የአፍሪካ ቅንብር | ሊታወቁ የሚገባቸው ኤልጂቢቲኪው+ ዜናዎች ከአክራ፣ ባንጁኢ፣ ኪንሻሳ እና ባሻገር

በአክራ፣ ጋና የሚገኘው የኩዋሜ ንክሩማ መታሰቢያ ፓርክ - ከፋጤ የአህጉሪቱ ካራታ ጋር።

የፋጤ ወርሃዊ የኤልጂቢቲኪው+ ዜና ቅንብር፣ ከአህጉሪቱ አገራት ሙዚቃ አቀንቃኙን ከኮትዴቯር፣ ናይጄሪያዊዉን አገረ ገዥ፣ ኢትዮጵያዊያኑን ጥገኝነት ጠያቂዎች እና ከማላዊ፣ ከሞሮኮ፣ ከጋና፣ ከቤኒን፣ ከካሜሮን እና ከኢኳቶሪያል ጊኒ የተገኙ ታሪኮችን ይዟል።

በቤዛ ለዓለም 

ይህ ወር በአህጉሪቱ ላሉ ኤልጂቢቲኪው+ ማህበረሰቦች የተለያዩ ክስተቶችን ያተስተናገዱበት ሌላ ወር ነበር። አሳዛኝ ዜናዎች እና አሳሳቢ ለውጦቶች፣ በተራ ሰዎች ቆራጥነት እና ብልሃተኛነት ሚዛን መጠበቅ የተቻለበት ጊዜም ነበር።

የፋጤ ቡርኪና ፋሶ የተመሳሳይ ፆታ ፍቅር ግንኙነቶችን ወንጀል በማድረግ ከ30 በላይ የአፍሪካ አገራትን ለመቀላቀል የወሰደችውን እርምጃ ዘግቧል። በሌላ ቦታ፣ የስልጣን ኮሪደሮች በተለመደው የጠላት ሃይሎች ተሞልተው የነበር ቢሆንም፣ ጥቂት የተስፋ ጭላንጭሎችም ነበሩ። በመስከረም ወር፣ በአህጉሪቱ ባሉ የኤልጂቢቲኪው+ ሰዎች ላይ ተፅዕኖ ያሳድሩ ሌሎች ጠቃሚ ታሪኮችም ነበሩ። ፋጤ የነዚህን ዝጋቤዎች አርዕስተ ዜና ቅንብር እነሆ ይላል።

ፖለቲከኞች የተመሳሳይ ፆታ ፍቅር ግንኙነቶችን በጋና ብሔራዊ ምርጫ ላይ እንደ መሳሪያ መጠቀማቸው ተዘግቧል

ቤኒን የፀረ-ኤልጂቢቲኪው ጥቃት ፈጻሚዎችን ለፍርድ ለማቅረብ ተንቀሳቅሳለች ተብሏል

ኢትዮጵያዊው ጥገኝነት ጠያቂ ኤልጂቢቲኪው ዘመቻን ተከትሎ ከማልታ እስር ነፃ ወጥቷል

የሶዌቶ ኩራት በታላቅ ሰልፍ 21ኛ ዓመቱን በደቡብ አፍሪካ አክብሯል

ግብፅ በሴቶች እና በኤልጂቢቲኪው ጉዳዮች ላይ 'ግብረ-ገብ የጎደለው' ዕይታ ዓላቸው ያለቻቸውን ቲክቶከሮችን አሰረች

የፖሊስ መኮንን እና የአጎት ልጅ በደቡብ አፍሪካዊቷ ሌዝቢያን አክቲቪስት ግድያ ተከሰሱ

ሞሮኳዊት አክቲቪስት 'አላህ ሌዝቢያን ነው' ብለሽ ተሳድበሻል በሚል ለ 30 ወራት ታሰረች

ማዕከላዊቷ አፍሪካ ሪፐብሊክ የፈረንሳይ ኤምባሲን 'የኤልጂቢቲ መብቶችን እያስተዋወቀ ነው' በሚል ከሳለች

ትራንስጀንደር እስረኛ በፆታ ማንነቷ ምክንያት በደረሰባት መድልዎ የደቡብ አፍሪካን እስር ቤት ከሳለች

ተመሳሳይ ፆታ ፍቅር ግንኙነቶችን ወንጀል መሆንን ተከትሎ በቡርኪናፋሶ የሚኖሩ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎች የአድኖ ጥቃት ሰለባ እንዳይሆኑ ሰግተዋል

ትራንስ ካሜሩናውያን ለሆርሞን ምትክ ሕክምና ለማግኘት ከመደባኛው መንገድ ውጪ እየሄዱ ነው

በስፔን የሚኖሩ ኢኳቶሪያል ጊኒያውያን የኤልጂቢቲኪው አክቲቪስቶች ከሃግር ቤት የሚመጡ ስጋቶችን እየተታገሉ ነው

የኮትዲቯሯ ሮዛሊን ላዮ ኮንሰርቶች በሆሞፎቢያ ምክንያት በፈረንሳይ ተሰረዙ

የናይጄሪያ ካኖ ግዛት አስተዳዳሪ የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻን የሚከለክል ረቂቅ አፀደቀ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ግጭት ሴቶችን እና ኤልጂቢቲኪው ሰዎችን እንደደፈሩ አረጋገጠ

የጋዛ ፍሎቲላ አስተባባሪ በቱኒዚያው የኤልጂቢቲኪው አክቲቪስት ተሳትፎ ምክንያት ስራ ለቀቁ

የአሜሪካ የገንዘብ ድጋፍ መቋረጥ በማላዊ በተከበበው የስደተኞች ካምፕ ውስጥ ያሉ የኤልጂቢቲኪው ክሊኒኮችን አቆርቁዟል

Scroll to Top