የኢትዮጵያ ቀስተ ዳመና ሰራዊት

አንዳንዶች 'ኩዊር' የሚለውን መጠርያ ከተቃራኒ ፆታ አፍቃሪ (ሄትሮሴክሿል) ውጪ የሆኑትን ወይንም የፆታ ማንነታቸው ሲወለዱ ከተለየው ፆታቸው ጋር የማይዛመዱትን (ሲስጀንደር ያልሆኑ) ሰዎችን አካተው ለመግለፅ ይጠቀሙበታል። ሌሎች በዚህ መጠርያ አይስማሙም። ፋጤ በአብዛኛው 'ኤልጂቢቲኪው+' የሚለውን መጠቀምን ይመርጣል።

ኢትዮጵያውን ኤልጂቢቲኪው+ ማህበረሰብ ለህልውናቸው እና ለመሰረታዊ ሰብዓዊ መብታቸው ግንባር ላይ ሲሟገቱ፣ የማህበረሰቡ ተሟጋቾች፣ አክቲቪስቶች፣ እና ደጋፊዎች አንድ ላይ ኃይላቸውን በማቀናጀት ልብን፣ አዕምሮን፤ ህግ አርቃቂ ድሎችን ለማግኘት እና ለማሸነፍ ስትራቴጂኪያዊ ዘመቻዎችን ማቀናጀት አለባቸው።

በቤዛ ለዓለም

የቀስተ ዳመና ሰንደቅ፣ ለኤልጂቢቲኪው+ ሰዎች የኩራትና የድጋፍ ሁለንተናዊ ተምሳሌት ነው። በማህበረሰቡ አባላት እና ደጋፊዎች ክብረ በዓላት ላይ እና ለመብታቸው በሚያደርጉት ተጋድሎ ላይ በማውለብለብ እንደ ልዩ ምልክትም ይጠቀሙበታል። በሰንደቁ ላይ ያሉት በርካታ ቀለሞች በፆታዊ ተማርኮ እና ባህርያት፣ የፆታ ማንነቶች እና መገለጫዎች ላይ ተመሰርቶ በማህበረስቡ ውስጥ ያሉትን በርካታ እና የተለያዩ ማንነቶች የሚያንፀባርቁ ናቸው። ከዚህ ደማቅ ዓርማ ጀርባ ሰዎች ነው "የቀስተ ዳመና ሠራዊት" ብለን የጠራናቸው።

አንዳንድ የዚህ ዓለም አቀፍ ሠራዊት አባላት ግንባር ቀደም ተጋዳዮች ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ ከያሉበት ሆነው ይዋጋሉ። ይህ ሁኔታ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገራት ከሚገለፅበት የበለጠ የትም ቦታ የለም። “የቀስተ ዳመና ሠራዊት” የሚለው መጠሪያ፣ ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑ (ጌዬ፣ ሌዝቢያን፣ ትራንስ፣ ባይሴክሿል፣ ኩዊር) ሰዎች ለመሰረታዊ ሰብዓዊ መብቶቻቸው እና ለህልውናቸው የሚሟገቱበትን ጥልቅ ምንነት የሚያንፀባርቅ ቃል ነው። ትግላቸው ምናልባት የተለየ ሊሆን ይችላል ነገር ግን ከመላው አህጉር ትግል ጋር የሚመሳሰል ነው።

በበርካታ የአፍሪካ ሀገራት ፀረ-ኤልጂቢቲኪው+ ንግግሮች እና እንቅስቃሴዎች እየጨመሩ ነው። በተለይ እንደ ዩጋንዳ እና ጋና ባሉ ሀገራት ጥብቅ ህጎች እየረቀቁ እና ከባድ ቅጣቶች ስራ ላይ እየዋሉ ያለበት ሁኔታ ይታያል። የህግ መሻሻል በተገኘባቸው እንደ ቦስትዋና እና አንጎላ ባሉ ሀገራት ሳይቀር፣ ማህበረሰቡ አሁንም ከሰፊው ህዝብ ስጋት እና አደጋ እየተጋፈጡ ይገኛሉ። 

በአንዳንድ ቦታዎች ሁኔታዎቹ በጣም አስጊ ከመሆናቸው የተነሳ፣ አምንስቲ ኢንተርናሽናል በዚህ ጉዳይ ላይ ያወጣውን ረፖርቱ ይፋ ሲያደርግ፣ "የመጥፋት አደጋ ላይ ወድቀናል፤ ፀረ-ኤልጂቢቲኪው+ አዝማሚያዎች እንዲሁም ህግንና የሰብዓዊ መብትን እንደመሳሪያ መጠቀም መጨመር ይታያል ብሎ ድርጅቱ ተናግሯል።" 

የአምንስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ክልላዊ ዳይሬክተር የሆኑት ታይጌሬ ቻጉታ፣ ይህ መግለጫ የተጋነነ እንዳልሆነ አበክረው ይገልፃሉ። መቀመጫቸውን ጆሃንስበርግ ያደረጉት እኝህ ባለሙያ ባለፈው ዓመት እንደጠቀሱት፣ ''በመላው አፍሪካ፣ የኤልጂቢቲኪው+ ግለሰቦች በዕድገታቸው እና በማንነታቸው ላይ ቀጣይነት ያለው፣ አስጨናቂ የሆኑ ተቃውሞችን በመጋፈጥ ሕጋዊና ማህበራዊ መብቶቻቸው ላይ ጉልህ እንቅፋት እየገጠማቸው ይገኛሉ'' ብለዋል። 

"ህጋዊ መሰረት የሌለው እስራት እና በእስር ማቆየት እየተለመደ መጥቷል። እራስን መሆን እንደ ወንጀል ተደርጎ እየተቆጠረ ነው። በአንዳንድ አካባቢዎች የሞት ቅጣት በግለሰቦች ላይ እንደ አንድ አስደንጋጭ ሰቆቃ ይንዣበባል። ይህ አንድ ሰው እራሱን በመሆኑ ብቻ የሚገጥመው አሰቃቂ ኢፍትሃዊ ቅጣት ነው። እየተጋፈጥን ያለነው ነገር እየከፋ የሚሄድ ሆሞፎቢክ የህግ ጦርነት ነው ብለን ልንገልጸው የምንችለው ነገር ብቻ ነው።"

በኢትዮጵያ የኤልጂቢቲኪው+ ማህበረሰብ፤ የተመሳሳይ ፆታ ፍቅርን ከሚወነጅል፣ ከሚቀጣ እንዲሁም አካላዊ ጥቃት፣ መድሎና እንግልትን በሚፈጥር ፈታኝ ፓለቲካ እና ማህበራዊ ሁኔታ ውስጥ እያሉም ክብርን፣ ተቀባይነት እና እኩልነት ለማግኘት ድምፅ ሳያሰሙ እየታገሉ ይገኛሉ።

የፕሮግሬሲቭ ኩራት ባንዲራ፣ ኤልጅቢቲኪው+ ትራንስጀንደር እና ኢንተርሴክስ ሰዎችን ጨምሮ፣ የተገለሉ የማህብረሰቡን ንዑስ ክፍሎችን የሚወክል ነው።

በመላው አገር፣ ከፍተኛ ተደማጭነት ያላቸው የሃይማኖት መሪዎች እና የመንግሥት ተዋናዮች በተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ሰዎች ላይ የኃይል እርምጃ እንዲወሰድ፣ የፍርሃትና የጥላቻ መንፈስ እንዲሰፍን የሚደረጉ ፅንፈኛ እርምጃዎችን እያበረታቱ ይገኛሉ። በሰፊው ተንሰራፍቶ የሚገኙት ማህበራዊ አመለካከትና ባህላዊ ደንቦች፣ የኤልጂቢቲኪው+ ሰዎች በአንድ ወቅት ቤት ብለው ይጠሯቸው በነበሩበት ቦታዎች መኖር በጣም አደገኛ እንዲሆንባቸው አድርገዋል። ቀድሞ በማህበረሰቡ መካከል እንደሌለ ተደርጎ የነበረው ይህ የኤልጂቢቲኪው+ ማህበረስብ፣ አሁን አሁን "ሰዶማዊነትን እቃወማለሁ" በሚሉ፣ ፍፁም ማንነቱን በማይወክሉ መፈክሮች፣ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ግልጽ ግብ ግብ ገጥሟል። 

የኢትዮጵያ ኤልጂቢቲኪው+ ማህበረሰብ እያጋጠሙት ያሉት ፈተናዎች ከወንጀል ክስ የዘለሉ ናቸው። ግለሰቦች በህግ ብቻ ሳይሆን እየተንሰራፋ በመጣው የህዝብ መንጋ ጥቃት ኢላማ ሆነዋል። ከሦስት ዓመታት በፊት ነው የጀመርነው ያሉት ሁለት የሃይማኖት ቡድኖች፣ ይህን አፀያፊ የ[ፀረ-ኤልጂቢቲኪው] ተቃውሞ ቀድሞ ያስጀመረ የሚለውን ማዕረግ ለመውሰድ በአደባባይ ሲከራከሩ ተሰምተዋል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ፣ በቀጥታ ዥረት (ላይቭ ስትሪም) ይዘት ፈጣሪዎች ማበረታቻ እና ቅስቀሳነት፣ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን ናቸው ተብለው የተገመቱ ሰዎችን ለመግደል ቅስቀሳ በቲክ ቶክ ላይ እንዲለመድ እና ሌሎችን ደግሞ ዓመፅ እንዲቀሰቅሱ እና ያላሰለሰ ጭካኔያዊ ተግባራትን እንዲፈፅሙ እንዲያበረታቱ ሆኗል።

