የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ቡድኖች ፀረ-ኤልጂቢቲኪው+ ጥቃቶችን በተመለከተ ያሳዩት አስደንጋጭ እና አስከፊ ዝምታ!

በሀገሪቷ ያሉ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እየተደረገ ስላለው ሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ የኤልጂቢቲኪው+ መብቶች ተሟጋች ቡድን ቤተ ጉራማይሌ መዝግቦ ያቀረበውን አዲስ መረጃ እውቅና አልሰጡም፤ ተግባሩንም አላወገዙም። 

በቤዛ ለዓለም

በኢትዮጵያ ኤልጂቢቲኪው+ ሰዎች ላይ እየተፈፀመ ያለውን ጥቃት የሚገልጽ አዲስ የመረጃ ዶሲየ በባለፈው ሳምንት በቤተ-ጉራማይሌ ይፋ ሆኗል። የፋጤ አገር በቀል የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችን መልስ ለማወቅ፣ በበርካታ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ላይ ምላሽ የሚሰጡን እነዚህን ድርጅቶችን አነጋግሯል። ማናቸውም ግን ምንም አልሰጡም! 

ከተለቀቁት መረጃዎች መካከል አንደኛው ቪዲዮ፣ አንድ ተጠቂ በገዛ ደሙ ከጀርባው “ቡሽቲ” የሚል ቃል ተፅፎ የተደበደበበትን ክስተት የሚያሳይ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ሁለት ወንዶች በሆቴል ክፍል ውስጥ ቆንጨራ በያዙ አጥቂዎች የደረሰባቸውን ድብደባ እና አፀያፊ ማንቋሸሽ የሚያሳዩ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ጠል (ሆሞፎቢክ) ቪዲዮዎች ሲሆኑ፤ በተጨማሪ ሌሎች ሰዎች ተይዘው የግዳጅ ኑዛዜ እንዲያረጉ ግፍ ሲፈጸምባቸው እና ጥቃት ሲደርስባቸው የሚያሳዩ ናቸው።

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ዝምታ እና ከዕርምጃ መቆጠብ ተስፋ አስቆራጭ ቢሆንም ያልተጠበቀ አይደለም ሲሉ አክቲቪስቶቹ ይናገራሉ። በኤልጂቢቲኪው+ ሰዎች ላይ የሚደርሰውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ፣ የሀገር ውስጥ ቡድኖች በይፉ ሲያወግዙ የሚያሳዩ መዛግብት የሉም። “አንድነታቸውን እና ታማኝነታቸውን የሚያሳዩበት ጊዜ አሁን ነው” ሲል የቤተ ጉራማይሌ ተባባሪ መስራች ባህሩ ሸዋዬ ተናግሯል።

ፋጤ የፋጤ አስተያየት እንዲሰጡ ጥያቄ ያቀረበላቸው አራቱ ግንባር ቀደም መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፡- በብርሃኑ አዴሎ የሚመራው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣ በአቶ መሱድ ገበየሁ የሚመራው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ህብረት (ኢሰመድህ)፣ በአቶ ተስፋዬ ገመቹ የሚመራው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) እና በቅርቡ በመሠረት አሊ መመራት የጀመረው የሰብዓዊ መብቶች ማኅበር በኢትዮጵያ ናቸው።

“ማየት የምንፈልገው በኢትዮጵያ ያሉ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰትን ሪፖርት እንዲያደርጉ እና እንዲያወግዙ ነው። የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን መብቶች ሰብዓዊ መብቶች ናቸው።” ሲል ተናግሯል፣ ተሟጋች ቡድናቸው በሀገሪቱ ውስጥ በኤልጂቢቲኪው+ መብቶች ላይ ከሚያተኩሩ ጥቂቶች መካከል አንዱ የሆነው የቤተ ጉራማይሌ ተባባሪ መስራች ባህሩ ሸዋዬ። “የደቦ ፍርድ፣ ያለፈቅድ የሰዎችን ወንም የድርጅት ግል መረጃዎችን በበይነመረብ ላይ ማጋለጥ፣ ትክክለኛም ይሁን በግምት የሰዎችን [ፆታ ተማርኮ] መሰረት አድርጎ መጉዳት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ነው።” 

ከችግሮቹ መካከል አንዱ የፆታ ተማርኮ እና የፆታ ማንነት በኢትዮጵያ አጠቃላይ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች የስራ ሃልፊነቶች ላይ ሊመዘገቡ ቀርቶ ተልዕኮዎቻቸው ውስጥ እንኳን አልተካተቱም። 

