ ፆታ ህግን) በፊርማ ባፀደቁበት ወር፣ እንዲ አይነቱ የተስፋ ጭላንጭል አስፈላጊ ነው። በዩጋንዳ፣ ጋና እና በሌሎች አገሮችም፣ የፀረ-ኤልጂቢቲኪው ጥቃቶች የተጠናከሩበት ወርም ነበር።
የፋጤ የወሩ ተሟጋችን እናስተዋውቃችሁ
በአፍሪካ ውስጥ በአብዛኛው የኤልጂቢቲኪው ዓርዕስተ ዜናዎች በአሳዛኝ ታሪኮች ቢዋጡም፣ ከእነዚህ አሳዛኝ ታሪኮች ጎን ለጎን አዎንታዊ ገጽታዎቻችን ላይ ለማተኮር እንዲረዳን፣ አዲስ ተከታታይ ፕሮግራም ይዘንላችሁ መጥተናል። በየወሩ በአህጉሩ ውስጥ ያሉ ታታሪ አራማጆችን፣ ለሌሎች ሲሉሕይወታቸውን ከፍተኛ አደጋ ላይ ለመጣል ከባድ ውሳኔ እስከሚያደርጉ፣ ጀግና፣ ደፋር እና የሚደነቁ የኤልጂቢቲኪው መብት ተሟጋቾችን እናከብራለን። ምንም እንኳን በክልላችን የኤልጂብቲኪው መብቶችን ማራመድ የግል መስዋዕትነት የሚጠይቅ ቢሆንም፣ ጥረታቸው የሚገባውን ትኩረት አያገኝም።
በተከታታዩ 'የፋጤ የወሩ ተሟጋች የመጀመሪያው እን ግዳችን፤ የጋናዊቷ ትራንስጀንደር ሙዚቀኛ ኤንጅል ማክሲንቄስ እናት የሆኑት፣ ፎስቲና ኣራባ ፎርሰን ናቸው። ጋና፤ አስከፊውን ፀረ-ኤልጂቢቲኪው ረቂቅ ሕግን እንደገና የማነሳሳት እጣፈንታ ሲጋፈጣት፣ ፎስቲና በማህበራዊ ሚዲያ ላይ፣ ይህን አሳዛኝ የሆነውን ሕግ በይፋ በሚያስደምም መልኩ አውግዟል።
"እንደ እኔ ያሉ የኤልጂቢቲኪው ልጆች ያሏቸው እናቶች መጥተው እንዲቀላቀሉንና ከእኔ ጋር ተባብረው ለልጆቻችው እንዲታገሉ እጠይቃለሁ። ከልጆቻችሁ አትሽሹ። ህበረተሰብ እንዲገፏቸችሁ እና ልጃቹህ፣ አጋንንት አለበት እንዲሏችሁ አትፍቀዱ፤ አይደለም፤ ልጃቹህ የተፈጠረው በእግዚአብሔር ነው እናም ልጃቹህ ልዩ ነው። እንደማንኛውም ሰው፣ ሰዎች ናቸው፣ እናም እንደማንኛውም ሰው ሊኖሩ ይገባቸዋል … ኤልጂቢቲኪው ልጄን እወዳለሁ" ሲሉ በጋናው የጥብቅና ቡድን ራቲፋይ ጋና በመጋቢት ወር በቪድዮ መልዕክት አስተላልፈዋል።.
