ደቡብ አፍሪካዊቷ ተመሳሳይ ሴት ፆታ አፍቃሪ የፓርላማ አባል ሆነች

Palomino Jama

ፓሎሚኖ ጃማ (ግራ) በደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ቶኮ ዲዲዛ (ቀኘ) አማካኝነት በሰኔ 17፣ 2025 ቃለ መሃላ ፈጸመች።

ፓሎሚኖ ጃማ በሰኔ 17 በዓለም አቀፍ የኩራት ወር ወቅት ቃለ መሃላ መፈጸሟ በአፍሪካ ፖለቲካ ውስጥ ለኤልጂቢቲኪው+ ውክልና መፈጠር አዎንታዊ እርምጃ ነው።

በቤዛ ለዓለም

ይፋዋ (አውት) የኤልጂቢቲኪው+ አክቲቪስት እና ደቡብ አፍሪካዊቷ የሴቶች መብት ተሟጋች ፓሎሚኖ ጃማ፣ ሰኔ 17 ቀን አዲስ የፓርላማ አባል ሆና በይፋ ቃለ መሃላ ፈፅማለች።

ጃማ ስለሁኔታው በ ፌስቡክገጿ ላይ አስተያየቷን ስትገልፅ፡ “ቤተሰቦቼ፣ ጓደኞቼ እና አጋሮቼን በጣም አመሰግናለሁ። መልካም ምኞቶቻችሁን በጣም አደንቃለሁ፣ በእውነት ጠንክሬ እንድሰራ እና አዲሱን ሃላፊነቴን በስኬት እንድወጣ አነሳስቶኛል” ስትል ተናግራለች። 

የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ (ኤኤንሲ) ፓርቲ አባል የሆነችው ጃማ፣ በደቡብ አፍሪካ ፓርላማ ውስጥ እንደ ዲን ማክፈርሰን፣ ዲዮን ጆርጅ እና ማፓሴካ “ስቲቭ” ሌትሲኬ ካሉ ሌሎች ይፋ ኤልጂቢቲኪው+ ህግ አውጪ ሚኒስትሮችን ተቀላቅላለች።

ጃማ ባለፈው ዓመት ቃለ መሃላ ከፈፀሙት የኤኤንሲ ባልደረባዋ ሌትሲኬ በመቀጠል፣ ሁለተኛዋ፣ ይፋ ጥቁር ደቡብ አፍሪካዊት ተመሳሳይ ሴት ፆታ አፍቃሪ የፓርላማ አባል ትሆናለችም ተብሏል። ሌትሲኬ፣ የኤልጂቢቲኪው+ አክቲቪስት እና ሳይሪል ራማፎሳ ፕሬዝዳንት ከመሆናቸው በፊት ምክትል የነበረች ስትሆን፣ በሃገሪቱ ውስጥ ባሉ እንደ ሊን እና ዛኬሌ ባሉ ሌሎች የፖለቲካ ፈርቀዳጆች ኮቴ ተከትለው ፓርላማ ገብተዋል። ድብልቅ ዝርያ ያላቸው፣ ይፋዋ ተመሳሳይ ሴት ፆታ አፍቃሪ ሊን ብራውን፣ እ.ኤ.አ በ 2014 በቀድሞው ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ የካቢኔ ሚኒስትር ተደርገው ተሹመው ነበር፤ በተመሳሳይ ዓመትም የዴሞክራቲክ አሊያንስ ፓርቲ አባል ዛኬሌ ቤሌ የመጀመሪያው ጥቁር የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ የፓርላማ አባል ሆነው ተመርጠዋል።

ምንም እንኳን ደቡብ አፍሪካ የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻን ጨምሮ፣ የኤልጂቢቲኪውን መብቶች በህገ መንግስቷ የምታከብር ብቸኛዋ አፍሪካዊት ሀገር ብትሆንም፣ የኤልጂቢቲኪው+ ማህበረሰብ አሁንም ከህብረተሰቡ ውስን አካላት ብዙ ፈተናዎች ይገጥሟቸዋል።

