ደፋሩ የኢትዮጵያ ተመሳሳይ ፆታ ወንድ አፍቃሪ መብት ተሟጋች እምነቱን ለመጠበቅ መረጠ

ኢትዮጵያዊዉ የኤልጂቢቲኪዉ መብት አራማጅ ሮቤል መሰረት ኃይሉ። ፎቶ፡- ከሮቤል ኃይሉ

ሮቤል መሰረት ኃይሉ ቤተ ጉራማይሌ የተሰኘውን፣ በተደጋጋሚ የጥቃት ሰለባ ለሆኑ ኤልጂቢቲኪው+ ግለሰቦች ድጋፍ የሚሰጥ ተሟጋች ቡድን በአጋርነት ከመመስረቱ በፊት፣ በሚስተር ጌይ ወርልድ ውድድር ላይ የተሳተፈ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ በመሆን ታሪክ ሰርቷል።

በቤዛ ለዓለም

ሮቤል መሰረት ኃይሉ፤ በኢትዮጵያ ባህላዊ ልብስ ተውቦ በሚስተር ጌይ ወርልድ መድረክ ላይ ሲወጣ፣ ፍርሃት ብቻ አልነበረም ተሸክሞ የወጣው። የዛሬ አስራ አራት አመት የሃያ አራት አመቱ ወጣት ሆኖ፣ የኮነነችውን ሀገር ከባድ ሸክም እና እድሜ ልኩን መደበቅን የተማረበትን እውነት ይዞ ነበር። የመድረኩ መብራት ፊቱ ላይ ከመምብራቱ ጥቂት ደቂቃዎች በፊት፣ ሮቤል አይኑን ጨፍኖ ጸሎቱን አደረገ።

“ወደ መድረኩ ስወጣ በጣም ፈርቼ ነበር” ሲል ያስታውሳል አሁን በ30ዎቹ ዕድሜ መጨረሻ ላይ የሚገኘው ሮቤል፤ ሕይወቱን ለዘላለም የለወጠውን የጆሃንስበርግን ገጠመኝ ሲያወጋኝ። ምንም እንኳን ውድድሩ በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደበት እና ኢትዮጵያ በውድድሩም ለመጀመርያ ጊዜ የተወከለችበት ቢሆንም፣ እንደሌሎች ተወዳዳሪዎች ተሞክሮውን በደስታ ማሳለፍ እንዳልቻለ ሮቤል ይናገራል። 

ከልዩ ፈገግታዎችና ለካሜራ ዝግጁ አልባሳት ጀርባ፣ የትውልድ አገራቸውን የሚያሳይ ሳሽ ያነገቡ ተወዳዳሪዎች በመድረኩ ላይ ሲዘዋወሩ ፍርሃት ነግሦ ነበር። ያንዳንዶቹ ፍርሃት በታዳሚው ጭብጨባና፣ ከዘናጩ ቲያትር ቤት ድምፅ ማጉያዎች በሚሰማው ደማቅ ሙዚቃ የታጀበውን መድረክ ፍርሃት ነበር፤ የሌሎቹ ጭንቅ ደግሞ በቅርብ ከሚያያቸው በሺህ ከሚቆጠሩ ሰዎች አልፎ፣ በየአገራቸው የሚጠብቋቸውን እንደመገለልና ሥራን እንደማጣት ያሉ ህይወትን ባንድ ጊዜ ሊለውጡ የሚችሉ ሁኔታዎችን ስጋት ላይ ነበር። ለሮቤል ግን ፍርሃቱ ከዚህም ስር የሰደደ ነበር። 

"ትኩረቴን ሕይወቴን በማዳን ላይ አድርጌ ነበር” ይላል አሁን በስደት አሜሪካ የሚኖረው ሮቤል። "በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እኔን ለመጉዳት ሲሉ ፕሮግራሙን ለማወክ እየዛቱ ነበር። ከግድያ ዛቻ የተነሳ ተጨማሪ የደኀንነት ጥበቃ ማግኘት ነበረብኝ"።

በቀጣዩ ማለዳ ህይወቱ ሙሉ ለሙሉ ተለወጠ። የሮቤል ፊት ከናሚቢያው ዌንዴሊነስ ሃሙቴኒያ ጋር፣ በውድድሩ ከተሳተፉት መካከል የመጀመሪያዎቹ ጥቁር አፍሪካውያን አንዱ በመሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ አነጋጋሪ የዜና ርዕስ ሆኖው ሰነበቱ። ናሚቢያ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪነትን ከወንጀል ነፃ ስታደርግ፣ የኢትዮጵያ ሕግ ለተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎች ረጅም የእስር ቅጣት ማስተላለፏን ቀጥላለች። ይህም ለተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎች ያላትን ጥላቻ በመቀጠል፣ እንደበፊቱ አሁንም የሰዎችን ህይወት አደጋ ላይ መጣሏንን ቀጥላለች።

"ከዚያ በኋላ ምን እንደሚሆን በማሰብ እጅግ እንደተጨነኩኝ አስታውሳለሁ። የት እሄዳለሁ? እንዴት እኖራለሁ? ከውድድሩ በኋላ ሕይወቴ ምን ይመስላል?"

