በብሬንዳ ቢያ ኢንስታግራም ገጽ ላይ የተለጠፉ ምስሎች
በባለፈው ዓመት የኤልጂቢቲኪው+ ሰዎች ከህግ አንፃር እንደ ወንጀለኛ በሚቆጠሩባት የመካከለኛዋ አፍሪካ አገር፣ የካሜሮን ፕሬዚዳንት ፖል ቢያ ሴት ልጅ ብሬንዳ ቢያ ተመሳሳይ ሴት ፆታ አፍቃሪ መሆኗን በይፋ ተናገረች።
በቤዛ ለዓለም
የካሜሩን ፕሬዝዳንት ሴት ልጅ ብሬንዳ ቢያ፣ በካሜሩን ተወላጅ ሙዚቀኛ ዴንሲያ ሶንኪ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የስም ማጥፋት ውንጀላ ጋር በተያያዘ፣ በጄኔቫ ስዊዘርላንድ የህግ ክርክር ውስጥ ገብታለች ሲል የስዊዝ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን አገልግሎት የሆነው ስዊዝኢንፎበግንቦት ዘገባው አስነብቧል። ምንም እንኳን የጉዳዩ ዝርዝሮች በፋጤ በተናጥል ሊረጋገጡ ባይችሉም፣ ፍርድ ቤቱ በቢያ ላይ ብይን ሰጥቷል ተብሏል። የፋጤ.
በሀገሯ ሙዚቀኛ መሆን ምትመኘው እና አወዛጋቢ የሆነችው ቢያ፣ ባለፈው አመት ተመሳሳይ ሴት ፆታ አፍቃሪ መሆኗን በተናገረችበት ወቅት ዓለም አቀፍ አርዕስት ለመሆን በቅታለች። ብራዚላዊት ሞዴል ከሆነችው ሌዮን ቫለንሳ ጋር ስትሳሳም የሚያሳይ ምስል ካጋራች በኋላ፣ ቢያ የፆታ ዝንባሌዋን ከፈረንሳይ ጋዜጣ ለ ፓሪዚየንባደረገችው ቃለ-ምልልስ አረጋግጣለች። ከ1982 ጀምሮ በስልጣን የቆዩት፣ በዘጠናዎቹ እድሜ ላይ ያሉት የካሜሩኑ ፕሬዝዳንት አባቷ ፖል ቢያ እና እናቷ ቀዳማዊት እመቤት ሻንተል ቢያ፤ ይህን የድፍረት እርምጃዋን ድንገተኛ እና ያልተጠበቀ እንደሆነ ተናግረዋል።
ብሬንዳ ቢያ ባለፈው አመት ቫለንሳን አቅፋ በኢንስታግራም ባሳየችው ልጥፍ ላይ "እኔ በአንቺ አቅሌን ስቻለሁ፣ እናም ዓለም እንዲያውቅልኝ እፈልጋለሁ" ስትል ፅፋለች። ከቤተሰቧ ተቃውሞ ቢገጥማትም ቢያ በወቅቱ ልጥፉን አላነሳችውም ነበር።
መቀመጫወን በእንግሊዝ ያደረግው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሂውማን ዲግኒቲ ትረስትመረጃ መሰረት፣ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት በካሜሩን ሕግ የተከለከለ ሲሆን የገንዘብ እና እስከ አምስት ዓመት በሚደረስ የእስር ቅጣት ያስቀጣል። አንድ የካሜሩን የመንግሥት ባለስልጣን ከቢቢሲ እንደተናገሩት፣ ይህ "የቤተሰብ ጒዳይ" በመሆኑ ባለሥልጣናቱ በጉዳዩ ላይ አስተያየት ላለመስጠት መወሰናቸውን ገልፀዋል።
"ለካሜሩን ቀዳማዊት ሴት ልጅ ብሬንዳ ቢያ፣ በጣም ደስተኛ ነኝ! ይሁን እንጂ በካሜሩን ውስጥ የፀረ-ኤልጂቢቲኪዉ ህጎች በአብዛኛው ድሆች ላይ ያነጣጥሩ መሆኑን ዋና ማሳያ ነው። ሀብት እና ግንኙነቶች ለአንዳንዶች መከታ ሲሆኑ፣ ሌሎች ግን ከባድ መዘዞችን ይጋፈጣሉ" ስትል በእንግሊዝ መሰረቷን ያደረገችው ካሜሩናዊቷ የኤልጂቢቲኪዉ+ አክቲቪስት ባንዲ ኪኪ ስለጉዳዩ በወቅቱ በፌስቡክ ልጥፍ ባሰፈረችው ፅሑፍ አስተያየቷን ሰጥታለች።
ምንም እንኳን ያላት የህይወት ደረጃ በሀገሯ ውስጥ በጣም ከባድ ከሆኑት የፀረ-ኤልጂቢቲኪው+ ትንኮሳዎች ቢከላከልላትም፣ ቢያ ከካሜሩን የሀገር ውስጥ ፀረ-ኤልጂቢቲኪው ሕግ ደጋፊዎች ዘንድ ትችት ገጥሟታል። ፊሊፕ ኤንሱ ከዲዲኤችፒ ንቅናቄ በቢያ ላይ ለሀገሪቱ የህዝብ አቃቤ ህግ ቅሬታ ማቅረባቸው ተዘግቧል።
ብሬንዳ ቢያ ባለፈው ዓመት ባደረገችው ቃለ ምልልስ "ራስን መግለጥ ጠንካራ መልዕክት ለማስተላለፍ እድል ነው" ስትል ተናግራለች። ከአባቷ ፕሬዝዳንታዊ ስልጣን በፊት ጀምሮ ስለነበረው የፀረ-ኤልጂቢቲኪው ሕግ ስትናገር "ኢ-ፍትሃዊ ነው እናም የእኔ ታሪክ እንደሚለውጠው ተስፋ አደርጋለሁ" ስትል አክላለች።

