የፋጤ፤ የሚያዝያ ወር መገባደጃ ኤልጂቢቲኪው+ ዜና ቅንብሮች፤ የወሲብ ጤና በሴኔጋል፣ ፌሚኒዝም በናይጄሪያ፣ ሲኒማን በቱኒዚያ እና ከዩጋንዳ፣ ከቦትስዋና እንዲሁም ከካሜሩን የተውጣጡ መነበብ ያለባቸው ታሪኮች ላይ ቱክረትን አድርጓል።
በቤዛ ለዓለም
የሃይማኖት መሪዎች የጋራ ጠላትን ለመቃወም ልዩነታቸውን ወደ ጎን ሲያደርጉ፣ ትልቅ የፖለቲካ ጫና ሊያሳድሩ ይችላሉ። የቤተክርስቲያን፣ መስጊዶች እና የሃይማኖት አባቶች ባለፈው ወር በጋና፤ እንደዚህ ባለ ሁኔታ በኤልጂቢቲኪው ማህበረሰብ ላይ ተቃውሞ በማሰማት፤ ፕሬዚደንት ጆን ማሃማን በኤልጂቢቲኪው ሰዎች ላይ የሚደርሰውን ስደት የሚያጠናክር እና የሚደግፏቸውንም ሁሉ ወንጀለኛ የሚያደርግ ህግ እንዲፈርሙ በመጠየቅ ነበር።
በዚህ ሃሳብ ተስማምተው በአንድ ላይ ሲያቀነቅኑ የነበሩት፤ የአላባስተር ዓለም አቀፍ ሚኒስትሪ፣ ሕያው ያህዌ 7ኛ ቀን ሰንበት ጉባኤ እና የጋና የክርስቲያን ምክር ቤት መሪዎች ነበሩ። ፕሬዝዳንቱ ሕጉን በፍጥነት ለማጽደቅ እርምጃ አልወሰዱም በማለት ከተቹት በኋላ፣ ሌሎች የእምነት መሪዎችም ወደ ዘመቻው ተቀላቀሉ፤ ከእነሱም መካከል ቀደም ሲል ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ሰዎችን “አጋንንታዊ” ብለው የጠሩት የጋና ዋና እስላማዊ መሪ እና፣የ አንባሪያ ሱኒ ሙስሊም ማህበረሰብመሪ አባላት ይገኙበታል።
በኤልጂቲኪው ሰዎች ላይ የዘነበው የሃይማኖት ተቋሞ ዘመቻ በጋና ብቻ አላበቃም። በሴኔጋል፤ ከዚህ ቀደም ኤልጂቢቲኪው ናቸው ብሎ የጠረጠራቸውን ዝርዝር ለፖሊስ ያስረከበው የጃምራ እስላማዊ ድርጅት አመራሮች፤ በሌላ ታዋቂ ዘፋኝ መድረክ አልባሳት ላይ "የኤልጂቢቲኪው ቀስተ ደመና ቀለማትን" ምልክቶችን ለመመርመር በመወሰን በሚያዝያም ወር ብቅ ብለዋል። ይህ አስገራሚ ክስተት፣ ፀረ-ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ሃይማኖታዊ ቅስቀሳ፣ አሁን ላይ ከፖለቲካ አልፎ ወደ ኪነ-ጥበብ፣ መዝናኛ እና ሰፊው ባህል ላይ እንዴት እጁን እንደዘረጋ ማሳያ ነው።
በወሩ ከተስተዋለው የጠላትነት ስሜት ባሻገር፣ የታይነትና የእድገት ምልክቶችም ነበሩ። የኢቴክዊኒ ፕራይድ (ኩራት) አዘጋጆች በደርባን ከሚደረገው ሰልፍ በፊት ጭብጣቸውን ይፋ አድርገዋል። ይህም የኩራት ክብረ በዓላት፣ በደቡብ አፍሪካ ዙሪያ ባሉ 12 ከተሞች እና ክፍለ ሃገራት መከበሩን የሚያስታውስ ዜና ምንጭ ነበር። ብዙም ሳይቆይ አንድ የሰሜን አፍሪካ ፊልም ባለሙያ፤ በቱኒዝያ የተመሳሳይ ፆታ ሴት አፍቃሪ ጭብጥ ያለው ፊልም በመልቀቅ፣ ኤልጂቢቲኪው ታሪኮችን ከመግሬብ ወደ ዓለም አቀፍ ሲኒማ ቤቶች አመጥቷል። ሌላው ብሩህ ዜና የተሰማው ደግሞ ከቦትስዋና ሲሆን፣ ይህ ህጋዊ እርምጃ ወደ አዲሱ ተከታታይ ዝግጅታችን ያሻግረናል…
የፋጤ የወሩ ተሟጋች
በአፍሪካ አህጉር የሚገኙ፤ ለኤልጂቢቲኪው ማህበረሰብ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የሚታገልሉ ጀግና፣ ደፋር እና የሚደነቁ ሰዎችን ጨምሮ፤ ለሌሎች በማሰብ ራሳቸውን ከባድ አደጋ ላይ በመጣል ያለማሰለስ የሚታገሉ ተሟጋቾችና፣ ሌሎች በዕለት ትለት ህይወታቸው ማህበረሰቡን ለመርዳት ከባድ ውሳኔ የሚያደርጉትን ፋጤ በየውሩ ያወድሳል። የዚህ ወር የክብር ተሸላሚ፣ በድፈረትና በጀግንነቱ በቦትስዋና ታሪክ የሰራ ሰው ነው።
