በአዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ ወሳኝ ገፅታዎች አነሳሽነት በ ኤአይ እገዛ የተሰራ፣ ከፋጤ የአህጉሪቱ ካርታ ጋር።
የፋጤ ወርሃዊ የኤልጂቢቲኪው+ ዜና ከአህጉሪቱ የናይጄሪያ ፊልም ባለሙያዎችን፣ ዩጋንዳዊዎቹን ተማሪዎች፣ ግብፃውያኑን የእግር ኳስ አንጋፋ አለቆችን እና ከናሚቢያ፣ ቡርኪና ፋሶ እና ደቡብ አፍሪካ የተገኙ ታሪኮችን ይዟል።
በቤዛ ለዓለም
ከሁሉም በላይ በመጀመሪያ፣ በ 2026 መልካሙን ሁሉ እንመኝልዎታለን። ወደ አዲሱ ዓመት ባመራን ወር፣ ኤልጂቢቲኪው+ አፍሪካውያን እራሳቸውን በመሆናቸው ብቻ፣ ያለአንዳች ሌላ ምክንያት ዓይን ውስጥ ገብተዋል። ምንም እንኳን አሳዛኝ ዘገባዎች አርእስተ ዜናዎችን ተቆጣጥረው የነበረ ቢሆንም፣ በታህሳስ ወር የናይጄሪያ ፊልም ባለሙያዎች ስለ የተመሳሳይ ፆታ ፍቅር የሰሩት ዘጋቢ ፊልም፣ ዓለም አቀፋዊ መድረክ ያገኘበት ወር በመሆን ብሩህ ታሪክ የተመዘገበበት ወርም ነበረ።
ፋጤ፤ ኢትዮጵያውያን ኤልጂቢቲኪው+ ማህበረሰብ በወሳኝ ጉዳዮች ላይ መደበኛ ውይይት ለማድረግ የሚረዳ መድረክ በቲክቶክ የቀጥታ ስርጭት ለተከታዮቹ ማቅረብ የጀመረው በዚህ ወር ነበር። በርካቶችን ጭንቀት ውስጥ ካስገቧቸው ርዕሰ ጉዳዮች አንዱ የታዋቂው ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ ሶፎንያስ ዋሲሁን በማህበራዊ ድህረ ገጾች የተሰራጨው ታሪክ ነበር። ጉዳዩ፣ በተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪነት ተጠርጥሮ በውሽት ወጥመድ ታፍኖ የተያዘበት፣ የተደበደበበት እና የተዋረደበት ብሎም ድርጊቱ ተቅርፆ በማህበረአዊ ገፆች ላይ ተሰራጭቶ ነብር። በሀገሪቱ ታዋቂ ከሆኑ የቴሌቭዥን አዘጋጆች አንዱ የሆነው ሶፎንያስ ዋሲሁን፣ በዚህ መልኩ ሊጠቃ ይችላል የሚለው ሀሳብ ተራው ኢትዮጵያዊ ሊገጥመው የሚችለውን አስከፊ ጥቃት አመላካች ነው። ከዚህም በላይ “የቪድዮ ምስሉ በኤልጂቢቲኪው+ ኢትዮጵያውያን ላይ አገር አቀፍ ይዝት ያለው የጥላቻ ንግግር እና ዛቻ እንደገና እንዲቀሰቀስ አድርጓል” ሲል የተሟጋች ቡድኑ ቤተ ጉራማይሌ ዘግቧል።
ከሁለት ሳምንት በፊት በኢትዮጵያ ማህበራዊ ሚዲያ የፈጠራ ሽልማት ስነስርዓት ላይ የተገኙት ስድስት ቲክቶክ ፈጣሪዎች “ያልተገባ ልብስ” ለብሰዋል በሚል መታሰራቸው ሌላው አሳሳቢ ጉዳይ ነበር። በቢቢሲ ወርልድ ሰርቪስ ቃለ ምልልስ ያደረገው ኢትዮጵያዊው የቢቢሲ ጋዜጠኛ ቃልኪዳን ይበልጣልእንደሚለው፣ አንዳንድ እስራቶች የተቀሰቀሱት በወግ አጥባቂዎች ፋሽን ምርጫቸው ወደ “አደገኛ ክልል” የገቡትን እንዲቀጡ ለመጠየቅ ነው። "ለማለት የፈለጉትም [እንደ ‘ወንዶች ቦርሳ' እና ሌሎች መገለጫዎች ያሉ ያልተለመዱ አልባሳት] ኩዊር ወይም የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ አድረጎ እንደሚያስፈረጅ እና ይህም [በኢትዮጵያ] ከህግ ውጪ እንደሆነ ነው" ብሏል።
