ናሚቢያዊው ጌይ አክቲቪስት የዓለም አቀፍ ኤልጂቢቲኪው+ መብቶች ኮሚሽንን ለመምራት ተሾመ

የናሚቢያ ኤልጂቢቲኪው+ አክቲቪስት ፍሪድል ዳውሳብ

በባለፈው ዓመት በናሚቢያ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ወንዶችን የሚወነጅል ህግን የሚቃወም ክስን በተሳካ ሁኔታ የመራው ፍሪዴል ዳውሳብ፣ የከላይዶስኮፕ ትረስትን አዲስ ኮሚሽን ተቀላለቀለ።

በቤዛ ለዓለም

የናሚቢያ አክቲቪስት ፍሪድል ዳውሳብ በቅርቡ የኤልጂቢቲኪው+ መብቶች ላይ እየደረሰ ያለውን ተቃውሞ እና በደል ለመፋለም የተቋቋመው አዲስ እንቅሰቃሴ መሪ ሆነው ተሾሙ። መሰረቱን በእንግሊዝ ያደረገው፣ የዓለም አቀፉ የበጎ አድራጎት ድርጅት ከላይዶስኮፕ ትረስት፣ ኮሚሽኑን በሰኔ ወር በነበራቸው የኩራት ወር ዓመታዊ ፓርላማ ግብዣ ላይ አስጀምሯል።

"በናሚቢያ የነበረውን ፀረ-ኤልጂቢቲኪው+ ህግ በመሻር መሪ፣ ቀናተኛ ተሟጋች እና ተዋናይ የነበረውን — ፊሪዴል ዳውሳብን የዓለም አቀፉ የኤልጂቢቲኪው+ መብቶች ኮሚሽን የመጀመሪያው ኮሚሽነር መሆኑን ስንገልፅ በታላቅ ክብር ነው።" ሲል ከላይዶስኮፕ ትረስት በኢንስታግራም ልጥፍ አስፍሯል።.

የትረስቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አሌክስ ፋሮ፣ ኮሚሽኑ፣ "የምርመራ አካል እና የድጋፍ ጩኸት" ነው ብለዋል። እንደ የፒንክ ኒውስ ዘገባ “በነዚህ 18 ወራት ውስጥ ኮሚሽኑ እየጨመረ የመጣውን ፀረ-ኤልጂቢቲኪው+ መስፋፋት ምክንያቶችን የሚያጣራ ሲሆን፣ ስልታዊ ምክሮችን በማዘጋጀት ይህን እንቅስቀሴ ለመቀልበስ ለሚሰሩ መንግስታት፣ የሲቪል ማህበረሰባት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ስልታዊ ምክሮችን እና የመፍትሄ መንገዶችን ያቀርባል።

ለሁለት ዓመታት በዩናይትድ ኪንግደም የናምቢያ አየር መንገድ የበረራ አስተናጋጅነት ሲሰራ የነበረው ፊሪዴል፣ አክቲቪስት የሆነው ወደ ናሚቢያ ከተመለሰ በኋላ ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ አይቢኤስ/የዓለም ዩኒቨርስቲ አገልግሎት የተባለ የበጎ አድራጎት ድርጅትን ተቀላቀለ። በዚህ በጎ አድራጎት ድርጅት ለኤልጂቢቲኪው+ ሰዎች፣ በወሲባዊ ጤና ፕሮግራሞች እንዲሁም ከኤችአይቪ/ኤድስ ጋር ለሚኖሩ የአእምሮ ጤና ፕሮግራሞች ላይ ሲሰራ ቆይቶ፣ በኋላም ወደ ፖዘቲቭ ቫይብስ ትረስት፣ ዘ ሬንቦው ፕሮጀክት እንዲሁም በብሔራዊው ኤልጂቢቲኪው+ ድርጅት አውትራይት ናምቢያ፣ በዋና ዳይሬክተርነት አገልግሏል።