የጋና 'የሰዎች ወሲባዊ መብቶች እና የቤተሰብ እሴቶች ረቂቅ ህግ' ከፀደቀ፣ ኤልጂቢቲኪው ሰዎችን የሚያገለግል ወይም ለእነሱ የሚሟገት ማንኛውም ሰው፤ ጠበቆች፣ የጤና ባለሙያዎች ወይም የቤተሰብ አባላት ይሁኑ ለወንጀል ክስ ያጋልጣል። ሂዩማን ራይትስ ዎች እንደሚለው፣ ረቂቅ ህጉ አጋርን የሚገልፅበት መንገድ፣ "ከባህሪ ቁጥጥር በላይ ይዘልቃል፣ ማንነትን ወንጀል ያደርጋል፣ ተሟጋችነትን ያደናቅፋል፣ አስፈላጊ የሲቪል ማህበረሰብ መዋቅሮችን ያፈርሳል፣ እና ዜጎች እርስ በእርሳቸው ላይ እንዲሰልሉ እና እንዲወጋገዙ ያስገድዳል።”
“ይህ የሚመጣው ረቂቅ ሕግ በጣም ብዙ ሥቃይ አስከትሎብኛል፤ እንደ እኔ ያሉ እናቶችም በዚሁ ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ አውቃለሁ። ረቂቁ የራሴን ልጅ ሪፖርት የማድረግ ግዴታ እንዳለብኝ ይናገራል፤ እንዲሁም ባለስልጣናት ልጄን መጥተው እንዲያስሩ የመንገር ግዴታ አለብኝ! እናት የምታልፍበትን ስቃይ ተመልከቱ። ምንም አይነት ረቂቅ ሕግ መጽደቅ አያስፈልገውም። መሰረዝ አለበት።”
- ግልፅ በሆነ ጭንቀት እና ብስጭት ፎርሰን። የፎርሰን ልብ የተሞላ ዘመቻ እንደ ፐልስ ጋና ባሉ ዋና ዋና ሚዲያዎች ከመዘገቡ በፊት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ጋር ተዳርሷል።.
ሌሎች የመጋቢት ወር ዓርዕስተ ዜናዎች እነሆ።
በዩጋንዳ በመሳሳም ወንጀል ታስራው የነበሩት ሴቶች በዋስትና ከተፈቱ በኋላ በድጋሚ ታሰሩ
እስላማዊው ቡድን ጃምራ የኤልጂቢቲኪው ሰዎች ዝርዝር ለሴኔጋል መርማሪዎች አስረከበ
የአሜሪካ ወግ አጥባቂ የክርስቲያን ቡድን የሴኔጋሉን የ ፀረ-ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ አዝማቾችን ደገፈ
በዲሞክራቲክ ኮንጎ የሚገኙ አማፂያን የኤልጂቢቲኪው ተሟጋቾች ላይ ከፍተኛ ጥቃት ለመፈጸም ዒላማ ማድረጋቸውን የተባበሩት መንግስታት አስጠነቀቀ
የናይጄሪያ፣ ኒጀር እና ቻድ ሴት-ፆታ ተላባሽ ወንዶች ሚስጥራዊውን 'ያን ዳኡዱ' ድግስ ተሳተፉ
የዩጋንዳ ፍርድ ቤት የ ፀረ-የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን ህግን የሚቃወሙ ተሟጋቾችን ለመስማት ቀጠሮ ሰጠ
የአሜሪካ ኮሌጅ በፀረ-ኤልጂቢቲኪው አቋማቸው የተነሳ ለጋና ፕሬዚዳንት የሰጠውን የክብር ዲግሪ ሰረዘ
የናይጄሪያ የፀረ-ተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ህግ አመፅን እና ‘አስፈራርቶ የመቀማት ኢኮኖሚ’ እያቀጣጠለ ነው
የኬንያ ፍርድ ቤት በዘረፋ እና በአስገድዶ ቅምያ ወንጀል የተሰማሩትን ፀረ-ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ አቀጣጣዮችን አሰረ
![]()
የኤልጂቢቲኪው ተሟጋቾች አሜሪካ ላዛምቢያ የምታደርገውን ኤችአይቪን የመከላከል ጥረት የድጋፍ ዕርዳታ ማቆሟ ስጋት አሳድሮባቸዋል
ከአዲሱ ዓመት ጀምሮ በዩጋንዳ የኤልጂቢቲኪው ማህበረሰብ ላይ የሚፈጸመው ጥቃት ጨምሯል
የደቡብ አፍሪካ የሜትሮፖሊታን ማህበረሰብ አብያተ ክርስቲያናት የተመሳሳይ ፆታ ወንድ አፍቃሪ ኢማምን መግደል አወገዙ
'እስልምናን በመሳደብ' በእስር ላይ የምትገኘው ሞሮኳዊቷ ኤልጂቢቲኪው ተሟጋች እጇን የመቆረጥ አደጋ ተጋርጦባታል
የሴኔጋል ፕሬዚዳንት የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነቶችን የእሥራት ቅጣት በእጥፍ የሚያሻሽል ሕግ ፈረሙ
የቦትስዋና የተመሳሳይ ሴት ፆታ አፍቃሪያን ጥንዶች የመጋባት መብታቸውን ለማስከበር መንግሥትን ፍርድ ቤት አቆሙ

