የለውጡ ተሳታፊ ይሁኑ
ጥበብ ስራ አስተዋጽዖ አበርካቾች የተደረገ ግብዣ።
በአንድ የተወሰነ ጭብጥ ወይም ጉዳይ ላይ የግል ፅሑፍ፤ መረጃን መሰረት ያደረጉ እና አሳማኝ ሪፖርታዦች፣ ቃለ-መጠይቆች፣ የምርምር ወይም የፈጠራ ስራዎችን ማበርከት ይፈልጋሉ? ለማጋራት የሚፈልጉት የፎቶግራፍ፣ የምስል ወይም የግራፊክስ ዲዛይን ችሎታ አሎት? ፅሆፎችን ማረም ወይም መተርጎምስ? የፈጠራ ችሎታዎን ተጠቅመው፣ ለማህበረሰባችን የህይወት ተሞክሮዎችን ወይም የእርሶን ልዩ እይታ ለመግለፅ ይፈልጋሉ?
ፋጤን በመቀላቀል ችሎታውን እውን ያድርጉ።
አስታውሱ፣ ተልእኳችን ኤልጂቢቲኪው+ ኢትዮጵያውያንን እና ዓለም አቀፍ የሃበሻ ዳያስፖራን የሚመለከቷቸውን ዘገባዎች ከመላው አፍሪካ በመዳሰስ ማሳወቅ፣ ማነሳሳት እና ማበረታታት ነው። በግልፅ መናግር ብቻ ሳይሆን አሳቢ እና ገንቢ የሆነ ትርጉም ያለው ይዘት በመፍጠር፣ እዚህ ገፅ ላይ በገለፅናቸው መርሆች መሰረት በቅንነት፣ በትክክለኛ እና ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ንቁ ማህበረሰባችንን እናሳተፍ። ይህ ማንነታችንን ለማክበር፣ መሰረታዊ መብቶቻችንን የምናረጋግጥበት እና የምንፈልገውን ለውጥ እውን ለማድረግ ልዩና ታሪካዊ አጋጣሚ ነው።
ድምፆን ያሰሙ። እራሳችንን በእውነት ተንጸባርቆ የምናይበት ቦታ እንገንባ። ፕሮፖዛል ወይንም ሃሳቦትን* በአጭሩ በ info@fattehmagazine.com ላይ በኢሜል በመላክ ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መልእክት በመላክ ያካፍሉ።
*ማሳሰቢያ፡ ፋጤ በሰብዓዊ መብቶች ላይ አትኩሮ የሚሰራ፣ ለትርፍ ያልተቋቋመ ገለልተኛ መፅሔት ነው። በአሁኑ ጊዜ የበጎ ፈቃደኛ አስተዋፅዖ አበርካቾችን እንፈልጋለን። እያንዳንዱን ፕሮፖዛልና ሃሳብ ከልባችን እያደነቅን፣ ከተላከልን ወይም ካዘዝነው/ከተነጋገርነው ሥራ በኋላም ቢሆን የእኛን የአርታያን እሴቶች ወይም ደረጃ የማያሟላ ማንኛውንም ይዘት እንዳይታተም የመከልከል መብታችን የተጠበቀ ነው።