በነውጡ መካከል መገኘት

ሚስተር ጌይ ኢትዮጵያ ነኝ የሚል ሰው የመኖሩ ሃሳብ በራሱ በከፍተኛ ያስቆታቸው፣ የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ጉዳዩን በፍጥነት ቀብ አደረጉት። ስልኩ ያለማቋረጥ ይጠራ ጀመር። የጥላቻ መልዕክቶች እየነጎዱ መምጣት ጀመሩ። ምንም እንኳ ቤተሰቦቹን ለማስጠንቀቅ ያቀደ ቢሆንም፣ እድሉን ለማግኘት ሳይችል ቀርቷል፤ "ሀሉም ነገር በፍጥነት ነበር የሆነው"።

ምላሹ እንደፍጥነቱም አስከፊም ነበር። ሮቤል ቤተሰቦች ከዱት፣ ጓደኞቹ አሳፈርከን በሚል ኮነኑት፣ አንድ ጊዜ ያገለገለባት ቤተክርስቲያን ያኔ በሯን ዘጋችበት፣ ጎረቤቶች ግፍ አከታተሉበት፣ አብሮ አደጎቹ በሁሉም በይነመረብ መድረክ ላይ ጥርቅም አደረጉት። ከዚህ ሁሉ በተጨማሪ አንዳንድ በኢትዮጵያ ኤልጂቢቲኪው ማህበረሰብ ዘንድም፣ በውድድሩ ላይ መሳተፉ በራሱ፣ ከፍተኛ ውጥረትና ዓመፅ በአብዛኛው ላይ ሊቀሰቅስ ይችላል በሚል ስጋት አዝነውበት ነበር።

የሚያቀው ህይወት በጥቂት ቀናት ውስጥ ሲገለባበጥ፣ በረትቶ እንዲጓዝ የረዳው እምነቱ ነበር። "መንፈሳዊነቴ በከፍተኛ መጠን ረድቶኛል። መሰረቴ ነበር" ሲል ሮቤል ያስታውሳል። 

ያኔ ነበር በመድረክ ላይ ለራሱ በሹክሹክታ ወደ ፀለያት ፀሎቱ የተመለሰው። የጸሎቱ ዋና መልዕክት "እግዚአብሔር ስህተት እንደማይሰራ አምናለው"። ለጥንካሬ የቀረበ ልመና፤ እውነተኛ ራስን ለመሆን ቃልኪዳን የገባበት እና፣ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን አፈንጋጭ እንደሆኑ ለማሳመን ሃይማኖትን ለሚጠቅሱ ደግሞ የማያሻማ ተቃውሞ ነበር።

"ለመለወጥ መለመኔን አቁሜ ጥበቃ እንዲደረግልኝ መጠየቅ ጀመርኩ። 'ነገ ሌላ ቀን ነው፣ ብቻህን አይደለህም፣ የተሻለ ቀን ይመጣል' የሚለኝ ድምፅ በውስጤ ይመላለስ ነበር"። 

ምንም እንኳን ብዙዎቹ ጨርሰው ቢከዱትም፣ ሮቤል ብቻውን አልነበረም። የቅርብ ጓደኞቹ የማያወላውል ድጋፍ፣ የአማካሪው ማበረታታዎች፣ የሥነ-ልቦና ምክር አገልግሎት ማግኘቱ፤ ክስተቱ ያስከተለውን ውጣውረድ መቋቋም እንዲችል ረድቶታል። አሁን ላይ ሆኖ ድፍረቱንና ጥንካሬውንሄን ያስከተለውን ተፅዕኖ ተመልክቷል። "ከነበረው ሚዲያ ሽፋን የተነሳ ኢትዮጵያዊያን ለስለ ህልውናችን ትኩረት መስጠት ጀምረዋል። የሉም ለማለት እንዳይችሉ አድርጓቸዋል። ይህ በራሱ ትልቅ ዕምርታ" እንደሆነ ይገልፃል።

በአስርት አመታት ልዩነት ሮቤል፣ በ2022 በሳን ፍራንሲስኮ የኩራት ቀን ላይ ተገኝቶ (ግራ) እና በጆሃንስበርግ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በሚስተር ​​ጌይ ወርልድ በ2012 መድረክ ላይ ተሳትፎ (ቀኝ)። ፎቶ፡- ከሮቤል ሀይሉ

