ይህ ታሪካዊ ውሳኔ በአፍሪካ ውስጥ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ መመሪያ ነው ብሏል፣ ትራንስ ሴቷን አቤቱታ አቅራቢ በፍርድ ቤት የደገፈው የኬንያ ተሟጋች ቡድን ጂንሲያንጉ።
በቤዛ ለዓለም
አንዲት ትራንስ ሴት በኬንያ የህግ ክርክሯን በድል አጠናቃለች። ዳኛዋ እሷን በመደገፍ ፍርዱን ከሰጠች በኋላ፣ መንግስት ትራንስጀንደር ሰዎችን የሚጠብቅ ህግ እንዲያወጣ ትዕዛዝ አስተላልፋለች። አገር በቀሉ የኢንተርሴክስ፣ የትራንስጀንደር እና የጀንደር ነን-ኮንፈርሚንግ ተሟጋች ቡድን ጂንሲያንጉ፣ ፍርዱን “ፈር ቀዳጅ” ሲል ገልፆታል።
ትራንስ ወይም ትራንስጀንደር ሴት ማለት፣ በወሊድ ጊዜ የፆታ ማንነታቸው ወንድ ተብሎ ቢለይም/ቢመዘገብም፣ ነገር ግን የሚኖሩት እንደ ሴት እና የፆታ ማንነታቸውንም ሴት ብለው የሚገልጹ/የሚጠቀሙ ሰዎችን ያመለክታል። ትራንስጀንደር የሚለው መጠርያ የፆታ ማንነታቸወን የቀየሩትን/በመቀየር ላይ ያሉ ሰዎችን ያመለክታል። በፍርድ ቤት ‘ኤስሲ/SC’ በሚሉው የስሟ መነሻዎች የምትታወቀው አቤቱታ አቅራቢ፣ ከጊዜ በኋላ ጉዳዮቿን በሚደግፈው በጂንሲያንጉ ማንነቷን ታውቋል። "የኤልዶሬት ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለትራንስጀንደር አትሌቷ እና የጂንሲያንጉ አባል ሼይስ ቼፕኮስጊን በመደገፍ የፍርድ ውሳኔ ካስተላለፈ በኋላ፣ ለመብቷ ጥሰትም [1 ሚሊዮን ሺሊንግ] ካሳ እንዲከፍላት ወስኗል" ሲል ናይሮቢ መቀመጫውን ናይሮቢ ያደረገው ቡድን ነሐሴ 20 በፌስቡክ ልጥፍ ፅፏል። አንድ ሚሊዮን የኬንያ ሺሊንግ በግምት 7,600 ዶላር ነው።
የኬንያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ውሳኔውን “ታሪካዊ ድል” ብሎታል። መንግስታዊ ያልሆነው ድርጅት በዘገባው፣፣ የነሐሴ 12 ፍርድ "የወህኒ ቤቶች ለክብር እና ለግላዊነት ጥበቃ እንደማይሰጡ ከወሰነ በኋላ፣ የትራንስጀንደር መብቶችን የሚጠብቅ ህግ እንዲያወጣ" ለግዛቱ መመሪያ ሰትቷል ብሏል። በአማራጭ፣ በህጉ ላይ አስፈላጊ የሆኑትን ክፍተቶች ለመሙላት መንግስት የ 2024 ቱን የኬንያ የኢንተርሴክስ ሰዎች ህግን ማሻሻል እንደሚችል ዳኛው ተናግረዋል።
"የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በደስታ እንቀበላለን፤ ይህም መንግስት በ ‘ኤስሲ/SC’ መሰረታዊ መብቶች ላይ የጣለው ገደብ፣ ስቃይ እና ጭካኔ፣ ኢሰብዓዊ ወይም አዋራጅ አያያዝ፣ እኩልነት እና አድልዎ፣ ክብር፣ ነፃነት እና ደህንነት እንዲሁም ግላዊነት ህገ መንግስታዊ እንዳልሆኑ ያረጋገጠ ነው" ሲል ኬኤችርሲ (KHRC) ተናግሯል።
ወንድ ሆና የተወለደችው ቼፕኮስጊ ከልጅነቷ ጀምሮ ሴት ሆና የኖረች ሲሆን፣ መታወቂያ ካርድ፣ የልደት የምስክር ወረቀት እና ፓስፖርት ጨምሮ፣ ሴት የፆታ ምልክት ያላቸው ኦፊሴላዊ ሰነዶችን አግኝታለች። እ.ኤ.አ. በ 2019 ሆስፒታል ውስጥ “ሌላ ሰውን አስመስለሻል” በሚል በእስር ቤት ተይዛ፣ የራቁት ፍተሻ፣ የብልት እና የሆርሞን ምርመራ ያለፍቃዷ ተደርጓባታል፣ የደም ናሙና ቅጂም በግዳጅ ተወስዶባታል። የግል የህክምና መዛግብቶቿም ለመገናኛ ብዙሃን በድብቅ ይፋ ተደርገዋል።
በወቅቱ የኬንያ ጋዜጦች የቼፕኮስጊን ፆታ በማሳሳትና እና በድሮ ስያሜዋ በመጥራት ብዙ ዘገባዎችን አውጥተዋል።
