ቡርኪና ፋሶ የተመሳሳይ ፆታ ፍቅር ግንኙነቶችን ወንጀል የሚያደርግ ሕግ አረቀቅች

በቡርኪና ፋሶ ዋና ከተማ ኦጋዱጉ የሚገኘው የብሔራዊ ጀግኖች ሐውልት

ወታደራዊቷ የምዕራብ አፍሪካዊት አገር መንግሥት የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን የሚከለክለውን የተሻሻለውን የቤተሰብ ሕግ ረቂቅ ስራ ላይ አዋለ።

በቤዛ ለዓለም 

ቡርኪናፋሶ በሐምሌ 9 የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ድርጊቶችን ማገዷን አስታውቃለች። የሀገሪቱ የፍትህ ሚኒስትር ኤዳሶ ሮድሪግ ባያላ፣ በኤኤፍፒ የዜና ወኪል እንደተገለፀው "ከዚህ በኋላ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት እና ተያያዥ ተግባራት በህግ ያስቀጣሉ" ሲሉ ተደምጠዋል።

አዲሱ ህግ፣ የሰፊው የቡርኪና ፋሶ የጋብቻ ህጎች ማሻሻያ ክፍል ሲሆን ለሃይማኖታዊ እና ልማዳዊ ለሆኑ ጥምረቶች ብቻ እውቅና የሚሰጥ ነው። ይህ ህግ አሁንም በወታደራዊ ቁጥጥር ስር ባለው ፓርላማ እና በ2022 በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን በተቆጣጠሩት በጊዜያዊው ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ትራኦሬ መፅደቅ አለበት።  

እንደ አለማቀፉ የሌዝቢያን፣ ጌይ፣ ባይሴክሹዋል፣ ትራንስ እና ኢንተርሴክስ ማህበር (ኢልጋ)፣ ከ 54ቱ የአፍሪካ አገራት፣ ቡርኪናፋሶ፣ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ወንጀል ካልተደረገባቸው 22ቱ የአፍሪካ አገራት መካከል ነች። የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነቶች በማህበረሰቡ መካከል የተወገዙ እና የሚጠሉ ቢሆንም፣ በህግ የተከለከለ ሆኖ አያውቅም ሲል የ ከቢቢሲ ረፖርቱ.

የቡርኪና ፋሶ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ( ሲኤንዲኤች), Gonta Alida Henriette Da, ) ፕሬዚዳንት ጎንታ አሊዳ ሄንሪዬት ዳ፣ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን ሕገ ወጥ ማድረግ "የሰብዓዊ መብቶች ትልቁ ጥሰት እና በመቶ ሺዎች በሚቈጠሩ ሰዎች ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድር ነው" ብለዋል።

በቡርኪናፋሶ ከ23 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ይኖራሉ። እንደ ሰብዓዊ መብት ጥበቃዘገባ፣ "የሀገሪቱ የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ በ2024 በከፍተኛ ሁኔታ እያሽቆለቆለ ሄዷል፤ ምክንያቱም እስላማዊ ታጣቂ ቡድኖች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያደረሱት ገዳይ ጥቃት መበራከት የተነሳ እና ወታደራዊ ሃይሎች እና የመንግስት ደጋፊ ሚሊሻዎች ባደረጉት የፀረ-ሽምቅ ዘመቻዎች ለተጨማሪ በደል መፈፀም ምክንያት ሆነዋል።"

Scroll to Top