እነዚህ የማያቋርጡ ዛቻዎች፣ ትንኮሳ እና ጥቃት የዕለት ተዕለት እውነታዎች ሆነዋል። ብዙዎችም ለመኖር ሲሉ እውነተኛ ማንነታቸውን እንዲደብቁም ተገደዋል። የሰብዓዊ መብት ድርጅቶቹ አውት ኢን ኢትዮጵያ እና ቤተ ጉራማይሌ በመተባባር በቅርብ ጊዜ ባወጡት "አውት ኢን ኢትዮጵያ" በተሰኘ ረፖርቱ ፣ እየተባባሰ ከመጣው ምስል አንፃር፣ 94% የሚሆኑ የኤልጂቢቲኪው+ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሀገሪቷ፣ ለመኖር ደህንነቷ የተጠበቀ ነው ብለው እንደማያምኑ መናገራቸው የሚያስደንቅ አይደልም ብለዋል። 

ሌላው እያደገ የመጣ ልማድ፣ ኤልጂቢቲኪው+ ግለሰቦችን እና አጋሮቻቸውን ማጋለጥ ነው። ይህም የሁኔታውን አደገኛነት እና እየተባባሰ የመጣውን አመፀኝነትን ፍራቻ ጨምሮ ማህበራዊ መገለልን ያሳያል። መንግስትም ሆነ መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት እነዚህን ተግባራት ሲያበረታቱ የኤልጂቢቲኪው+ ማህበረሰቡ ፅናት ወሳኝ ነው።

ይህ ነቅተን መኖር ያለብን ጊዜ ነው። የኤልጂቢቲኪው+ ግለሰቦች እንደ ጠላት፣ እንግዳ ነገር ወይም ያፈነገጡ ተደርገው መታየት እስኪያቆሙ ድረስ በዚህ ውጊያ ሁላችንም ስደተኞች እንደሆንን ማስታወስ ይኖርብናል። ከዚህ ሁኔታ አንፃር አንዳንድ የማህበረሰባችን አባላት ብልሃት በተሞላበት ግን፣ ልብን በሚነካ መልኩ 'ዜጋ' የሚለውን አማርኛ ቃል፣ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያንን ለመግለፅ የተጠቀሙ ሲሆን፣ ይህ ቃል የአንድ ሀገር ዜጋ የሚል ትርጉም አለው። እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ኤልጂቢቲኪው+ በሀገራችን የመሆን መብት እና ትክክለኛ ቦታ ያለን እንደመሆናችን የምንጠይቀው የተለየ መብት ወይም ጥቅማ ጥቅም አይደለም፤ ይልቅ መሠረታዊ የሰብዓዊ መብቶቻችን እውቅና እንዲሰጣቸው፣ እንዲከበሩ እና ጥበቃ እንዲደረግላቸው ፍትህ ለማግኘት ነው።  

"በዚህ ውጊያ ሁላችንም ስደተኞች እንደሆንን ማስታወስ ይኖርብናል።"

የቀስተ ዳመና ሠራዊት አባል ለመሆን የሚፈልጉ አጋሮች ሆሞፎቢያን (ፀረ-ኤልጂቢቲኪው+) እና ትራንስፎቢያን (የፆታ ማንነታቸውን የቀየሩትን/በመቀይር ላይ ያሉትን ተቃውሞ) በመዋጋት እና እኩልነትን በመደገፍ አስተዋፅዖ ሊያበረክቱ ይገባል። የሚያጋጥሙንን ፈታኝ ሁኔታዎች ክብደት ብንገነዘብም፣ በአንድነት ግንዛቤን ለመጨመር፣ የኤልጂቢቲኪው+ ሰዎች ተቀባይነትንና እይታን ለማሰደግ ሀገር በቀል እንቅሰቃሴ በማድረግ ለተሻለ ነገ ተስፈኞች ነን። ተደማጭነት ያላቸው የባል መሪዎች፣ እንደ መገናኛ ብዙኃን እና መዝናኛ ባሉ ቁልፍ መስኮች ያሉትን ልማዶች በመቃወም ከእኛ ጋር እንዲተባበሩ እና አቋማቸውን እንዲያሻሽሉ አሳማኝ ስልቶችን መጠቀም አለብን።