"ፍርድ ቤቱ ‘ኤስሲ/SC’ ን እንደ ትራንስጀንደር እውቅና እንዲሰጣት የሰጠው ውሳኔ፣ ትራንስጀንደር ሰዎች የግል የፆታ ማንነታቸውን የመወሰን መብቶቻቸውን የበለጠ ያረጋግጣል። ግዛቱ ለዚያ የፆታ ማንነት፣ በኬንያ የህግ ማዕቀፍ ውስጥ ህጋዊ እውቅና እንዲሰጥ ያዛል። ይህ እውቅናን ከክርክር ወደ ተግባር የሚያንቀሳቅስ ወሳኝ እርምጃ ነው" ብሏል ኬኤችርሲ (KHRC)፣ ከተሟጋች ቡድኖቹ ጋልክ፣ ዘ አምክ አፍሪካ ኢኒሺኤቲቭ፣ ዘ ኢኒሺኤቲቭ ፎር ኢኳሊቲ እና ዲስክሪሚኔሽን፣ ናሽናል ጌይ እና ሌዝቢያን የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እንዲሁም ፔማ ኬንያ በህብረት የፈረሙትን መግለጫ ጠቅሶ ተናግሯል።
ቡድኖቹ የጠቅላይ አቃቤ ህግ ፅህፈት ቤት፣ ፍርዱን ተከትሎ አስፈላጊውን አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ እና ፓርላማም "በፍርድ ቤቱ የተገለጸውን የህግ ማርቀቅ እድሉን ተጠቅሞ እኩልነትን መሠረታዊ እሴትና የሁሉም ትራንስጀንደር ኬኒያውያን እውነታ እንዲሆን ክትትል እንዲያረግ ጥሪ አቅርበዋል።"
ፍርዱ በኬንያ ህገ-መንግስታዊ ማዕቀፍ ውስጥ ለትራንስጀንደር መብቶች በህግ ዕውቅና ማግኘት እያደገ መምጣቱን በሚያሳዩ ቀደምት ጉልህ ጉዳዮች ላይ የተመሠረተ ነው።
የ 2014 ቱን በኋላ ላይ አስታውሷል። ያስታወሱት የጂንሲያንጉ የግንኙነት መሪ ሎሊን ኦንጌሪ፣ “ፍርድ ቤቱ ትራንስጀንደር የሆነች ሴት የአካዳሚክ ሰርተፍኬቷ የፆታ ማንነቷን እንዲያንፀባርቅ መብት እንዳላት እውቅና ሰጥቷል።” ብለዋል።
የቅርብ ጊዜው የ ቼፕኮስጊ ጉዳይ ሊያስከትል የሚችለውን ተፅእኖዎች በመቀጠል ሲያብራሩ፣ "ውሳኔው ተግባራዊ ከሆነ ለአስርተ ዓመታት የዘለቀውን እና በትራንስጀንደር ሰዎች ላይ የሚደርስባቸውን በህግ መዛግብት መደበቅ እና መድልዎ፣ የፆታ ማንነትን ግልጽ የሆነ ህጋዊ እውቅና በመስጠት በስራ፣ በመኖሪያ ቤት፣ በጤና አጠባበቅ እና በትምህርት ተቋማት ላይ ከሚደርሱ መድልዎ ይጠብቃል፤ እንዲሁም የህዝብ አገልግሎቶችን ያለ አድልዎ እና ትንኮሳ ማግኘት ያስችላል።"
"ይህ ድል፣ እንደ ንቅናቄ ለጋራ ግቦቻችን በህብረት ስንተጋ፣ ግቦቻችንን ይበልጥ ማሳክት እንደምንችል የሚያሳይ ጠንካራ ማሳሰቢያ ነው" ሲል ሎሊን ተናግረዋል። የትራንስጀንደር ኤዱኬሽን ኤንድ አድቮካሲ (TEA) በጥያቄው ውስጥ ያበረከተውን ቀደምት አስተዋፅዖም ጠቅሰው "በቀጣይ፣ ጂንሲያንጉ የስቴቱን ቀጣይ እርምጃዎች በቅርበት ይከታተላል" በማለት አጠቃለዋል።
ሰፊው የኬንያ የኤልጂቢቲክው+ መብቶች ትግል በሂደት ላይ ያለ ሲሆን፣ ኤልጂቢቲክው+ ሰዎችም በየጊዜው መድልዎ፣ ስደት እና ጥቃትም ይደርስባቸዋል። መቀመጫውን በዩናይትድ ኪንግደም ያደረገው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ሂውማን ዲግኒቲ ትረስት ዘገባ፣ በተመሳሳይ ፆታ ወንዶች መካከል የሚደረግ ወሲባዊ ግንኙነቶች በሀገሪቱ ውስጥ ወንጀል ሲሆን፣ እስክ 14 ዓመት በሚደረስ እስራትም ሊያስቀጣ ይችላል።
ይህ የቅርብ ጊዜ ጉዳይ፣ በተለይም ሀገሪቱ በምስራቅ አፍሪካ ክልል ውስጥ ከሚገኙት የበለጠ ታጋሽ እና የኤልጂቢቲክው+ ተሟጋች ቡድኖች በግልፅ መስራት በሚችሉባት አገር ውስጥ፤ አወንታዊ፣ ተስፋ ሰጪ እና አንድ እርምጃ ወደፊት መሻግርን ማሳያ ምልክት ነው።

