የአፍሪካ ቅንብር | ሊታወቁ የሚገባቸው የኤልጂቢቲኪው+ ዜናዎች ከሊሎንግዌ፣ ከራባት፣ ቡካቩ እና ባሻገር

በሊሎንግዌ፣ ማላዊ የሚገኘው የብሔራዊ ጦርነት መታሰቢያ ግንብ - ከፋጤ የአህጉሪቱ ካራታ ጋር።

የፋጤ ወርሃዊ የኤልጂቢቲኪው+ ዜና ቅንብር፣ ከአህጉሪቱ አገራት ቱኒዚያዎቹን እስረኞች፣ የጋናን ዩኒቨርስቲዎች፣ የቦትስዋናን የኩራት ቀን ዝግቶችን እና ከከኬንያ፣ ከዩጋንዳ እና ከናይጄርያ የተገኙ ታሪኮችን ይዟል።

በቤዛ ለዓለም 

ህዳር በመላው አፍሪካ ላሉ ኤልጂቢቲኪው+ ማህበረሰቦች ከባድ ወር ነበር። በአንዳንድ ሀገራት ያሉ የፖለቲካ መሪዎች የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ መሆንን ወንጀል አድርገው ያፀደቁበት፣ ሌሎች ደግሞ ከባድ ቅጣትን ለመጣል ቃል የገቡበት አስቸጋሪ ወር ሆኖ አልፏል። የትራንስ ጤና ክሊኒኮች፣ በዓለም ዓቀፍ የዓለም አቀፍ ድጋፍ መቋረጥ ምክንያት የመዘጋታቸው ዜና በተለይም፣ የትራንስጀንደር መታሰብያ (የትራንስጀንደር ዴይ ኦፍ ሪመንበራስ) ቀንን ባከበርንበት ወር መከሰቱ ተስፋ አስቆራጭ ነበር።

ነገር ግን፣ የባህር ማዶ የህግ ድጋፍ ዘመቻዎች የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ወንዶች ከእስር ቤት እንዲፈቱ ያበረከቱት አስተዋፅዎች እና የኩራት ቀን ዝግጅቶች ባልተጠበቁ ቦታዎች መካሄዳቸው፣ የተስተዋሉበት ጥቂት ብሩህ ቦታዎችም ነበሩ። ታዋቂዋ የዩጋንዳ አጋር ዊኒቢያኒማ፣ ዓለም ዓቀፋዊ መድረክዋን ተጠቅማ ማህበረሰቡን እንደምትደግፍ ስታረጋግጥ መስማት ልብን በሃሴት የሞላ አስደሳች ጊዜ ነበር። የዓለም ጤና ጉባኤን ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት የዩኤንኤድስ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር፣ የኤልጂቢቲኪው ሰዎች ጤና ሊጠበቅ የሚችለው መብታቸው ሲጠበቅ ብቻ ነው ሲሉ አቋማቸውን በድጋሚ አስታውቀዋል።

በዚህ ወር በጆሃንስበርግ ውስጥ ጉልህ የሆነ ስብሰባ ተካሂዷል፤ ከአህጉሪቱ እና ከሀገር ውጭ ያሉ የኤልጂቢቲኪው አክቲቪስቶችን፣ ድርጅቶችን እና አጋሮችን ያሰባሰበው ነበር ሰባተኛው የፓን አፍሪካ ኢልጋ ክልላዊ ኮንፈረንስ። ፋጤ በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው ዝግጅት ላይ መገኘት ባይችልም፣ ከፓን አፍሪካ ኢልጋ መሪ ጋር ቃለ ምልልስ ለማድረግ ጠይቀናል። ማንኛውንም እድገት ወይም ውጤት ለእርስዎ እንድንዘግብ እንዲረዳን፣ ጥያቄያችንን እንደሚያስተናግዱ ተስፋ እናደርጋለን።

በመላው አፍሪካ የኤልጂቢቲኪው ሰዎችን የሚነኩ እና በህዳር ወር የወጡ አንዳንድ ጠቃሚ ታሪኮች አርዕስተ ዜናዎቻችን እነሆ።

የማላዊ መንግስት ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪነትን ህገወጥ ለማድረግ ማቀዱን ተከትሎ የተነሳውን የይገባኛል ጥያቄን ውድቅ አደረገ

የጋና ፕሬዝደንት ኤልጂቢቲኪው ሰዎችን እና አጋሮቻቸውን ህገወጥ የሚያደርግ ህግ ለመፈረም ቃል ገብተዋል

የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪውን ናይጄሪያዊ እስረኛ በ‘ፕሮጀክት ናት አሎን’ የህግ እርዳታ ድጋፍ ነፃ ወቷል

የደቡብ አፍሪካ ትራንስጀንደር ክሊኒክ የዩኤስኤአይዲ የገንዘብ ድጋፍ ከተቋረጠ በኋላ ተዘግቷል

አስር ኤልጂቢቲኪው ካሜሩናውያን ከታሰሩ እና ማስለቀቂያ ከተጠየቁ በኋላ ተለቀቁ

የዩጋንዳ ሊቀጳጳስ የዓለማቀፉን አንግሊካን ቤተ ክርስቲያን ኤልጂቢቲኪው ደጋፊ መሪን ተቃወሙ

ኤልጂቢቲኪው ሰዎች በማዳጋስካር ስለሚደረስው መገለል በድህረገፅ ላይ ተናግረዋል

የመጀመሪያው ኩራት የቀደም የቦትስዋና ዝግጅት ተነሳሽነት በፓላፓይ ጋቦሮኔ ተካሂዷል

የኮንጎ ኤልጂቢቲኪው አክቲቪስት በሬዲዮ ከተናገሩ በኋላ ጥቃት እና ዘረፋ ደረሰባቸው

የቱኒዚያ ፀረ-ኤልጂቢቲኪው ጭፍጨፋ ከ70 በመቶ በላይ እስራት በማስከተል ጨመሯል

የተራቡ ኤልጂቢቲኪው+ ስደተኞች የዓለም አቀፍ ረድኤት መቆራረጥን ተከትሎ ከኬንያ ካምፕ ሸሹ

ኬፕ ታውን ፕራይድ የ 2026 ን የኩራት ቀን ጭብጥን እና በደቡብ አፍሪካ የሚከበረበትን ቀን ይፋ አድርጓል

የዲኤንቢ ታሪኮች ናይጄሪያዊ ደራሲ ሃይማኖታዊ 'የለውጥ ሕክምና' ልምዱን ገለጠ

የጋና ዩኒቨርሲቲ የኤልጂቢቲኪው እንቅስቃሴዎችን መፍቀዱን ካደ፣ ይቅርታ እንደሚሻም አስታውቋል

ዩኤስአይዲ ድጋፍ መቋረጥ ኤልጂቢቲአይኪው ሰዎች የሚገለገሉባቸውን የማላዊ ጤና እንክብካቤ ክሊኒኮች በግዳጅ እንዲዘጉ ምክንያት ሆኗል

ፋሚሊ ዎች የተባለ የዩኤስ አክቲቪስት ፀረ-ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ቡድን በዩጋንዳ ህግ ውስጥ ያለውን ሚና ውድቅ አደረገ

ግሎባል ቅንጅት (ግሎባል ኳልሽን) በስድብ ወንጀል በእስር የምትገኘውን የሞሮኮ አክቲቪስት እንድትፈታ ጠየቀ

የደቡብ አፍሪካ ኤልጂቢቲኪው ሙስሊም ቡድን በተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪው ኢማም ግድያ ላይ የፖሊስ ዝምታን ነቅፏል

Scroll to Top