አንጎላውያን በኤልጂቢቲኪው መገናኛ ብዙኃን ላይ በተጋረጠው እገዳ ላይ ያላቸውን ስጋት አሰሙ

የትራንስ መብቶች ድርጅት ሙቪሜንቶ ኡ ሱ ትራንስ አንጎላ ሰንደቅ ዓላማ ምስል ከፌስቡክ ገፅ

ሀገር በቀል ተሟጋቾች የሆኑት ሙቪሜንቶ ኡ ሱ ትራንስ አንጎላ እና አይሪስ አንጎላ ማህበራት፣ ፀረ-ኤልጂቢቲኪው ተሟጋቾች የኤልጂቢቲኪው+ ሰዎችን "ለማግለል እና ለማጥፋት" እየተዘጋጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በቤዛ ለዓለም 

"የማህበራዊ እና ሃይማኖታዊ አክቲቪስቶች" ነን ብለው በሚጠሩ አሳቻ ቡድኖች "የኤልጂቢቲኪው ሰዎችን እይታ እና መረጃ የሚፈጥሩ ይዘቶች እና ማጣቀሻዎችን ከቲቪ እና ከኢንተርኔት ለማጥፋት የሚፈልግ ዘመቻ በአንጎላ እየተፋጠነ ነው" ሲሉ በአይሪስ አንጎላ ማኅበር የአስተዳደር እና የፋይናንስ ዳይሬክተር የሆኑት ሪሊኩያ ራያን በሰኔ ወር ከማንባኦንላይን.

"እነዚህ ቡድኖች ሚስጥራዊ ናቸው [ነገር ግን] ማንነታቸውን እየመረመርን እና ተገቢውን እርምጃ እየወሰድን እንገኛለን።” ሲሉ ራየን ተደምጠዋል። አክለውም "ይህ በግልፅ [በአንጎላ] ህግ ላይ ያስመዘገብነውን በተለይም የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን ከወንጀለኝነት ያስወገድንበትን ለውጥ ወደኋላ ለመመለስ የሚደረግ ጥረት ነው። ከህግ አንፃር ከታየም ተግባራቸው ህገ መንግስቱን ይቃወማል። ህጉ እኩልነትን፣ ሰብዓዊ ክብርን እና ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን የሚያረጋግጥ ዋስትና የሚሰጥ ነው።”

በየካቲት 2021 የአንጎላ ፕሬዝዳንት ጆአዎ ሉሬንኮ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን በማፅደቅ፣ ፆታዊ ተመርኮ ላይ የተመሰረተ አድልዎን የሚከለክለውንም የተሻሻለ ህግ ፈርመዋል።

የሙቪሜንቶ ኡ ሱ ትራንስ አንጎላ፣ የትራንስ መብቶች ድርጅት መስራች ኢማኒ ዳ ሲልቫ እንዳሉት፣ የኤልጂቢቲኪው ይዘት ያላቸውን መረጃዎች ማስወገድ በሃገሪቷ ውስጥ ቀድሞም እየተበደሉ ላሉ ትራንስ ሰዎችን ሁኔታዎች የሚያባብስ ነው። "ማህበረሰቡን የችግር መንስኤ እንደሆንን ለማሳመን የሚደረግ ጥረት ነው። ይህ ደግሞ ቀድሞም እኛን ለማግለል እና ለማጥፋት ለሚፈልጉ ማስተባበያ የሚፈጥር ነው።" ሲሉ ዳ ሲልቫ ከማንባኦንላይንበፓሊስ መኮንኖች፣ በመምህራን እና በጤና ባለሙውያዎች ምክንያት የሚደርሰውን መድልዎ እየጨመረ መምጣቱንም አክለው ገልፀዋል።

የሙቪሜንቶ ኡ ሱ ትራንስ አንጎላ፣ በድርጅቱ የ ፌስቡክ ገፅ ላይ ትራንስጀንደር አንጎላዊቷ ዘፋኝ ቲቲካ የተፃፈውን እና እየተባባሰ የመጣውን ጠላትነት የሚያጎላ ግልፅ ደብዳቤ በሰኔ ወር መጨረሻ አጋርቷል።  

"ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በኢንተርኔት ላይ እንደ አርቲስት፣ እንደ ሴት፣ እንደ ሰው በምንም መንገድ ማንነቴን የማይወክሉ ነገሮችን በማተም፣ የጥቃት፣ የአድማ እና የስም ማጥፋት ዒላማ ሆኛለሁ።" ሲል የቲቲካ ደብዳቤ ይነበባል።