እ.ኤ.አ የ2012ቱ ውድድር እውነታውን እንዲጋፈጡ እስኪያስገድዳቸው ድረስ ብዙዎች፣ በጭራሽ በኢትዮጵያ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎች የሉም ብለው ሲያምኑ፣ አንዳንዶች ደግሞ የሉም ብለው ያስመስሉ ነበር። ምክንቱም ማንም በድፍረት ራሱን ለዓለም ይፋ ያደረገ ስላልነበረ። በመጨረሻም ሮቤል ይሄንን ሲያደርግ፣ ሚዲያዎች ለዘመናት የቆየውንና ኤልጂቢቲኪው ሰዎችን ከማህበረሰብ መዛግብት እንዲሰወር በእጅጉ ያበረከተውን፣ ፍጹም ዝምታ እንዲሰብሩ አስገድዷቸዋል።

ሮቤል ከትግሎች ጥቅሞችን አግኝቷል። “ምንም እንኳን በሕይወቴ ላይ በነበረው አደጋ ምክንያት ከተማ መቀየር ቢኖርብኝም፣ በመጨረሻም ውድድሩ ማንነቴን ሳልደብቅ፣ እውነተኛ ራሴን ሆኜ እንድኖር አስችሎኛል” በማለት ይናገራል። 

እስከ ዛሬ ድረስ በሚስተር ​​ጌይ ወርልድ ውስጥ የተሳተፈ ብቸኛው ኢትዮጵያዊ እና የተመሳሳይ ፆታ ወንድ አፍቃሪ መሆናቸውን በአደባባይ ይፋ ካደረጉ እጅግ ጥቂት ትውልደ ኢትዮጵያውያን መካካልም የመጀመሪያው ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ የኤልጂቢቲኪው መሆናቸውን ይፋ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በጣም አነስተኛ ከመሆኑ የተነሳ፣ ሁሉም በአንድ ሰማያዊ ሚኒባስ ታክሲ ውስጥ ሊሳፈሩ ይችላሉ።

ሮቤልን በውድድሩ ላይ ማየታቸው ማንነታቸውን እንዲቀበሉ እንደረዳቸው የሚገልፁ መልዕክቶች፣ ዛሬም ድረስ ይደርሱታል። “ወሲባዊ ዝንባሌያቸውን እንዲቀበሉ ወይም ብቻቸውን አለመሆናቸውን ወይም ደግሞ ኢትዮጵያዊ ተኩኖ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ መሆን እንደሚቻል እንዲገነዘቡ እንደረዳቸው ይነግሩኛል" ይላል

ሮቤል መሰረት ኃይሉ ከፍተኛ ታይታን በመምረጥ ታሪክ ሠርቷል። ለክርክር መነሻ መሆን ብዙ መሥዋዕትነት የከፈለበት የጀግንነት ተግባር ነበር። ነገር ግን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ያደረገው ነገር ግንዛቤ ማስጨበጥ፣ ውይይትን ማነሳሳት እና ያለፍርሃት ያለማቋረጥ ለህብረተሰቡ ለመቆም ሲሆን፤ ለፋጤ የመጀመሪያ ሽፋን እና ለኤልጂቢቲው ታሪክ ወር ተስማሚ ድምፅ እንዲሆን ያደረገውም ይህ ነው።

ማየት ማመን ነው 

በአሜሪካ ጥገኝነት ከጠየቀ በኋላ ሮቤል፣ ሕይወቱን እንደገና መገንባት ቀጠለ። እንደ ሂዩማን ራይትስ ካምፔይን እና አሳይለም ወርክስ ባሉተሟጋች ድርጅቶች ውስጥ በበጎ ፈቃደኝነት ሠርቷል። የፖለቲካ አመራር ሥልጠና በመውሰድ የማደራጀትና የተሟጋችነት ሙያውን ማጠናከር ችሏል። በፌስቡክ ገፅ ላይ'የኢትዮጵያ ኤልጂቢቲኪው' የሚባል ገጽ ከፍቶ ከሌሎች ጋር ሰፋ ያለ ግንኙነት ለመፍጠር ጥረት አድርጓል! 

እ.ኤ.አ በ2018፣ እነዚህ ግንኙነቶች እየተጠናከሩ ሄደው፣ የቤተ ጉራማይሌ የተባለ የተሟጋች ቡድንን በስደት ካሉ ሌሎች የኢትዮጵያ ኤልጂቢቲኪው አክቲቪስቶች እና አጋሮች ጋር በአጋርነትእንዲጀምር መንገድ ከፍተዋል። “ዓላማችን ኤልጂቢቲኪው ኢትዮጵያውያን የሚያስፈልጓቸውን ድጋፍ እንዲያገኙ ለመሟገት፣ ታሪካዊ ዘገባዎችን እና ግንኙነቶችን እንዲገነቡና እንዲጠናከሩ የሚያግዝ ተጓዳኝ መድረክ መፍጠር ነበር” ሲል ሮቤል ያስረዳል። 