የዳውሳብ የአዲሱ ዓለም አቀፍ ኮሚሽን ሹመት፣ ሌሎች የዘመቻ አራማጆችን በስራው እንደሚያበረታታ እና እንደሚያደፋፍር ይጠበቃል። ዳውሳብ የናሚቢያ የፍርድ ቤት ክስ ጉዳዩን፣ ከብሪቲሽ በጎ አድራጎት ድርጅት ሂውማን ዲግኒቲ ትረስት ድጋፍ ጋር በመሆን፣ በቅኝ ግዛት ዘመን በወንዶች መካከል የሚደረጉ ተመሳሳይ ፆታዊ ድርጊቶችን የሚከለክሉ (የ"ሰዶማዊ" እና "ተፈጥሮአዊ ያልሆነ ፆታዊ ወንጀሎች") ህጎችን ከያዘው ደቡባዊ አፍሪካዊቷ አገር ህገ መንግስት፣ ታሪክዊ በሆነ መልኩ እንዲሻር ያስቻለው ባለፈው ዓመት ነበር።

በባለፈው አመት በናሚቢያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተተላለፈውን ብይን አስመልክቶ "የፈለግነውን ሰው ማፍቀር ከእንግዲህ ወዲህ ወንጀል አይሆንም" ሲል ዳውሳብ ለ ከቢቢሲመግለጫ ሰጥቷል። አክሎም "ከእንግዲህ በማንነቴ የተነሳ በገዛ ሀገሬ የወንጀለኛነት ስሜት አይሰማኝም" ሲል ተደምጧል።

ዳውሳብ፣ ለቶማስ ሮይተርስ ፋውንዴሽን የሚዲያ አገልግሎ ኮንቴክስት፣ "በብዙ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን ወንዶች እና ትራንስ ሴቶች ጭንቅላት ላይ የተንጠለጠለ ሰይፍ ተወግዷል። የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን ጠሎች ከአሁን በኋላ ምርኩዝ የላቸውም። ጨካኞች በህጋዊ ስርዓታችን እና በህጋችን ውስጥ እኛን ለመጨፍለቅ ሊጠቀሙበት የሚችሉት መሳሪያ የላቸውም።" ሲል ተናግረዋል።

አንዳንዶች ዳውሳብን ‘የነፃነት ታጋይ’ ብለው ሲያወድሱ፣ በናሚቢያ የኤልጂቢቲኪው+ መብት ተቃዋሚዎች ደግሞ ስራውን አውግዘዋል። ዳውሳብ ውሳኔው ከተላለፈ በኋላ ተቃውሞ እንደነበረ ገልፆ፣ "በኢንተርኔት ላይ በተለይም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የጥላቻ ወንጀሎች መበራከታቸውን አይተናል። በተለይም ወጣቶች እና ትራንስ ሰዎች ላይ ብዙ መፈናቀልን [ተመልክተናል]" ሲል ዳውሳብ ተናግሯል። 

ጉዳዩን ለማወሳሰብ የናሚቢያ መንግሥት፣ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔ ላይ ይግባኝ ብሏል። ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ “ሕገ መንግሥቱ በፆታ ላይ የተመሠረተ መድልዎን ብቻ ነው እገዳ ያደረገው ወይስ፣ ህጉ የፆታ ተማርኮን ይጨምራል አይጨምረም” ሲል በሐምሌ 2025 ተጨማሪ ማብራሪያም ጠይቋል ሲል ኮንቴክስት ዘግቧል። በወቅቱ ይግባኙ የሚወሰንበት ቀን መግለጫ አልተሰጠበትም። 

ባለፈው አመት የዳውሳብ ፍርድ ቤት ድልን ተከትሎ፣ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ናንጎሎ መምባ የኤልጂቢቲኪው+ መብቶችን የበለጠ ለማደናቀፍ ጋብቻን በሁለት ተቃራኒ ፆታዎች መካከል ብቻ የሚደረግ መሆኑን የሚገልጽ ህግ አሳልፈዋል። አዲሱ መንግስት በኤልጂቢቲኪው+ ጉዳዮች ላይ ምን አይነት አቋም እንደሚይዝ ለማየት በመጋቢት ወር ስራ የጀመረችው የሀገሪቱ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ኔቱምቦ ናንዲ-ንዳይትዋህ ላይ ሁሉም ዓይኖች አርፈዋል።

እስከዚያው ድረስ፣ "ከፍተኛ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ህገ መንግስት፣ ማንኛውንም በናሚቢያ ውስጥ ያለ ሰው፣ ፆታ ተማርኮአቸው ወይም ፆታ ማንነታቸው ምንም ይሁን ምን፣ ከለላ እና ጥበቃ ሊደረግላቸው እንደሚገባ አበክሮ እንሚያሰምርበት ተስፋ እናደርጋለን" ሲል ዳውሳብ ተናግሯል።

Scroll to Top