የአፍሪካ ቀንድ አገራት ኤልጂቢቲኪው+ ማህበረሰብ ኩራትን በቪየና አከበሩ 

የ2025 የአፍሪካ ቀንድ ኩራትን አስመልክቶ በኢትዮጵያ የስራ ቋንቋ በአማርኛ፣ “የማፍቀር ነፃነትን ማክበር” በሚል መሪ ቃል የተለጠፈ ማስታወቅያ ምስል። ምስል ከቤተ ጉራማይሌ።

ታዳሚዎች፣ ከአፍሪካ ቀንድ ገራት ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሶማሊያ እና ጅቡቲ እንዲሁም ዓለም ዓቀፍ ዳያስፖራዎች የራሳቸውን ልዩ የኩራት በዓል ለማክበር በኦስትሪያ መዲና ተሰባሰቡ!

በቤዛ ለዓለም

ይህ ሁሉ የተሰነፀው፣ እንደ እ.ኤ.አ በ2020ዓ.ም፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ኤልጂቢቲኪው+ ሰዎች በቨርቷል ቴክኖሎጂ ድጋፍ አማካኝነት የአፍሪካ ቀንድ አገራት ኩራትን ለማክበር ሲቀላቀሉ ነበር። ከዚህ ወሳኝ የኦንላይን ስብሰባ አምስት ዓመታት ቆይታ በኋላ፣ የአፍሪካ ቀንድ አገራት የኩራት በዓልን፣ ለመጀመርያ ጊዜ በአካል ከሰኔ 12-15፣ 201 የሙዚቃ ከተማ ተብላ በምትጠራው በቪዬና በደምቀት ተከብሯል። በቤተ ጉራማይሌ_የተሰናዳው ይህ አስደናቂ ዝግጅት፤ ከተለያዩ የአፍሪካ ቀንድ አገራት ከኢትዮጵያ፣ ከኤርትራ፣ ከሶማሊያ፣ ከጅቡቲ እንዲሁም ከእነዚህ ገራት ትስስር ያላቸውን ሰዎች ያስጎረፈ ነበር።

አንዳንዶች ከአፍሪካ አህጉር ሌሎች ደግሞ ከአሜሪካ፣ ከእንግሊዝ፣ ከፈረንሳይ፣ ከስዊድን፣ ከጀርመን እና ከኖርዌይ ድረስ በመብረር፣ ከቅርብ እና ከሩቅ በርካታ ታዳሚዎች ወደ ኦስትሪያ ዋና ከተማ ጎርፈዋል። በመረሻቸው ቪየናም፣ ይህ ብዝሃነተን የተላበሰ ነገር ግን አስደናቂ ማህበረስብ "የማፍቀር ነፃነትን እናክብር" በሚል መርህ በአንድነት ለአራት ቀን በቆየው በዓል ላይ ተሳትፈዋል። 

ፎቶዎች፡ ቤተ ጉራማይሌ

በስብስቡ ላይ የተገኙ እንግዶች፣ በአፍሪካ ቀንድ አገራት ላሉ የኤልጂቢቲኪው+ ሰዎች፣ ደስታ አንዱ የተቃውሞ እርምጃ መሆኑን እንዲያስታውሱ እና ከዚህ ልዩ በዓል ጀርባ ያለውን ተነሳሽነት እንዳይዘነጉ ተበረታተዋል። 

"ዓላማችን ህልውናችንን ማሳየት ነው። በማህበረሰባችን ውስጥ ደስታን በመፍጠር፣ እርስ በእርሳችን እና ከእኛ ጋር በአካል ለሌሉት ጭምር 'አለን፣ ነበርን፣ እንኖራለን" የሚልም ይቅርታ የማያስጠይቅ መግለጫችን ነው። ከተቃዋሚዎች ክርክር በልጠን እንኖራለን። ህልውናችን ለክርክር የሚቀርብ አይደለም። ተቀባይነት ለማግኘት አንሰራም። ለማንም ሳይሆን ለራሳችን አለን" ሲሉ ቤተ ጉራማይሌ የአፍሪካ ቀንድ ፕራይድ ድህረገጽ ላይ አስፍረዋል።.

የዚህን ዝግጅት አመጣጥ በተመለከተ የቤተ ጉራማይሌ ተባባሪ መስራች የሆኑት ፋሪስ ኩቺ ገዛኸኝ፣ የኖርዌይ ማህበረሰብ አባላት የጉዞ ቅርጸቱን ለማነሳሳት እንደረዷቸው ገልፀዋል።