ሮቤል ከአጋር መስራቾቹ ባህሩ ሸዋዬ እና ፋሪስ ኩቺ ገዛኸኝ ጋር፣ “የኮቪድ ወረርሽኝን ጨምሮ አዘውትሮ ከሚቀያየረው የፖለቲካ እውነታ አንፃር”፣ ተጨባች እድገት አሳይተናል ይላል፣ “የኩዊር ኢትዮጵያውያንን ታሪክ ሰብስቦ የያዘውን “ጥቁር እንግዳ" የተባለውን መፅሐፍ እና በበይነመረብ ላይ የተዘጋጀውን የአፍሪካ ቀንድ ኩራት ክብረ-በዓልን እንደ ምሳሌ እያነሳ። 

"በኢትዮጵያዊያን የኤልጂብቲኪውአይኤ+ መብቶች ጉዳይ ላይ ዓለም አቀፍ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ እና የማህበረሰቡ አባላት አጣዳፊ የአደጋ ጊዜዎችን እንዲያልፉ የሚያግዙ ትብብሮችንም አቋቁመናል። ይህም ከበይነመረብ ያለፈቃድ መጋለጥንና ትንኮሳን ጨምሮ ማህበረሰቡ፣ ከፍተኛ አደጎውችን መጋፈጥ እንዲችል አስችሏል። በምላሹም፣ ከማህበረሰቡ ጋር ለመማማር የሚያስችል መሰረት እንደገነባን አምናለሁ።”

ሮቤል የግል ታሪኩ፣ አሁን ላይ ተግቶ ለሚሰራው ስራ ግብዓት ሆነውታል። መጀመሪያ በኢንስታግራም፣ በኋላም በቲክቶክ አማርኛን በመጠቀም፣ ስለ ዕለት ተዕለት ልምዶቹ ወይም የተሳሳቱ አመለካከቶችን እና ስጋቶችን እያነሳ፣ በአለን ሾውየቀጥታ ዝግጅቱ ላይ ያወያያል። "ሰዎች ታሪክን በራሳቸው ቋንቋ ሲሰሙ በተለየ መንገድ ያዳምጣሉ” ሲል ይገልፃል። 

አላማው ግልጽ ነው፤ “ሌሎች ‘ሕፃን ሮቤሎች እኔ ባለፍኩበት እንዳያልፉ መርዳትና”፣ ከፆታዊ ዝንባሌዎቻቸው ወይም ከፆታ ማንነታቸው ጋር ትግል ሲያደርጉ ሕይወት ትንሽ ከባድ ለሆነባቸው በርካታ ከዕይታ ተደብቀው የሚገኙ፣ ኤልጂቢቲኪው ኢትዮጵያውያንን፣ ኤርትራውያንና የዓለም አቀፉ የሃበሻ ዲያስፖራ አባላት ላይ ብርሃን ማብራት ነው። ሮቤል ስለ ልጅነታቸው፣ ስለቤተሰባቸው፣ ስለ ዕምነታቸው፣ ስለ ግዞታቸው፣ ስለ ፍቅራቸው፣ ስለ ፍርሃታቸው፣ ስለ ተስፋቸው እና ስለ ህልውና ትግሎቻቸው በግልጽ እንዲያጋሩ ይጋብዛቸዋል።  

"ዝምታ ከእንግዲህ በኋላ አማራጭ አይሆንም። ስለ ማኅበረሰባችን የሚነገሩት ውሸቶች በተደጋገሙ ቁጥር፣ [ስለ ራሳችን ባለን ግንዛቤ ላይ ሳይቀር ስር እየሰደዱ] እውነት እየሆኑ ይመጣሉ” ሲል ሮቤል ያስጠነቅቃል። በማህበራዊ አውታር ላይ በተደጋጋሚ መታየቱ ቢደክመውም፣ ለምን እንደሚቀጥል ሲገልፅ “ሌላ አማራጭ የለንም” ይላል። 

ሮቤል ከሚያደርጋቸው ቃለ ምልልሶች ባሻገር፣ የተሳሳተ መረጃን ይሞግታል፤ ለተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎች ጭፍን ጥላቻ ላላቸው ሰዎች በተረጋጋና በማያሻማ መንገድ ምላሽ ይሰጣል። ስለ ሥነ ምግባር፣ ጤና ወይም ሕግ አደገኛ የሆኑ አሉባልታዎች ሲቀርቡ በትዕግስት እና ድምፁን ከፍ ሳያደርግ ምላሽ ይሰጣል። አንዳንድ ጊዜ ቃላት ሊገልፁለት ሲዳግት፣ ሙዚቃ ወይም መዝሙር የልቡን እንዲናገሩለት ይጋብዛል።

ሮቤል የተሳሳተ መረጃን ይሞግታል እንዲሁም ጭፍን ጥላቻ በተረጋጋና ምላሽ በምስጠት፣ የጎመኢንት ምላሽን ኝዛቤ ማስጨበቻ ያደርጋል። ፎቶ፡- ከሮቤል ሀይሉ