የህዝብን አስተያየት መቀየር እና በህብረተሰቡ ውስጥ ሌሎች አወንታዊ ለውጦችን ለማምጣት ብልህ፣ ጥንቃቄ ያለው ፈጠራ እና በሚገባ የተደራጀ ዘመቻ ይጠይቃል። አስቸኳይ የሆነ የፓለቲካ ተሃድሶም አስፈላጊ ነው። ከአካባቢው ወረዳ ምክቤት ጀምሮ እስከ ከፓርላማ እና ጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ድረስ ለምናደርገው እልህ አስጨራሽ ከባድ ትግል ያለንን ኃይል ሁሉ መሰብሰብ አለብን። የመንግስት ባለስልጣናት ኤልጂቢቲኪው+ ሰዎችን እንዲጠብቁ እና እንዲያበረቱ ለማሳመን ተሟጋቾቻችን እና አክቲቪስቶቻችን የበለጠ ስልታዊ እና ትኩረት የተሞላበት አካሄድ መከተል አለባቸው። ፖሊሲ አውጪዎችን ለውጥ የሚያመጣ የተለየ ህግ እንዲቀርፁ ለማሳመን፣ ግልጽ ዓላማ ያለው የድርጊት መርሃ ግብር መቅረፅ ይጠይቃል።

ደስ የሚለው፣ ለተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የቀረበው አንድ ሪፖርት ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ ያለመ ነው። በቤተ ጉራማይሌ እና በ ዘ አድቮኬትስ ፎር ሂዩማን ራይትስ የተፃፈው፣ "የኢትዮጵያ ባለድርሻ አካላት ሪፓርት ለተባበሩት መንግስታት ዓለም አቀፍ ወቅታዊ ግምገማ" በባለፈው አመት ለኢትዮጵያ መንግስት ስምንት ምክረ ሀሳቦች ሰጥቷል።

ረፖርቱ ኢትዮጵያ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን ወንጀለኛ የሚያደርግ ህጓን እንድታስወግድ እና የኤልጂቢቲኪው+ ግለሰቦችን ከአድልዎ፣ ህጋዊ መሰረት የሌለው እስር፣ እንዲሁም በህግ አስከባሪዎች፣ በሃይማኖት መሪዎች እና በአመፀኛ ቡድኖች ከሚፈፀም በደል እንድትጠበቅ ያሳስባል። የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተጠያቂነትንም አካቶ በመያዝ፣ በህዝብ ትምህርት ቤት የሚሰጡ ዓሉታዊ ማጠልሽቶችን እንድትቀንስ እና በኤልጂቢቲኪው+ ጉዳዮች ላይ ለአገልግሎት ሰጪዎች ልዩ ስልጠና መስጠትን ይጠይቃል። በተጨማሪም ኤልጂቢቲኪው+ ግለሰቦችን በብሔራዊ የጤና ስልቶች ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጣቸው ቡድኖች አድርገው በመቀበል እቅዶቻቸው ላይ እንዲያካትቱ ይመክራል። በበይነ መረብም ሆነ ከበይነ መረብ ውጪ የሚደረጉ ጥቃቶችን ለመከላከል፣ የጥላቻ ንግግር ሕጎች ላይም ማሻሻያ እንዲደረግ ይመክራል።

ለእነዚህ የእርምጃ ጥሪዎች የኢትዮጵያ መንግስት ምን ምላሽ ሰጠ? ማንኛውም የፖለቲካ ወይም የዲፕሎማሲያዊ ባለስልጣናት ምክሮቹን አይተው አስተያየት የሰጡ ስለመሆናቸው እስካሁን ግልጽ አይደለም። ሆኖም ፋጤ ማንኛውንም ውጤት ለማግኘት እና መንግስትን ተተጠያቂ ለማድረግ ጉዳዩን ማጣራቱን ይቀጥላል። ከሁሉም በላይ፣ ይህ የእያንዳንዳችን የወደፊት ዕጣ ፈንታን የሚመለከት ጉዳይ ነው።

በኢትዮጵያ ያለው የኤልጂቢቲኪው+ መብት ትግል አሳሳቢ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ነው፤ ለይስሙላ የሚደረግ የአክቲቪዝም እንቅስቃሴ መሳሪያ ወይም ህሊናን ነፃ ለማድረግ ወይም ተከታዮችን እና ደጋፊዎችን በባዶ ማሰባሰብያ ዘዴ አይደለም። የሁሉንም ሰው የጋራ እርምጃ እና አጋርነትን የሚጠይቅ ነው። ፍቅር በጥላቻ እንደሚሸንፍ እና እያንዳንዱ ግለሰብ ደህንነቱ፣ ክብሩ ወይም ነፃነቱ ሳይጓደል እውነተኛ ህይወት መምራት እንዲችል፣ ከቀስተ ዳመና ጦር ጎን የምንቆምበት ጊዜ አሁን ነው። ካስማው ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍ ያለበት ጊዜ ነው።

የቀስተ ዳመናን ሰራዊት፣ ከፋጤ ጋር በመተባበር ወይም በመደገፍ ለመቀላቀል ለምትሹ፣ በኢሜል ይፃፉልን info@fattehmagazine.com.

Scroll to Top