የአፍሪካ ቅንብር | ወቅታዊ የኤልጂቢቲኪው+ ዜና ከካምፓላ እስከ ካኩማ እና ባሻገር

በካምፓላ መልካምድር እና በዩጋንዳ ምስሎች ላይ ተመስርቶ፣ በፋጤ የአህጉሪቱ ካርታ ጋር በሰው ሰራሽ አስተዉሎት የተሰራ

ሊነበቡ የሚገባቸው የፋጤ ወርሃዊ የኤልጂቢቲኪው+ ዜና ጥንቅር፣ የናይጄሪያ ክለብ ልጆችን፣ የደቡብ አፍሪካ ሰባኪዎችን፣ ጋቦናውያኑን ዘፋኞችንና ከግብፅ፣ ጋና እና ሴኔጋል የተውጣጡ ታሪኮችን ይዳስሳል።

በቤዛ ለዓለም 

ዓለም አዲሱን ዓመት ሲያስተናግድ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኤልጂቢቲኪው+ አፍሪካዊያን የአዲሱን ዓመት መግብያ በራሳቸው መንገድ አስተናግደዋል። ጥር ወር፣ ለኢትዮጵያውያንና ለኤርትራውያን እንደ ገና/ልደት እና ጥምቀት ያሉ በየዓመቱ በድምቀት የሚከበሩ በዓላት ወር ቢሆንም፣ ለአንዳንድ ኤልጂቢቲኪው ሰዎች ግን እነዚህ በዓላት የተወሳሰቡ ናቸው። በአህጉሩ ውስጥ ማኅበረሰቡን የሚያጋጥሙ የተለመዱ ችግሮች እንደገና ብቅ በማለታቸው፣ የበዓላቱ የደስታ ድባብ ባአጭር እንዲቀጭ አስገድዷል።

ከጋና እስከ ዩጋንዳ እንዲሁም ከግብፅ እስክ ሴኔጋል ድረስ፣ ዓርዕስተ ዜናዎች የተምሉት በቅርብ በምናውቃቸው የጭቆና እና የጥቃት ታሪኮች ነበሩ። በጥር ወር የአፍሪካ የሰብዓዊ መብቶች ጥምረት በኤልጂቢ ሴቶች ላይ፣ በቤተሰቦቻቸው እና በማህበረሰባቸው ውስጥ እንዲሁም በታሰሩባቸው ወይም በተፈናቀሉባቸው አስቸጋሪ አካባቢዎች ላይ የተስፋፋውን ጥቃት አጉልቶ አሳይቷል። ነገር ግን ጥቂት የተስተዋሉ የተስፋ ምልክቶችም ነበሩ፤ በተለይም ኬንያ ውስጥ በኪነጥበብ ዘርፍ የኤልጂቢቲኪው ውክልና ማግኘትን ጨምሮ፣ የአንድ ሙዚቀኛ የጋቦን ተሞክሮ ያካተቱ ተስፋ የሚሰጡ ክስቶችም ነበሩ። 

ፋጤ ከእነዚህ ተቃውሞዎች ባሻገር፣ በያለንበት አንድነት እና መደጋገፍ ምን እንደሚመስል የሚዳስስ የቲክቶክ ቀጥታ ስርጭት ፕሮግራሙን አጠናክሮ ማዘጋጀቱን ቀጥሏል። በሁለት ሳምንት አንዴ የሚቀርበው ይህ የቀጥታ ስርጭት አብዛኛውን ጊዜ ለተገለሉ ኢትዮጵያውያን ኤልጂቢቲኪው ማህበረሰብ ደህንነቱ የተጠበቀ የመወያያ ቦታን ለማቅረብ እየተጋ ይገኛል። በእኔ አዘጋጅነት ሀገሪቱ የስራ ቋንቋ በሆነው አማርኛ የማቀርብላችሁ፣ ‘ስለ ህግ’ (ህግን እና የደህንነት ስጋቶችን ማስተዋል) እና ‘ስነ ጤና’ (የአካል፣ የአዕምሮ፣ የወሲብ ጤና) የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በማተኮር የሚያደርግ ውይይት ነው።

