የአፍሪካ ቅንብር | ሊታወቁ የሚገባቸው ኤልጂቢቲኪው+ ዜናዎች ከያውንዴ፣ ካኖ፣ ጆሃንስበርግ እና ባሻገር

Reunification Monument in Yaoundé, Cameroon, overlaid with Fatteh’s map of the African continent.

የፋጤ ወርሃዊ የኤልጂቢቲኪው+ ዜና ቅንብር፣ ጋናዊቷን ትራንስ ሙዚቀኛ፣ ዩጋንዳዊዎቹን ካቢኔ ሚኒስትሮች፣ የደቡብ አፍሪካን የኩራት ሰልፍ መሪ እንዲሁም ከናይጄሪያ፣ ከኢትዮጵያ እና ከታንዛኒያ የተገኙ ማኛ ታሪኮችን ይዟል።

በቤዛ ለዓለም 

የአፍሪካ ኤልጂቢቲኪው+ ጉዳዮች በአሜሪካ የባህል እሰጣ ገባዎች እና በአውሮፓ የስደት ክርክሮች ጋር በተቆራኙበት በዚህ ወር፣ ዓለም አቀፋዊ የፖለቲካ ክስተቶች የዚህ ወር የዜና ዘገባዎች ላይ ትልቅ ተፅዕኖ አሳድረዋል። ይሁንና የአፍሪካ ፖለቲከኞች በአገር በቀል ብሎም በአካባቢያቸው ባሉ አክቲቪስቶች እና ስነ-ጥበብ ባለሙያዎች ጫና እና ግፊት ቢደረግባቸውም፣ በማህበረሰቡ ላይ የራሳቸውን ጦርነት ከማዋጅ አላገዳቸውም።

ይሄኔ ነው ታድያ ከደፋር እና የፈጠራ ችሎታ ከተካናቸው ሰዎች የምንበረታታው። የኬንያውን ፖፕ ሙዚቃ ኮከብ ዊሊስ ቺማኖ, ፣ ከፋጤ ጋር በነበረው ግለፅና፣ ቀናና አዝናኝ ቃለ ምልልስ፤ ከሚስጥር ማንነቱ ወደ ነፃነት ያደረገውን ጉዞ እና ለምን የኤልጂቢቲኪው ዓርዓያ ሆኖ በመታየቱ ቢደሰትም ግን አንዳንዴ አስመሳይ እንደሆነ እንደሚሰማው በቅደም ተከተል ዘግቧል። በናይሮቢ ውስጥም ሆነ ባሻገር፣ በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ የህይወት ተሞክሮዎች ንፅፅር ግን በጣም የተለያየ ሊሆን ይችላል። 

በጆሃንስበርግ፣ ከኤልጂቢቲኪው ማህበረሰብ ውስጥ የተቃውሞ ዛቻ ቢሰነዘርም፣ አውራ ጎዳናዎቿ በአፍሪካ ውስጥ ቀደምት የሆነውን የኩራት ሰልፍን ለማክበር በተሰበሰቡ በደስታ ተሞልተው ነበር። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ እንደ ያውንዴ እና ካኖ ባሉ ከተሞች ትራንስ ሴቶች እና ተመሳሳይ ፆታ ወንድ አፍቃሪዎች ከተዋረዱ እና ጥቃት ከደረሰባቸው በኋላ፣ በሀሰት ክስ በፖሊስ እየታሰሩ ነበር። በኒውዮርክ ታይምስ ላይ (የእኛ አይነት ፍቅር አይነገርም)' Our Kind of Love Is Unspeakable’, በሚል ርዕስ የታተመው እና በኢትዮጵያ ውስጥ ስለተመሳሳይ ፆታ የፍቅር ግንኙነት የሚዳስስ የግል ተሞክሮን ጨምሮ በዚህ ወር ጥቂት አስገራሚ ክስተቶችም ነበሩ።

በጥቅምት ወር፣ በአህጉሪቱ ባሉ የኤልጂቢቲኪው+ ሰዎች ላይ ተፅዕኖ ያሳድሩ ሌሎች ጠቃሚ ታሪኮችም አሉ። የፋጤ የአርዕስተ ዜናዎች ቅንብር የሚከተለውን ይመስላል።

የጆሃንስበርግ ኩራት (ፕራይድ) ዳይሬክተር የተቃውሞ ዛቻ ጥያቄዎችን ‘የተሳሳተ መረጃ’ በማልት ውድቅ አድርገውታል

ፖሊስ በካሜሩን አምስት ሰዎችን ‘ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ብሎ በመጠርጠር’ አስሯል

የእስልምና ሐይማኖት ፖሊስ በናይጄሪያ ውስጥ 'ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ሠርግ' ታዳሚዎችን በቁጥጥር ስር አዋለ

ጋናዊቷ የትራንስ ሙዚቀኛ ኤንጅል ማክሲን ‘ካወርድ’ የተሰኘውን የተቃውሞ ዜማዋን ለቃለች

ኔዘርላንድስ የጥገኝነት ጥያቄያቸው ውድቅ የተደረጉ ኤልጂቢቲኪው ሰዋችን ወደ ዩጋንዳ አትልክም

ካሜሩናዊቷ ትራንስ ሴት ከምርጫ በኋላ 'ህዝብን በመረበሽ' ቁጥጥር ስር ውለዋል

የደቡብ አፍሪካ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የፀረ-ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ጠል (ሆሞፎቢክ) ሬዲዮ አስተናጋጅን ሊመረምር ነው

የዩጋንዳ ፀረ-ኤልጂቢቲኪው ቄስ የቻርሊ ከርክ ግድያን ምክንያት አድርገው የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ጠል (ሆሞፎቢክ) መጽሐፍን እየሸጡ ነው

የጋና ፖለቲከኞች ስለ ፀረ-ኤልጂቢቲኪው ቢል ያለበት ሁኔታ ግራ እንዳጋባቸው አምነዋል

ከፀረ-ኤልጂቢቲኪው የዩጋንዳ መሪ ጋር የታየው የዩኤስ ፖለቲከኛ አመለካከቷን እንደማያውቅ ተናገረ

የማምባኦንላይን መስራች በደቡብ አፍሪካ የሲሞን ንኮሊ ሽልማትን ሊቀበል ነው

በዩጋንዳ ያለው ፀረ-ኤልጂቢቲኪው ጥቃት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን ተዘገበ

በኤልጂቢቲኪው+ ታንዛኒያውያን ምን ያህል እንደተገለሉ የሚዘግብ አዲስ ሪፖርት ወጣ

'አላህ ሌዝቢያን ነው' በሚል የስድብ ወንጀል የተከሰሰችው የሞሮኮ አክቲቪስት የእስር ቅጣት ውሳኔ ፀደቀ

ደቡብ አፍሪካ በኤልጂቢቲኪው 'የለውጥ ሕክምናዎች/ልምምዶች' ላይ ያላትን መታገስ ሪፖርቱ ተቸ

ኤጲስ ቆጶሱ ከናይጄሪያ የሜቶዲስት ቤተክርስትያን ምዕመናን 'በጅምላ መውጣትን' በኤልጂቢቲኪው ሰዋች መካተት ላይ አላከዋል

Scroll to Top