አገር በቀሉ ኤልጂቢቲኪው+ ድርጅት ኤምቤሬስ ዳይቨርሲቲ ሙቭመንት የጃማ ሹመት ለንቅናቄው ጥሩ እርምጃ ሲል አወድሷታል። "ፓሎሚኖ ልምድ ያላት የኩዊር አክቲቪስት እና ቁርጠኛ የሆነ የአመራር እና የአገልግሎት ታሪክ ያላት ማህበረሰብ ገንቢ ነች… ወደ ፓርላማ መሰማራቷ [እና] ቦታውን መያዟ፣ በህዝብ ቢሮ ውስጥ ለወጣት እና ለኩዊር ውክልና ከፍተኛ ትርጉም የሚሰጥ ነው" ሲል ቡድኑ፣ ለአሜሪካ ሚዲያ ሆን ተብሎ የሚፈፀም ማስፈራሪያ ነው” ብሏል።.

የኤልጂቢቲኪው+ ሰዎች በከፍተኛ የስልጣን እርከኖች ውስጥ መገኘት ከእይታ እና ውክልና በላይ ነው። ጉዳዮች በጠረጴዛ ዙሪያ ሲሞገቱ ማህበረሰቡ ድምፅ ይኖረዋል፣ ይህም ኤልጂቢቲኪው+ ሰዎች የፖለቲካ ተፅዕኖን ተጠቅመው በህግ የተደገፈ ለውጥ እንዲያቀጣጥሉ፣ ፖሊሲዎችን እና ሌሎች የመንግስት እርምጃዎችን ተጠቅመው የህዝብን አስተያየት ለመቅረፅ የሚያስችል ኃይል ይሰጣቸዋል። 

የተባበሩት መንግስታት የበለጠ ሰፊ ጥቅሞችን እንዳሉት ያምናል። መንግሥታዊ ያልሆነው ድርጅት በ2023 መግለጫ ሲሰጡ ማውጣቱን አስከትሎ፣ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም “የኤልጂቢቲኪው+ ሰዎች በፓርላማ ውስጥ ያላቸው የፖለቲካ ውክልና እና በምርጫ ወቅት የሚኖራቸው ተሳትፎ ሰብዓዊ መብቶችን ለማሻሻል እና ጠንካራ ዴሞክራሲን ለመገንባት አስፈላጊ ነው” ሲል ረፖርቱ

ምንም እንኳን በአፍሪካ አህጉር ያለው ውክልና አሁንም በጣም ዝቅተኛ ቢሆንም ግን ይፋ የኤልጂቢቲኪው+ ፖለቲከኞች ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ዓለም አቀፍ ዕመርታዎችን እያደረጉ ነው። ከ1976 ጀምሮ እስከ እ.ኤ.አ 2018 መጀመሪያ ድረስ፣ በጠቅላላው 326 ግልጽ ኤልጂቢቲ ተወካዮች በ48 አገሮች ውስጥ የብሔራዊ ፓርላማ አባል ሆነው ተመርጠዋል ሲል፣ በቻፕል ሂል ዩናይትድ ስቴት የሚገኘው የሰሜን ካሮላይና ዩንቨርሲቲ፣ የኤልጂቢቲኪው ውክል እና መብት ጥናት ቡድን ያሳያል። 

በአፍሪካ የመጀመሪያው የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ የፓርላማ አባል ዛኬሌ መቤሌ፣ ከአስር ዓመታት በፊት ከማንባኦንላይንጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት፣ “አስከፊ ከሆኑት የሆሞፎቢያ ጉዳቶች አንዱ በወጣት ኤልጂቢቲ ሰዎች ራስ መተማመን ላይ ያለው ጎጂ ውጤት ነው… በህብረተሰቡ ውስጥ በይፋ የሚታዩ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን አሸናፊዎች መኖራቸው፣ ለወጣት የኤልጂቢቲ ሰዎች በራስ የመተማመን ስሜት እንዲገነቡ ለማነሳሳት አርዓያዎች እንዲኖራቸው እና ለህልሞቻቸው መሳካት ጠንክረው እንዲሰሩ በማድረግ ጉዳቱን መቋቋም ያስችላል።" ብለዋል። 

Scroll to Top