“በየዕለቱ 120 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን እንደሚጠሉኝ እያወቅሁ ነው ከእንቅልፌ ምነቃው። ይህ የማልጠራጠረው እውነታዬ ነው” ይላል ሮቤል፣ በቀላል አማርኛ። "እኔ ግን አልጠላቸውም። ሰዎች የሚጠሉኝ ታሪኬን ስለማያውቁ ይመስለኛል። ለዚያም ነው በኢትዮጵያውያን ላይ ተስፋ የማልቆርጠው፤ በእርግጥ ቢያውቁኝ ኖሮ ይህን ያህል ሊጠሉኝ የሚችሉበት ምንም ምክንያት የለም"።

ሮቤል የንቅናቄውን እድገት ከማጋነን ይቆጠባል። ከእይታ ጎን ለጎን የሚመጣ ተቃውሞ፣ እንደሚያድግ ይጠብቃል። “አሁን፣ አንድ እርምጃ ወደፊት እየሄድን ግን፣ ሶስት እርምጃ ወደ ኋላ እየተጎተትን ያለን ያህል ነው የሚሰማኝ” ሲል ስጋቱን ይገልፃል። በተጨማሪም የፀረ-ኤልጂቢቲኪው ፕሮፓጋንዳ፣ የፖለቲካ እና የሃይማኖት መሪዎች የሚሰነዘሩት ሰብዓዊነትን ዝቅ የማድረግ ዘመቻዎች፤ የዓመፅ ጥቃቶች መጨመር፣ የንቅናቄዎች ሀብት መቀነስ እና፣ በኢትዮጵያ ውስጥ በቋሚነት ስጋት ውስጥ በሚኖሩ ኤልጂቢቲኪው ሰዎች ላይ ስለሚያደርሰው ጉዳት ያለውን ስጋትም ያጋራል።

"ሁላችንም የምንጋራው አንድ ነገር አለ። ሁላችንም፣ የግል ደህንነታችንን መጠበቅ ግድ ይለናል። የእኔ ደህንነት የእኔ ብቻ አይደለም፣ የማህበረሰቡም ጭምር ነው" ሲል ያሳስባል ሮቤል። ሀሉም የግልና የበይነመረብ ደህንነት መጠበቅያ ስትራቴጂ እንዲኖረው እያበረታታ። 

"ሆኖም አሁንም ቢሆን ግን፣ ሰዎች የተሳሳተ ነገር ሲጽፉ ወይም ሲያጋልጡ መገሰፅንና መቃወምን ልማዳችን ልናደርግ ይገባል" ሲልም ያሳስባል።

እምነትን መጠበቅ

ሮቤል በኢትዮጵያ ሲያድግ የተለየ እንደሆነ እየተነገረው ነበር። "የተለየው እንደነበርኩ አውቃለሁ፤ ወንድ እንደምወድም አውቃለሁ። አንድ ቀን ወንድ እንደማገባም አውቃለው። ነገር ግን እንዴት መግለፅ እንዳለብኝ አላቅም ነበር" ይላል ፈገግ እያለ። በህፃንነቱ፤ አንድ ቀን የልጅነት ፍቅሩን፣ አሜሪካዊውን ዘፋኝ እና የዘፈን ደራሲ አሸርን እንደሚያገባ እንደቀልድ ይናገር ነበር። 

ከስምንት ዓመቱ ጀምሮ ወደ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሲመላለስ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሰዶምና ገሞራ የጥፋት ታሪኮችን እና ወንድን የሚወድ ወንድ የሚደረስበትን ጥፈት ብዙ ጊዜ ይሰማ ነበር። እነዚህን ቅጣቶች፣ አስጸያፊ ኃጢዓቶችን ለፈጸሙ እንደ መለኮታዊ ቅጣት አድርገው በመቁጠር ያስፈሩት ነበር። “ስለ እኔ እያወሩ እንደሆነ ነበር ሚሰማኝ” በዚህም ምክንያት "ከእራሴ፣ ከመንፈሳዊ ህይወቴ እና ከቤተክርስቲያን ህብረቴ ጋር ከፍተኛ ትግል ውስጥ ገባው።" 

እነዚህ ተሞክሮዎች ከፈጣሪ ጋር የረጅምና የግል ውይይት መነሻ ሆኑ። "ለምን እንዲህ ፈጠርከኝ? ለምን ሌላ ወንድ መውደድ ኃጢአት ሆነ? ብዬ ብዙ ጊዜ ፈጣሪን እጠይቅ ነበር” በማለት ሮቤል ያስታውሳል። ለወላጆቹ ታዛዥና ብቁ ዜጋ ለመሆን የተቻለውን ሁሉ ጥረት የሚያደርግ ቢሆንም፣ ሊቆጣጠረው የማይችለው አንድ ነገር መኖሩን ተረዳ። 