"እ.ኤ.አ በ2024 በኦስሎ የሚገኘው ድንቅ [ኤልጂቢቲኪው+] ቤተሰቦቻችን፣ የኦስሎ ኩራትን እንድናከብር ጋብዘውን ነበር። በእነሱም አነሳሽነት፣ በገዛ ሀገራችን ኩራትን ማክበር እስክንችል፣ የአፍሪካ ቀንድ ኩራት በመላው ዓለም ጉዞ እንደሚያደርግ በደስታ እንገልፃለን።" ሲሉ ኩቺ በቪየናው የመክፈቻ ስነስርዓት ላይ ገልፀዋል። የቀጣዩ ዓመት ዝግጀትም በዴንማርክ ዋና ከተማ ኮፐንሃገን እንደሚካሄድም አሳውቀዋል።  

የኤልጂቢቲክው+ አአክቲቪስቶቹ ፋሪስ ኩቺ ገዛኸኝ (ግራ) እና ባህሩ ሸዋዬ (ቀኝ)።

የቤተ ጉራማይሌ ቤት መስራቾች ፋሪስ ኩቺ ገዛኸኝ (‘ኩቺ’) እና ባህሩ ሽዋዬ (‘ባሂ’) በግዞት ከመሰደዳቸው በፊት ተወልደው ያደጉት በኢትዮጵያ ሲሆን፣ በቅደም ተከተል በቪየና እና በለንደን የኤልጂቢቲኪው+ አክቲቪስት ናቸው።

አንድ ቀን የኵራት ዝግጅቶችን በአፍሪካ ቀንድ ሃገራት ለማካሄድ ቃል የገቡት ኩቺ፣ ማህበረሰቡ ብዙውን ጊዜ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ሊኖራቸው የሚገባውን የማይበገር ተስፈኝነት እና ቆራጥነት ተምሳሌት አስታውሰዋል።

"በእርግጠኝነት ሀገራችን ላይ እንደምናካሂደው ያለምንም ጥርጥር አምናለሁ" ያሉት ኩቺ፣ "ማህበረሰባችን እኛን የመውደድ አቅም እንዳለው አምናለሁ። [ለዚህ ማረጋገጫም] እኛ እራሳችንን መውደድ መቻላችን ነው። ተወልደን ያደግነው በተመሳሳይ [ቦታ]፣ አስተሳሰብ እና ሁናቴዎች ውስጥ ቢሆንም፣ እራሳችንን ለመውደድ መርጠናል" ሲሉ አክለዋል።

አዘጋጆቹ የአፍሪካ ቀንድ አገራት ኩራት በዓላትን በማዘጋጀት ግንኙነቶችን ስለመፍጠር ብቻ እንዳልሆነ አበክረው ገልፀዋል። ይህ በዓል፣ ችለው መገኘት በቻሉት ላይ ብቻ የሚያበቃ እንዳልሆነም አክለዋል። 

"ኩራት ሰልፍ ወይም ድግስ ብቻ አይደለም፤ እራስን ሆኖ አንድ ተጨማሪ ቀን የመኖር ዝምተኛ ተጋድሎ ነው። በግልፅ አደባባይ ላይ ሰልፍ ማድረግ ባትችልም ህልውናህ በራሱ ተቃውሞ ነው። ኩራት የአንተ ነው፤ በህልሞችህ ውስጥ እና በዙሪያህ ላሉ በምታሳየው እንክብካቤ ውስጥ የሚገኝ ነው። ጊዜው ሲደርስ ለአንተ በመካከላችን ስፍራ እንፈጥራለን፣ ምክንያቱም ከመካከላችን ማንም ወደኋላ የሚተው የለም" ሲሉ ባሂ ተናግረዋል።

በዝግጅቱ ላይ የታደሙ እንግዶች በፆታዊ ዝንባሌያቸው ወይም በፆታ ማንነታቸው የተነሳ፣ ዕለት ተዕለት የሚገጥማቸውን ስደት እና ከፍተኛ ችግር ተቋቁመው፣ በአፍሪካ ቀንድ ገር ለሚኖሩ የኤልጂቢቲኪው+ ማህበረሰቦችን ለአፍታ ቆም በማለት አስታውሰዋል።

"ኩዊርነት ብዙውን ጊዜ እንደ ባዕድ ከውጪ የመጣ የሞራል ስጋት ተደርጎ በሚታይበት ክልል፣ ይህ ክብረ በዓል ታሪካችንን የሚመልስ የወደፊት እጣፋንታችንንም የሚያጠነክር ነው። በህይወት ከመትረፍ ባሻገር፤ ሁሌም እንደኖርን፣ ብቻችንን እንዳልሆንን እና ደስተኛ መሆን እንደሚጋብን ያስታውሰናል። የአፍሪካ ቀንድ ኩራት ያልተወነጀልንበት፣ ዝም ያልተሰኘንበት፣ እንደ ረቂቅ ያልተቆጠርንበት፣ እንቁ እና የተቀደሰ ስፍራ ቀርፆልናል። እራሳችንን ለመሆን ንግግርና እና ማብራሪያ ሳንሰጥ የምንታይበት ስፍራ ነው።" ሲሉ ባሂ ተናግረዋል። 

