እንኳን ወደ ፋጤ በደህና መጡ!

የፋጤ መስራች እና ዋና አርታኢ ቤዛ ለዓለም ምስል። ምስሉ ሙሉ ለሙሉ እሳቸውን ስለመምሰሉ ዋስትና አንሰጥም።

በመጀመሪያው የዓርታዒ ደብዳቤያቸው ለኢትዮጵያ እና ለዓለም አቀፍ ሀበሻ ዲያስፓራ በአማርኛ እና በኢንግሊዘኛ የሚቀርበው በዓይነቱ ልዩ ስለሆነው ፋጤ መፅሔት ምስረታ ዋና አዘጋጅ ቤዛ ለዓለም አብራርተዋል።

የአርታዒ ደብዳቤ

ውድ አንባቢያን

ይህ መፅሔት፣ ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረ ነው ማለት ማጋነን አይሆንም። በተደራጀና በሚያምር መልኩ እንዲወጣ፣ ይዘቱ ከፍተኛ ጥራት ያለው እንዲሆን በመፈለግ እና እውነቱን እንነጋገር ከተባለ ደግሞ፣ የእኔ መዘግየት ተደምሮበት እዚህ ለመድረስ ትንሽ ጊዜ ወስዶብናል። ነገር ግን አሁን አሳክተነዋል። በአነስተኛ በጀትም ቢሆን ባገኘነው ስኬት እንዴት እንደኮራው ልነግራችሁ አልችለም። ፋጤ የተባለውን ይህን መፅሄት ላዘጋጀንለት ማህበረሰብ የምናስተዋውቅበት ጊዜ አሁን ነው።

ገና ብዙ ስራ ሊቀረን ይችላል ፣ ነገር ግን በአይነቱ ለየት ያልን ነን። ፋጤ በዓይነቱ የመጀመርያ፣ በእንግሊዝኛ እና የኢትዮጵያ የሥራ ቋንቋ በሆነው በአማርኛ የሚታተም የኤልጂቢቲኪው+ መፅሔት ነው። ትዕቢት የተሞላን እንዳንመስል እየሰጋን (በእራሳችን መንገድ በትህትና) ለመስራት ተስፋ የምናደርገው፣ በኢትዮጵያ ውስጥ እና በዓለም አቀፍ የሀበሻ ዲያስፖራ ለሚኖሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ 'የማይታዩ' የኤልጂቢቲኪው+ ሰዎች ላይ ብርሃን ማብራት ነው። በዚህ ልዩ እና ንቁ ማህበረሰብ ያላችሁ ሁላችሁም ወደፊት እንድትራመዱ እና የራሳችሁ ታሪክ ደራሲ እና ዋና ገፀ ባህሪያት እንድትሆኑ ለማበረታታት መጥተናል።

በዛሬው ዓለም ፋጤን መመስረት፣ አስቸኳይ እና እጅግ ግላዊ ነው። እየኖርን ያለነው የኤልጂቢቲኪው+ መብቶች ወደ ኋላ እየተንሸራተቱ ባሉበት ወቅት ነው። እነዚህን መብቶች መጀመርያ እውን ባደረጉት አንዳንድ ሀገራትም ይሄ ክስተት እይተለመደ መቷል። ደስ የሚለው ነገር፣ በየቦታው የለውጥ ዕድገት መኖሩ ነው። ነገር ግን በመላው አፍሪካ ሆሞፎቢያ እና ትራንስፎቢያ እየጨመረ መጥቷል። አገሮች በእኛ ላይ ህግን እያከረሩ እና ከባድ ቅጣትን እያስተዋወቁ ይገኛል። በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የኤልጂቢቲኪው+ ማህበረሰብ፣ በሌሎች የአህጉሪቱ ሀገራት ውስጥ እንዳሉት ሰዎች ዕለት ተዕለት ጥላቻን፣ ጥቃትን፣ ወንጀለኝነትን እና ስደትን እየተጋፈጡ ይገኛሉ። ይህ መቆሞ አለበት!

ከዚህ ዳራ በተቃራኒ፣ ከመቼውም ጊዜ በላይ አሁን፣ በማህበረሰብ ሃይል፣ በጋዜጠኝነት እና ታሪክን በማጋራት ለመታገል፣ ለማሳመን እንዲሁም ለክብር፣ ለነፃነት እና ለእኩልነት መብታችን መቆም እንደምንችል አምናለሁ። ፋጤ የተወለደው ፍጹም አስፈላጊ ስለሆነ ነው። ፋጤ የተመሰረተው፣ እይታችንን ለመጨመር፣ በተለምዶ በደበቀን ወይም በዝምታ ባፈነን ቋንቋ ውስጥ ይዘቶች እንዲኖሩን እና ትግላችንን ሳንሸፋፍን የምንበረታታበት ቦታ ለመፍጠር ከምን ጊዜውም በላይ አስፈላጊ ስለሆነ ነው። በዋናው የኢትዮጵያ ሚዲያ የማይታሰብ እንዲሁም በሌሎች የኤልጂቢቲኪው+ መፅሔቶች የማይዘገብ ቢሆንም፣ ፋጤ መፅሄት ላይ በሚያነቡት ነገር እራስዎን ሙሉ በሙሉ በሚያንፀባርቅ እና እውነተኛ በሆነ መልኩ ተወክለው እንዲያዩ እንፈልጋለን። ውስጣዊ ውስብስብነታችንን እንቀበለው።

ፋጤ እናንተን ለማሳወቅ፣ ለማነሳሳት፣ ለማበረታታት እና እንዲሁም ለማዝናናት መጥታለች። አጋሮችን እና ተመልካቾችን የእኛን ዓለም እንዲመለከቱ መስኮት ይከፍታል ብለንም ተስፋ እናደርጋለን። ይህ መፅሔት ብቻ አይደለም፤ የማንነታችንን ሙሉ ገፅታ የምናከብርበት፣ ጎጂ ትረካዎችን የምንቃወምበት እና የኤልጂቢቲኪው+ ሰዎችን ደስታ በሙሉ ድፍረት፣ በግልፅ ፣ በሚያማምሩ ሁኔታዎች የምንቀርፅበትን ቦታ የምናበጅበት ነው። የማያሻሙ ፓን አፍሪካዊ ዜናዎችን፣ ስለ ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች እና ፈጠራ ባለሙያዎች የሽፋን ዘገባዎችን፣ ወይም በቀላሉ ራሶን እዚህ ለማይት ስለመጡ — እናመሰግናለን። በእነዚህ ገፆች ውስጥ ቆም ብለው እንዲያስቡ፣ ፈገግ የሚያስብሉ፣ የአብሮነት ስሜት እንዲሰማዎት ወይም ትንሽ ትንፋሽ ሰብሰብ እንዲያደርጉ የሚረዳዎትን ነገር እንደሚያገኙ ተስፋ አደርጋለሁ።

ለአዲስ ጅማሬዎች፣ አስፈላጊ የሆኑትን ጉዳዮች ለመሸፈን፣ ያልተነገሩ ታሪኮችን ለማሰማት እና የምንፈልገውን ለውጥ ለማምጣት እንካችሁ ብለናል። 

በኩራት፣ በአንድነት እና ጤናማ ከሆነ እምቢተኝነት ጋር 

ቤዛ ለዓለም

የፋጤ ዋና አዘጋጅ

Scroll to Top