ባለፈው ጥር ዝግጅታችን፣ የኤልጂቢቲኪው ሰዎች ህልውናቸው በራሱ ሕገ-ወጥ በሆነበት አገር ውስጥ ራሳቸውን ለመጠበቅ ሊወስዷቸው የሚገቧቸውን ተግባራዊ እና ንቁ እርምጃዎች ላይ ተወያይተናል። ማህበራዊ መድረኮቻችን ላይ 'መላ በሉኝ' የተሰኘ፣ ከእናንተ የሚላኩ ስም አልባ ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጥበት አዲስ አገልገሎትም ጀምረናል። ፍቅር፣ ደህንነት፣ ቤተሰብ፣ እምነት፣ ስራ እና ሌሎች ርዕሶችን የሚሸፍን ልዩ መድረክ በመክፈት ወሩን አገባደናል። ትኩረት የሚሹ አጣብቂኝ ሁኔታ አጋጥሞታል? ጥያቄዎትን በ info@fattehmagazine.com ወይም በማህበራዊ ገፆቻችን መልዕክት ላኩልን።

ውይይቱን ለመቅረጽ ካደረግነው መጠነኛ ጥረት ባሻገር፣ ከመላው አፍሪካ የመጡ ሪፖርቶች ብዙ መሰናክሎችንና የመቋቋም ችሎታን የሚያንፀባርቁ ሆነው አግኝተናቸዋል። በጥር ወር በአህጉሩ የኤልጂቢቲኪው ሰዎች ላይ ተፅዕኖ ያሳደሩ ታሪኮች አርዕስተ ዜና እነሆ።

ዪጋንዳ ምርጫ ከመካሄዱ አስቀድማ የኤልጂቢቲኪው እና የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ላይ እገዳ አድርጋለች

የኬንያ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ‘ራፊኪ’ የተሰኘ የተመሳሳይ ፆታ ሴት አፍቃሪ ላይ የተመረኮዘ ፊልም እገዳ ጥያቄን ውድቅ አደረገ

የአልቴ ክለብ ባህል ላይ ተጽዕኖ ያሳደሩ ናይጄሪያዊ የኤልጂቢቲኪው ግለሰቦች አሁን ላይ እየተገለሉ ነው

የግብጽ ፖሊሶች የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ወንዶችን በሥነ ምግባር ብልሹነት እና ብልግና ስም ለማጥመድ የመጠናኛ መተግበሪያዎችን እየተጠቀሙ ነው።

በሴኔጋል በ'ኢተፈጥሮዓዊ ድርጊት' አሥራ አንድ ሰዎች የተፈረደባቸው ሲሆን፣ ሌሎች አሥራ አንድ ሰዎች የፍርድ ቤት ቀጠሮ እየጠበቍ ነዉ

የኤልጂቢቲኪው ጥገኝነት ጠያቂዎች ከኬንያ የስደተኞች ካምፕ ማሻሻያ እንዳይገለሉ ስጋት ላይ ናቸው

ከ90% በላይ የሚሆኑት የተማሩ ኤልጂቢቲኪው ናይጄራዊያን ባለሙያዎች ለመሰደድ አቅደዋል

የጋና ትምህርት ሚኒስቴር ኤልጂቢቲኪው የሚጠቅስ የማስተማሪያ መጽሃፍ እንዲመለስ አዘዘ

ባይሴክሿሉ ዘፋኝ ጃን ሀሌክሳንደር ወደ ጋቦን የመመለስ ጕዞውን ዘግቧል

የደቡብ አፍሪካው የሃይማኖት መሪ በለውጥ ሕክምና ቪዲዮ ላይ አንድ ታዳጊን አዋረደ

የጋና ተቃዋሚ የፓርላማ አባል በፀረ-ኤልጂቢቲኪው ህግ ላይ የመንግስትን ዝምታ ነቀፈ

የዪጋንዳ ፀረ-ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ህግ ኤችአይቪን የመከላከል ጥረቶችን እያደናቀፈ ነው

Scroll to Top