ፎቶዎች፡ ቤዛ ለዓለም

ትኩረታቸውን በአካባቢያቸው ባለው ወዳጃዊ ስሜት እና ከተማዋ ላይ ወደ ተሰራጨው የወዳጅነት መንፈስ በማድረግ ታዳሚ እንግዶች፣ በከተማዋ የኩራት መንደር ራትሃስፕላዝ ሞቅ ያለ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ለበርካታ ዓመታት በአካል ያልተገናኙ ጓደኛሞች ሲገናኙ እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያ ብቻ የሚተዋወቁ ሰዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ሲገናኙ፣ ሲተቃቀፉ እና ሰላምታ ሲሰጣጡ መመልከት እጅግ ልብን የሚያሞቅ ክስተት ነበር። 

በቀጣዩ ቀን ቤተ ጉራማይሌ እንግዶችን በባህላዊ የኢትዮጵያ ምግቦች እና የቡና ስነ-ስርዓት አስተናግደዋል። ቀኑ ፍቅር እና በደስታ የተሞላ ሲሆን፣ ታዳሚዎች የልጅነት ትዝታ እና ሀገር ቤታቸውን የሚያስታውሱ ሙዚቃዎች እየሰሙ እና አብረው እየዘፈኑ አሳልፈዋል። ቀኑ በልዩ የሽክሸካ መርሃ ግብር ከመጠናቀቁ በፊት፣ ኩቺ የተዘጋጀውን ልዩ ኤግዚቢሽን መርቀው ከፍተዋል። 

በማግስቱ፣ ከአካባቢው ተሟጋች ቡድን _አፍሮ ሬይንቦ ኦስትሪያ_ጋር በመተባበር፣ ታዳሚዎች በቪዬና የኩራት ሰልፍ (ቪዬና ፕራይድ) ላይ ተሳትፈዋል። በሰልፉ ላይ የተለያዩ ጠንካራ መልዕክት ያዘሉ ቲሸርቶችን በመልበስ፣ የቀኑ ድምቀት የነበረውን የቀስተ ዳመና ባንዲራን እያውለበለቡ "አለን፣ ነበርን፣ እንኖራለን! " የሚለውን መፈክር፣ በኩራት፣ በአንድነት እና በልበሙሉነት አስተጋብተዋል።

ፎቶ፡ ቤተ ጉራማይሌ

ምንም እንኳ ዝግጅቱ የተካሄደው በአውሮፓ ቢሆንም፣ በአፍሪካ ላሉ ኤልጂቢቲኪው+ ማህበረሰቦች ያለው ፋይዳ ሊናቅ አይገባም ሲሉ፣ ባሂ ሃሳብ ሰጥተዋል። 

የአፍሪካ ቀንድ አገራት ኩራት፤ ምዕራባውያን ሳይኮርጅ፣ ነፃነትን መሰረቱ ያደረገ ንድፍ ነው። ኩዊርነት የባህል አንድ ክፍል እንጂ ስጋት እንዳልሆነ ያስተምረናል። የትውልድ አገሮቻችን እና አህጉራችን በአጠቃላይ፣ ለኩዊር ሰዎች ደህንነት እና ክብር መስጠት ማለት ባህልን ማጣት ማለት እንዳልሆነ፣ ነገር ግን የባህል እድገት ሂደት እንደሆነ ሊማሩ ይችላሉ። 

"በአፍሪካ ቀንድ አገራት ያሉ ሰዎች ታሪካችንን፣ ትግላችንን እና ደስታችንን እንዲያዳምጡ እንዲሁም የኩዊር ሰዎች ነፃ መሆን፣ ሁሉም ሰው ቀለል ያለ አየር እንዲተነፍስ እንደሚረዳ እንዲገነዘቡ እንጋብዛለን። ኩራት ልዩነትን ከመቅጣት ይልቅ፣ በመቀበል የተሻለ ነገን እንዴት መገንባት እንዳለብን ሁላችንንም ያስተምረናል "

ይህ አስደናቂ እና አይነተኛ ዝግጅት ከተጠናቀቀ በኋላ እንግዶች ቪየናን ለቀው ሲሄዱ፣ አዘጋጆቹ በኢንስታግራም የመለያያ ሀሳባቸውን አጋርተዋል። 

“የእኛ አብሮ መገኘት የምርጫ ቤተሰብ ድንበር የሌለው መሆኑን የሚያሳይ ህያው ማስታወሻ ነው” ሲል ቤተ ጉራማይሌ ፅፉል። አክሎም "ቦታ በሚነፍገን ዓለም ውስጥ ለራሳችን ቦታ ፈጥረናል። ከተለያዩ ከተሞች፣ አገራት እንዲሁም አህጉራት ከእኛ ጋር የአፍሪካ ቀንድ አገራት ኩራትን ለማክበር የተጓዛችሁ ሁላችሁንም ለማመስገን እንወዳለን። ከፍተኛ ክብር ተሰምቶናል።"

Scroll to Top