ለረጅም ጊዜ ችግሩ መንፈሳዊ እንደሆነ ያምን ነበር። የሚሰማው ነገር ሊፀዳ የሚችል መንፈስ እንደሆነ በማመን፣ ብዙ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ የፀበል ቦታዎች ይሄድ ነበር። ከአምልኮ ሥርዓቱ ጎን ለጎን፣ ሊመጣ ስለሚችለው ለውጥ ራሱን ለማዝጋጀት፣ ይፆምና ዕለት ዕለት ጸበል ይጠጣ ነበር። ግን ምንም አልተለወጠም። “ከዛ ሁሉ በኋላ” ይላል፣ “እኔ አሁንም ያው ሮቤል ነበርኩ።”

ከዚያ በኋላ የልጅነት እdሜውንራሱን በጥልቅት በማወቅ በፀጥታ አሳለፈ። ሮቤል 17 ሲሞላው፣ በአጎቱ ዊንዶውስ 95 ኮምፒውተር በመደወያ ኢንተርኔት በመጠቀሞ ለመጀመሪያ ጊዜ 'ጌይ‘ የሚለውን ቃል በመፈለግና። ኢንሳይክሎፒዲያዎችን በማንበብ ሌሊቱን ያሳልፍ ነበር።"የነበረኝን ስሜት አጠናከሩልኝ፤ ለራሴም ስም አገኘውለት"። "ዓይኔን የከፈት ጊዜ ነበር” በማለት ያስታውሳል። 

የአራማጅነት ዘር ተዘራ 

“በኢትዮጵያ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን መብቶች ትግል እንደሚያስፈልጋቸው ሁልጊዜ አምን ነብር” ይላል ሮቤል። ሰዎች በሚወዱት ሰው ምክንያት ምን ያህል ጭካኔ እንደሚፈጸምባቸው መገንዘብናና ስለጉዳዩ በግልፅ ከመናገር ጋር ተያይዞ ስለሚመጡ አደጋዎች ካለው መረዳት የተነሳ እርምጃ ለመውሰድ ወሰነ።

ሮቤል እንቅስቃሴውን የጀመረው የቀጣናው ተሟጋች ዋና ማዕከል በሆነችው በደቡብ አፍሪካ፤ የሚገኙ ኤልጂቢቲው ድርጅቶችን በማነጋገር፣ በኢትዮጵያ ያሉ ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎች ድምፃቸው እንዴት እንደታፈነ በማስረዳት ነበር። ከዚያም ሮቤል፣ እንደ ኮንዶም ያሉ የፆታዊ ጤና መጠበቅያ ግብዓቶችን መጠየቅ ቀጠለ። እነዚህ በኢትዮጵያ ውስጥ እስከ ዛሬ ድረስ በአግባቡ ሊዳረሱ ያልቻሉ ግብዓቶችን፣ በዘዴ ለማህበረሰቡ እንዲከፋፈል አድርጓል። 

ኢትዮጵያ፤ በአብዛኛዎቹ የአፍሪካ ኤልጂቢቲኪው ተሟጋቾች ድርጅቶች እይታ ውስጥ እንኳን ባልነበረችበት ወቅት፣ የሮቤል ፅናት ጎልቶ ታይቷል። አንዳንድ ድርጅቶች ይህን የመሰለ መሠረታዊ የወሲብ ደኅንነት መጠበቂያ ቁሳቁስን መጠየቁ በራሱ አስገርሟቸው ነበር። ጥቂቶች ደግሞ፣ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ መሆኑን ማረጋገጫ እንዲያቀርብላቸው ጠይቀውታል። ይህም ሮቤልን በጣም የረበሸ ጥያቄ ቢሆንም፣ ጥቂቶች ግን ከቆይታ በኋላ አድምጠውታል።

“እነዚያ ቀደምት ተሞክሮዎች ብዙ መደረግ ያለባቸው ነገሮች እንዳሉ አስተምረውኛል” “ለሁሉም የሚስማማ አንድ ዓይነት ተሟጋችነት ወይም አራማጅነት የለም። የግል ተሞክሯችንና እይታችንን ዋና መሰረት በማድረግ አቀራረባችንን ማስተካከል አለብን” ይላል ሮቤል።

የሮቤል አካሄድ ደፋር ሆኖ መቅረብ ነበር። ሰዎች በሚስተር ​​ጌይ ወርልድ ውድድር መድረክ ላይ ከታየ በኋላ ያሳለፈውን ሲሰሙ፣ አንዳንድ ጊዜ የድፍረት እርምጃውን እንደ ግድየለሽነት አድርገው ይቆጥሩታል። ራሱን በይፋ ማጋለጡንና እንዲሳተፍ ያነሳሳውን ቁልፍ ምክንያት በትክክል ቢያውቁ፣ ተቺዎቹ እንኳን ነገሮችን በተለየ መንገድ እንዲመለከቱት ሊያደርግ ይችላል።