ታህሳስ በተጨማሪም ዓለም አቀፉ የኤልጂቢቲኪው+ ማህበረሰብ ሶስት በዓላትን፦ የዓለም የኤድስ ቀን፣የሰብዓዊ መብት ቀን እና የዓለም ዓቀፍ ስደተኞች ቀን በማክበር ሰፊውን ዓለም የሚቀላቀልበትም ጊዜ ነው። መሰረቱን በካናዳ ያደረገው ሬንቦ ሬልሮድ እና መቀመጫውን በዩናይትድ ኪንግደም ያደረገው ድርጅት የአፍሪካ ሬንቦው ፋሚሊ ዓለም ዓቀፉን ማህበረሰብ፣ ከኤልጂቢቲኪው+ ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ጋር በመተባበር አጋርነት መቆም እንደሚያስፈልግ እንዲያስታውሱ ረድቷቸዋል።
የተባበሩት መንግስታት የኤችአይቪ/ኤድስ ፕሮግራም ዩኤንኤድስ የአፍሪካ መሪዎችን “ኤችአይቪን ለመከላከልና ለማጥፋት የሚደረገውን ዘመቻ እንዲደግፉ፣ ሰብዓዊ መብቶችን እንዲጠብቁ እና ኤድስን ለማስወገድ አዳዲስ የፈጠራ እድሎችን እንዲጠቀሙ” ጥሪ በማድረግ ሌሎች ሁለት ዝግጅቶችን አድርጓል። በሰብዓዊ መብቶች ቀን ድርጅቱ “ዓለም አቀፉ የኤችአይቪ ምላሽ በአስርት ዓመታት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ እጅግ በጣም ፈታኝ ጊዜ እየገጠመው ነው” ብሏል።
ድርጅቱ "የፖለቲካ አመራር፣ መዋቅራዊ መከፋፈልንና ልዩነትን የሚደርሱ ፖሊሲዎችን ለማራመድ እና ለአደጋ ተጋላጭ ህዝቦችን ለመጠበቅ"፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ፣ የጤና አጠባበቅ ተደራሽነት ላይ ያልተመጣጠነ እንቅፋት የሚያጋጥማቸው "ኤልጂቢቲኪው+ ሰዎች የጤና ሽፋን እንዲኖራቸው" መሆኑን ልዩ ማስታወሻ ሰጥቷል። ቃል አቀባዩ ማህበረሰቦችን ከኤችአይቪ አገልግሎቶች ለመገለላቸው መቀጠል “የቅጣት ህጎች፣ አድልዎንና መገለልን” ተጠያቂ አድርገዋል ።
በመላው አፍሪካ የኤልጂቢቲኪው ሰዎችን የሚነኩ እና በታህሳስ ወር የወጡ አንዳንድ ጠቃሚ ታሪኮች አርዕስተ ዜናዎቻችን እነሆ።
በተመሳሳይ ፆታ ዋትሳፕ ቡድን ውስጥ ያሉ አስር ወንዶች በሴኔጋል 'ተፈጥሯዊ ባልሆኑ ድርጊቶች' በሚል ታስረዋል
የናይጄሪያው የኤልጂቢቲኪው+ ዘጋቢ ፊልም አዘጋጅ ዓለም አቀፍ የስርጭት መድረክን አገኘ
በዩጋንዳ ዩኒቨርስቲ ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ጠል ህገወጥ የግድያ እንቅስቃሴ ሲመራ የነበረን ተማሪ አገደ
በኢትዮጵያ ኤልጂቢቲኪው+ ማህበረሰብ ላይ የተቀናጀ ጥቃት ተባብሷል
ቡርኪና ፋሶ ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪነትን በወንጀል ከፈረጀች በኋላ የመጀመሪያ ክስ አስመዝግባለች
የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ በተመሳሳይ ፆታ ወንድ አፍቃሪው ግድያ ተያይዞ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ጠል ተነሳሽነት እንዳለበት ጠየቀ
በተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪነትን ወንጀል ክስ ተያይዞ አምስት ወንዶች በሴኔጋል ከፋሽን ትርኢት ቀደም ብሎ ታስረዋል
የዩጋንዳ ኤልጂቢቲኪው+ ተሟጋቾች በሰብዓዊ መብት ቀን እየጨመረ ያለውን የመብት ጥሰት አውግዘዋል
ናሚቢያ እና ግብፅ ኤልጂቢቲኪው ከተባበሩት መንግስታት የአካል ጉዳተኝነት መብቶች ድምጽ ውስጥ እንዲወጣ ድጋፍ ሰጥተዋል
ግብፅ በአሜሪካ የእግር ኳስ ግጥሚያ ላይ የሚደረጉ የኩራት በዓላት እንዲሰረዙ ጠየቀች
ሃይማኖታዊ ኤልጂቢቲኪው+ ዩጋንዳውያን የራሳቸውን ኦንላይን እምነት ማህበረሰባትን መሰርቱ