ደብዳቤው ሲቀጥልም "እነዚህ ድርጊቶች እኔ በህዝብ ዘንድ ያለኝ ስም ለማጥፋት የተደረጉ ሙከራዎች ብቻ ሳይሆኑ፣ ብዙ ትራንስ ሴቶች በየእለቱ የሚያጋጥሟቸውን መዋቅራዊ ትራንስፎቢያ የሚያንፀባርቁ ናቸው። ይህ ህልውናችንን ለማፈን፣ ዋጋችንን እንድንጠራጠር እና ክብራችንን ለመሻር የሚሞከር የጥቃት አይነት ነው። እኔ ግን ዝም አልልም። ድምፄ ሁሌም የትግል፣ የባህል እና የለውጥ መሳሪያ ነው፤ መሆኑም ይቀጥላል። እኔ ቲቲካ ነኝ። ሴት ነኝ። ትራንስ ነኝ። እና አክብሮትን እጠይቃለሁ።"

በወቅቱ ተግባር ላይ የሚውሉ ፀረ-ኤልጂቢቲኪው ህጎች ቢኖሩም ቲቲካ እንዚህን እንቅፋቶች አሸንፋ፣ እ.ኤ.አ በ 2010 መግቢያ ላይ የ የኩዱሮ(የአንጎላ የሙዚቃ ዘውግ እና ተመሳሳይ ስም ያለው ዳንስ) ኮኮብ በመሆን ተወዳጅነትን አገኝታለች። እ.ኤ.አ በ 2012 ከ ከቢቢሲጋር ባደረገችው ቃለመጠይቅ አርቲስቷ ያለችበት ለመድረስ ያለፈቻቸውን ጥቃቶች ስትገልፅ፣ "በድንጋይ ተወግሪያለው፣ ተደብድቢያለው፣ በእኔ ላይ የተሰነዘሩ በርካታ ጭፍን ጥላቻዎችን አስተናግጃለሁ" ብላለች።

አንጎላ ውስጥ የኤልጂቢቲኪው ይዘት ያላቸውን ነገሮች ማገድ የኤልጂቢቲኪው ሰዎችን ከማገድ ጋር እኩል ነው፤ ይህም አገሪቱ በቅርብ ዓመታት ያደረገችውን እድገት ወደኋላ መመለስ ነው ሲሉ የደቡብ አፍሪካ የኤልጂቢቲኪው መብቶች ተሟጋች እና የ ዘ አዘር ፋውንዴሽን ተባባሪ ሊቀመንበር ሮዚ ሞቲኔ ጠቁመዋል። 

"ህልውናን ለማጥፋት ወይም ለማገድ የሚደረግ ማንኛውም ተግባር ከባድ ሁኔታን ይፈጥራል። ጥላቻን ህጋዊ ያደርጋል፣ ፅንፈኛ አመለካከቶችን ያጠነክራል፣ ለሆሞፎቢያ እና ለትራንስፎቢያ ህጋዊ እና ባህላዊ መሰረትን ይፈጥራል። ከባህል አንፃር ኩዊር እና ትራንስ ሰዎች ቦታ እንደሌላቸው፣ ህልውናቸው አሳፋሪ እና ወንጀለኛ እንደሆኑ መልዕክት ያስተላልፋል" ሲሉ ሞቲኔ ያብራራሉ።

እየጨመረ የመጣውን የፀረ-ኤልጂቢቲኪው ዘመቻዎች ማዕበል ለመዋጋት ከሌሎች አክቲቪስቶች ጋር በመቀላቅለ ክልላዊ ትብብር እንዲኖር ጥሪ ያቀረበችው ሞቲኔ፣ "የይምሰል አንድነት ድጋፍ” ብላ ከገለፀችው ነገር እንዲጠነቀቁም አሳስባለች።

"አንድ ቍልፍ ትምህርት የሉሶፎን፣ የፍራንኮፎን እና ሌሎች ብዙውን ጊዜ ወደ ጐን የተገለሉ ክልሎችን ያካተተ እውነተኛ፣ አስቸኳይ ፓን-አፍሪካዊ አንድነት አስፈላጊነት መሆኑ ነው። ይህ ማለት፣ የአንጎላን ነባራዊ ሁኔታ፣ ቋንቋ፣ የተለያዩ ህጋዊ መዋቅሮችን እና ተግዳሮቶችን መረዳት ማለት ነው" ብለዋል ሞቲኔ። 

"ጥበቃ የሌለው ታይታ በቂ አይደለም። የማህበረሰባችን ህጋዊ፣ ባህላዊ እና አካላዊ ጥበቃን ማረጋግጥ የሚችል አሰራር መገንባት አለብን።"

Scroll to Top