የሩዋንዳ ዋና ከተማ ኪጋሊ ከተማ ገፅታ፣ ከፋጤ የአህጉሪቱ ካራታ ጋር።
የፋጤ ወርሃዊ የኤልጂቢቲኪው+ ዜና ቅንብር፣ ከአህጉሪቱ ሀገራት እያስፈራሩ የሚዘርፉትን ከጋና፣ ሎቢስቶቹን ከኬንያ፣ ነገር ቆስቋሾቹን ከሞሮኮ፣ ሚንስትሮቹን ከናይጄሪያ እና ከዚምቧቤ፣ ከሩዋንዳ እና ከዩጋንዳ የተገኙ ታሪኮችን ይዟል።
በቤዛ ለዓለም
ይህ ወር በአህጉሪቱ ላሉ ኤልጂቢቲኪው+ ማህበረሰቦች የተለያዩ አስደንጋጭ ክስተቶችን ያተስተናገዱበት ወር ነበር። ነገር ግን ከባድ እውነታዎችን ለመጋፈጥ ማስተውልና እና ድፍረት የተሞሉ ድርጊቶች የታየበት ጊዜም ነበር።
የፋጤየግል የምርምር ውጤት፣ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች፣ በተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ሰዎች ላይ እየተፈጸሙ የሚገኙትን ፀረ-ኤልጂቢቲኪው+ ጥቃቶችን በተመለከተ ለዓመታት ያሳዩትን አስደንጋጭ እና አስከፊ ዝምታ አጋልጧል። በኬንያ አንዲት ትራንስ* ሴት ወሳኝ የሆነ የህግ ክርክርን አሸንፋለች። አገር በቀሉ ተሟጋች ቡድን ጂንሲያንጉ፣ ይህ “የኬንያ ፍርድ ቤት፣ የፆታ ማንነትን የመቀይር መብቶችን (ትራንስጀንደር መብቶችን) ህጋዊ ለማድረግ የሚረዳ ህግ እንዲያረቅ፣ ግዛቱን በግልፅ ትዕዛዝ ሲሰጥ የመጀመሪያ ጊዜ ነው” ብሏል።’
*ትራንስ የሚለው መጠሪያ፣ ሲወለዱ የተለየው የፆታ ማንነታቸወን የቀየሩትን/በመቀይር ላይ ያሉትን ሰዎች የሚገልጽ የእንጊልዘኛ ቃል ነው። በሐምሌ ወር፣ በአህጉሪቱ ባሉ የኤልጂቢቲኪው+ ሰዎች ላይ ተፅዕኖ ያሳድሩ ሌሎች ጠቃሚ ታሪኮችም አሉ። የፋጤ የአርዕስተ ዜናዎች ቅንብር የሚከተለውን ይመስላል፦
የሩዋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ፆታ ጥንዶች በሌሎች ሰዎች እገዛ ልጆች ማፍራትን የሚከለክል መተዳደሪያ ህግ አፀደቀ
የኤልጂቢቲ ተሟጋቾች በጋና ያስፈራሩ የሚዘርፉትን ቦታዎች ይፋ አደረጉ
‘ከማስተካከያ አስገድዶ መደፈር’ የተረፈችው የተመሳሳይ ሴት ፆታ አፍቃሪ በደቡብ አፍሪካ ፍርድ ቤት ፍትህን ጠይቃለች
የናይጄሪያው የአንግሊካን ቤተክርስቲያን ከዌልሽ ቤተክርስቲያን ጋር በኤልጂቢቲኪው ጉዳዮች ላይ ያለውን ግንኙነት አቋረጠ
ዳኛው በኒጀር በእስር ላይ የሚገኙትን የተመሳሳይ ፆታ ጥንዶችን ክስ ውድቅ አደረገ
ኮውከስ የፀረ-ኤልጅቢቲኪው+ ህግ መዘግየትን ተከትሎ የጋና መንግስትን ተቸ
የኬንያ አክቲቪስቶች በፀረ-ኤልጅቢቲኪው ቡድኖች የቀረበውን አቤቱታ ውድቅ እንዲያደርጉ የፓርላማ አባላትን ጠየቁ
በፀረ-ኤልጂቢቲኪው+ ጥቃቶች ምክንያት በኡጋንዳ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ የወደፊት ዕጣ በተመለከተ አሜሪካ ዝምታን መርጣልች
ካሜሩን የተመሳሳይ ፆታ ጭብጥ ያላቸው ፊልሞችን ተመልከታችኋል የሚል የኢማም ጥቆማን ተከትሎ አራት ሰዎች አስራለች
ደቡብ አፍሪካ በኤልጂቢቲኪው ጉዳዮች ላይ የህዝብ አስተያየትን ለመረዳት አዲስ ሀገር አቀፍ የዳሰሳ ጥናት ለማድረግ ዝግጅት ላይ ነች
አላህ ሌዝቢያን ነው” የሚል ፅሁፍ ያልው ቲሸርት በመብለሷ ምክኛት የታሰረችው የሞሮኮ አክቲቪስት ዋስትና ተከልክላለች
ከአየርላንድ የተባረረው የተመሳሳይ ፆታ ወንድ አፍቃሪ ናይጄሪያዊ የጥገኝነት ጉዳዩን ይግባኝ ማለት ይችላል
ዚምቧቤ ለኢንተርሴክስ ሰዎች እውቅና ለመስጠት የህግ ማሻሻያ ሂደት ጀመረች