በአፍሪካ በጣም አስፈላጊ ከሆኑ ኤልጂቢቲኪው ህግ ስኬቶች አንዱን ያሳካው የፋጤ የወሩ ተሟጋች፣ ለስዌሌትሰ ሞቺዲማንግ ነው። እንደ አንድ የቦትስዋና ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ዜጋ፣ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን ወንጀል የሚያደርጉ ድንጋጌዎችን በመቃወም እ.ኤ.አ. በ 2016 ተከራክሯል። በዚህም ጉዳይ የተነሳ፣ ከፍተኛው ፍርድ ቤት፣ እ.ኤ.አ. በ 2019 ህጉን ውድቅ ያደረገ ሲሆን፤ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትም ያንኑ ፍርድ ውሳኔ በ 2021 ደግፎ አፅድቆታል። ነገር ግን፣ ቦትስዋና በመጨረሻ እገዳውን ከህግ መጽሐፎቿ በማስወገድ የህግ ሂደቱን ያጠናቀቀችው በባለፈው ወር ነበር።

ምንም እንኳ የለስዌትሰ የህግ አማካሪ ቡድን፣ ተሟጋቾቹ እና ደጋፊዎቹ የጋራ ጥረት ቢታከልበትም፣ ለስዌሌትሰ ይህ ተራ ሰው ይህን ያልተለመደ እርምጃ ባይወስድ ኖሮ፣ ይህ ወሳኝ ስኬት ሊገኝ አይችልም ነበር። ሰብዓዊ መብት ተሟጋች የመሆን እውነተኛ ፍላጎት ያልነበረው የ21 ዓመቱ ተማሪ፤ ፖለቲከኞች አሻፈረኝ ቢሉም፣ የአፍሪካ ፍርድ ቤቶች የኤልጂቢቲኪውን ሰብዓዊ መብቶችን ማስጠበቅ እንደሚችሉ በሚያሳይ መልኩ ስሙን፣ ክብሩን እና የግል ደኅንነቱን የክርክሩ ዋና መነጋገርያ አድርጓል። ለመጀመሪያ ጊዜ ህጋዊ ድል በተጎናጸፈበት ወቅት"እኔ በማንነቱ የምኮራ ሰው ነኝ"፤ "ይህን ያደረግኩት እንደ እኔ ያሉ ሰዎች ማንነታችን ወንጀል እንደሆነ እንዳይሰማቸው ነው ብሏል።"
የሚያዝያ ወር ዓዕስተ ዜና ሙሉ ቅንብሮችን ይዳስሱ።
የሴኔጋል ፖሊስ ጠንከር ያለ ፀረ-ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ህግ ከወጣ በኋላ ከ100 በላይ ሰዎችን አስሯል
የዩጋንዳ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አንቲ ሆሞሴሽዋሊቲ አንቀፅ ህግ ላይ ይግባኝን አዘገየ
የጋና ዋና እስላማዊ ቄስ ከመሞቱ በፊት ህግ ፀረ-ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ህግ እንዲሆን ይፈልጋሉ
እስላማዊ ቡድን የሴኔጋል ዘፋኝን የኮንሰርት ልብስን 'ኤልጂቢቲኪው ቀለሞች' መረመረ’
በካሜሩን የትራንስ ታይነት ቀን ውድድር ተወዳዳሪዎች ጥቃትና ዝርፊያ ደርሶባቸዋል
በጋና የሚገኙ የአንባሪያ ሱኒ ሙስሊም መሪዎች ፕሬዝዳንቱ ፀረ-ኤልጂቢቲኪው ህግ እንዲፈርሙ አሳሰቡ
በፀረ-ኤልጂቢቲኪው እንቅስቃሴዎች የተነሳ የኤችአይቪ ታማሚዎች በሴኔጋል ውስጥ ህክምና መሻትን ፈርተዋል
የጋና ፓርላማ አባል ሬቨረንድ ንቲም ፎርጆር ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ናቸው የሚለውን ውንጀላ አስተባበሉ
የናይጄሪያ መደባኛ የሴቶች መብት እንቅስቃሴ ኤልጂቢቲኪው ሴቶችን ማግለሉን ቀጥሏል
በሙስና ወንጀል በአሜሪካ ማዕቀብ ዕገዳ ስር ያለው የዩጋንዳ ባለስልጣን በፀረ-ኤልጂቢቲኪው አቋሟን ደግፋ ተከራክራለች
ፀረ-ኤልጂቢቲኪው ጠላትነት ስጋት እየጨመረ በመጣባት ሞሮኮ ውስጥ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ አስከፊ ጥቃት ተሰነዘረበት
ካሜሩን ትራንስ ሰዎች በመታወቂያ ካርዶች ላይ ፆታን እንዲቀይሩ አልፈቀደም አለች
የጋና ፀረ-ኤልጂቢቲኪው ህግ አውጪ ሁለት ትራንስ ሴቶች እንዲታሰሩ ጠየቀ
የኢቴክዊኒ ፕራይድ (ኩራት) አዘጋጆች በደርባን ከሚደረገው ሰልፍ በፊት ጭብጣቸውን ይፋ አደረጉ
መቀመጫውን ፈረንሳይ ያደረገው ቱኒዚያዊ ፊልም ሰሪ በቱኒዝ የሌዝቢያን ፊልም ለእይታ አቅርቧል
በፍርድ ቤት ውሳኔ ከተወሰነ ከዓመታት በኋላ ቦትስዋና የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነቶችን ወንጀል የሚይደርገውን ህግን ሰረዘች