እ.ኤ.አ በ2011 የሚስተር ጌይ ወርልድ ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ በይነመረብ ላይ ሲተዋወቅና፣ ወድድሩ ወደ አፍሪካ ሊማጣ እንደሆነ ሲስማ ሮቤል፣ ስለ ውድድሩ የበለጠ ለማወቅ ጓጉቶ የውድድሩን ክልል ዋና ዳይሬክተር መልዕክት ይልካል። ዝግጅቱ የተመሳሳይ ፆታ ወንድ አፍቃሪውችን መብት በትምህርትና በሕዝባዊ ትዕይንት ለመሟገት ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ እንደሆነ እና ኢትዮጵያም ምንም አይነት ውክልና እንደሌላት ይነገረዋል። ዳይሬክተሩ ሁለት ጊዜ እንዲያመለክት ቢያበረታታውም፣ ነገር ግን ሮቤል ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን በማስተዋል እና ትኩረቱ ሊያስከትል የሚችለውን መዘዝ ስጋት ስለተሰማው ፈቃደኛ አልነበረም።

በመጨረሻ ሐሳቡን ያስቀየረው የጓደኛው አንድ አሳዛኝ ክስተት ነበር። ቤተሰቦቹ የተመሳሳይ ፆታ ወንድ አፍቃሪነቱን ካወቁ በኋላ እጁንና እግሩን በካቴና አስረው አጋንንት እንዲወጣለት ያስገደዱትን የቅርብ ጓደኛውን ማጣት ሃሳቡን አስቀይሮታል። "ቁስሉንና ጠባሳውን አየሁ። ያሳለፈውን አስከፊ ስቃይ አዳመጥኩ" ሲል ሮቤል ይጓደኛውን አሳዛኝ ታሪክ ያስታውሳል። ጓደኛው ከአራት ወራት በኋላ ህመሙን መቋቋም ሲያቅተው፣ "ነፃ ወጥቻለሁ፣ ለቆኛል" በማለት ለቤተሰቦቹ በመጮህ፣ ከመከራው ለማምለጥ አጋንንቱ በፀበል እንደለቀቀው በማስመሰል ራሱን ለማዳን ሞክሯል።

ብዙም ሳይቆይ ሮቤል ጓደኛው ይራሱን ህይውቱን እንዳጠፋ ይሰማል። “ሰዎች ይህን ያህል፣ በተለይም በገዛ ልጃቸው ላይ ይጭክናሉ ብዬ አልጠበኩም ነበር ላይ” ይላል ሮቤል። “የቅርብ ጓደኞቻችን በሚወዱት ሰው ምክንያት እየሞቱ እንደሆነ እና ማንም ሰው ስለነሱ እንደማያወራ እና ምንም እንደማያደርግ መገንዘቤ ልቤን ሰበረው።”

የጓደኛው የመጨረሻ መልዕክት፣ ሮቤል ሌሎች የሱን ተመሳሳይ ዕጣ ፈንታ እንዳይገጥማቸው አንድ ነገር እንዲያደርግ የሚገፋፋ ነበር። ከሁለት ሳምንታት በኋላ ሮቤል ይህንኑ ለማድረግ ወደ ሚስተር ጌይ ወርልድ ተመዘገበ። “እኔ የተመዘገብኩት፣ የተመሳሳይ ፆታ ወንድ አፍቃሪዎች በኢትዮጵያ እንዳለንና መብት ኝ እንደሌለን ለሰዎች ለማሳወቅ ነበር” ይላል። 

በተስፋ መኖር 

ሮቤል አሁንም በዚሁ እምነት በዚች ዓለም ላይ ይንቀሳቀሳል። ዛሬ ላይ በሚያከናውነው ሥራ፣ በሚያደርጋቸው ውይይቶች እና ከዚህ ሕያው ግን ተጋላጭ ማህበረሰብ ወደ እሱ ሲመጡ በሚያዳምጥበት መንገድም ጭምር ይስተውላል። 

እንደ ሮቤል ያሉ የመብት ተሟጋቾች ስራ የሚያከናውኑ ኤልጂቢቲኪው ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደረስው በደልና ጥቃት እየተበራከተ ባላበት ጊዜ፣ እና የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ሆኖ መጠራጠር ብቻ ከባድ ቅጣት በሚያስከትልበትም ወቅት ነው። ሮቤል ይህንን እውነታ እንዳለፈበትና ሕይወቱንም እነዚህ ክስተቶች በልዩ መልኩ እንደቀረፁት በሚያስመስክር መልኩ ስራውን በፅናት ያክናውናል።

የተቃውሞ እና የዕርቅ ታሪክ ተምሳሌት ከሆኑት ደቡብ አፍሪካውያን ያነሳሱታል። አገሪቷ ላይ የሚኖሩ ኤልጂቢቲኪው ሰዎች አሁን ላይ የሚያጣጥሙትን መብት እንዲጎናጸፉ ትልቅ አሻራ ያኖረውን፣ በተለይም የኔልሰን ማንዴላን የአፓርታይድ ትግል እና በተገለሉ ማህበረሰቦች ላይ የሚደርሰውን ጭቆና ለማሸናፍ ያደረጉትን የተቃውም ትግል።

በተመሳሳይ ሮቤል፤ ሰዎች የትኛውም ዘር ይሁኑ በሰብዓዊነታቸው ብቻ የሚከበሩበት፣ በፆታ ተሟርኳቸውና በፆታ ማንነታቸው አናሳ የማህበረሰቡ ክፍሎች የሚጠበቁበት፤ እንዲሁም በዘር እና በሃይማኖት መከፋፈል የሌለባት የወደፊት ኢትዮጵያን ያልማል።

“ጥያቄያችን መሰረታዊ የሰብዐዊ መብቶት ጥያቄ ነው። ልንደራደርበት የሚገባ የፖለቲካ አጀንዳ አይደለም። በሕይወቴ ልንደራደር አንችልም”። “ስበዕናዬ ለጥያቄ ወይም ለክርክር መቅረብ አይገባውም”፣ ሲል ሮቤል አጥብቆ ይናገራል። 

በኤልጂቢቲኪው የታሪክ ወር ዓለም ያለፈውን፣ የአሁኑንና የወደፊቱን ግንኙነት ላይ ሲያንፀባርቅ፣ ሮቤል ሰዎች ያላቸውን የአጋርነት መንፈስ ወደ ተግባር እንዲቀይሩ ይጋብዛል። ራሳቸውን በመግለጥ በኩራት የሚኖሩ በጣም ጥቂት እድለኞች፣ ይህ እድል ለሌላቸው ሰዎች ጥብቅ ለመቆም ሊነሳሱ የሚገባበት ጊዜ ነው" በማለት ያሳስባልሮቤል፣ በዓለም ዙሪያ የኤልጂቢቲኪው ሰዎችን ማንነት ወንጀል ከሆነባችው 64 አገራትን፣ ከነዚህም መካከል 32 ቱ አፍሪካ ውስጥ መሆናቸውንና የተቀሩት አብዛኛውን ደሞ ከባድ ጥላቻ የሚደርስበቸውን አገራት በመጥቀስ። 

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ፣ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪነት ሕይወት ድብቅ ባህሪ እና ይፋ መውጣት በራሱ አስከፊ መዘዝ ሊያስከትል በሚችልባቸው አገሮች “ከእኛ በፊት የመጡትን እና መንገድ የጠረጉልንን አሁንም ይህን የሚያደርጉትን መካድ የለብንም” በማለት ሮቤል ያሳስባል። 

“እነዚህ ሸምጋዮች፣ ተንከባካቢዎች፣ የማህበረሰቡ አደራጆች እና የዕለት ተዕለት ድካማቸው ሰዎችን በጭንቀት እና በፍርሃት በሚገለሉበትና በችግራቸው ጊዜ ጸንተው እንዲያልፉ መሰረት ሆነዋል። አብዛኞቹ ስራቸወን በዘዴ የሚሰሩ፣ እውቅና እንኳ ያልተሰጣቸው አልፎም የራሳቸውን ደህንነት አደጋ ውስጥ ከተው የሚሰሩ ሲሆን፤ ሌሎች ደግሞ የስራቸውን ፍሬ ሳያዩ እና እውቅና ሳይሰጣቸው አልፈዋል። ታሪኮቻቸው በራሳችን ቃል ሊነገሩ ይገባል" ይላል ሮቤል በቆራጥነትና ተነሳሽነት ባለው መንፈስ። አክሎም እንዲህ ዓይነት ታሪኮች ስለተከለከሉ፣ የጠፉ ወይም የሌሉ ግን ማለት እንዳልሆኑ በማከል።

ኤልጂቢቲኪው ኢትዮጵያ ሕይወት የጀመረው፣ ሮቤል በ2012 መድረክ ላይ ባሳየው እምቢተኝነት እንቅስቃሴዎች ነው የሚሉ የተሳሳቱ የታሪክ ንግርት መቀበል አያስፈልግም። ይህ ወቅጥ ታላቅ መሰረት የጣለ ክስተት እንደሆነ ለመገንዘብ ግን አያዳግትም። መዛግበትን አገላብጦ ላዬ፣ ሮቤል እንደ አንድ ወሳኝ ተምሳሌት እና በታሪክ መዛግበት ላይ፣ ፈር ቀዳጅ እንዲባል ያደርገዋል።

ሮቤል በኢትዮጵያ የኤልጂቢቲኪው ታሪክ ውስጥ የራሱን ቦታ ምን ብሎ እንድሚሰይመው ሲጠየቅ፣ ለአፍታ ዝም ካለ በኋላ። “ተስፋ። ተስፋኛ” አለ።

ለምን መሰለህ? “ምክንያቱም ዕድገቱ በቋፍ ላይ ያለ ቢመስልም እንኳ፣ ለውጥ እንደሚያመጣ ተስፋ አደርጋለሁ።”

Scroll to Top