በፅኑ የተገለሉትን አለማካተት 

የኢትዮጵያዊ ቡድኖች የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪነት ወንጀል ነው፣ የግብዓት ውስንነት የሌሎች ትኩረት የሚሹ ሰዎችን ጉዳይ ቅድሚያ እንዲሰጥ ያስገድዳዳል እንዲሁም በሠራተኞችን እና በተጠቃሚዎች ላይ ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ ስጋት ሰበብ በማድረግ ኤልጂቢቲኪው+ ሰዎችን ያገለሉ ይመስላል። ኤልጂቢቲኪው+ አክቲቪስቶች እነዚህን ሰበቦች ሙሉ በሙሉ ውድቅ ቢያደርጉም፣ በተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን ላይ በሰፊው የተንሰራፋ የሕዝብ ጠልነት ባለበት ሁኔታ ውስጥ ሰዎች ለደህንነታቸው ያላቸው ስጋት መሠረተ ቢስ አለመሆኑን ይቀበላሉ።

እ.ኤ.አ. በ 2007 በፒው የምርምር ማዕከል የተደረገ ጥናት እንዳመለከተው 97% ኢትዮጵያውያን ምላሽ ሰጪዎች ህብረተሰቡ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪነትን መቀበል የለበትም ብለው ያምናሉ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አመለካከቶች በጥቂቱ ተለውጠዋል። እ.ኤ.አ. በ 2022 በዓለም አቀፍ የእሴቶች ጥናትውስጥ 79% የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪነትን በጭራሽ ‘የሚደገፍ’ አይደለም ሲሉ፣ 5% ብቻ የሚሆኑት ሙሉ ለሙሉ ትክክል ነው ብለዋል። የተቀሩት እርግጠኛ አለመሆናቸውን ገልፀዋል። እንደ አፍሮባሮሜትር የዳሰሳ ጥናት ዘገባ፣ ባለፈው ዓመት 80% የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ጎረቤት እንዲኖሯቸው እንደማይፈልጉ አመላክተዋል።.

የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎች ላይ ያለው የህዝብ አመለካከት እጅግ በጣም አሉታዊ በመሆኑ ማህበራዊ ጥላቻ፣ አመፅን እና መድልዎን ብዙ ጊዜ የማይጠየቁበትን እና የማይፈተሹበትን ሁናቴ እንዲፈጠር አስተዋጽዖ በማድረግ፤ ወንጀለኛነትን ሽፋን እንዲያሰጠው እንዲሁም እዲጠናከር እድል ፈጥራል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ቤተ ጉራማይሌ የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ የኤልጂቢቲኪው+ ሰዎችን የመስዋዕት በግ አድርጎ መመልከትን እና የሚቀሰቅሰውን የደቦ ፍትህን ውድቅ እንዲያደርግና “ለሁሉም ዜጎች ክብር፣ ደኅንነት እና እንክብካቤ ላይ የተመሰረቱ አካታች እሴቶችን እንዲቀበል” ቀጥተኛ ጥሪ አቅርበዋል።

ተሟጋች ቡድኑ በመቀጠል የኢትዮጵያ መንግስትን፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን፣ የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮችን እና ሰፊው ዓለም አቀፍ ማህበረሰብን የሰብዓዊ መብት ጥሰትን በማውገዝ “በኢትዮጵያ ‘ዜጋ’/ኤልጂቢቲኪውአይኤ+ ሰዎች ላይ እየደረሰ ያለውን የተቀናጀ ጥቃት ለማስቆም” እርምጃ እንዲወስዱ አሳስቧል። ‘ዜጋ’ የሚለው የአማርኛ ቃል በአንዳንድ የኤልጂቢቲኪው+ ማኅበረሰብ አባላት፣ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያንን ለመግለፅ ሚስጥራዊ በሆነ ግን ልብ በሚነካ መንገድ የሚጠቀሙት ቃል ነው። 

በተለይ ለመንግሥት የቀረበው ጥሪ ትልቅ ትርጕም ያለው ነው። ቡድኑ የሀገሪቱን የፖለቲካ አመራሮች በፆታ ተማርኮ እና በፆታ ማንነት ላይ የተመሰረቱ የትኛውንም የጥቃት ዓይነቶች ሁሉ በይፋ እንዲኮንኑ፣ ወንጀለኞች ተመርምረው ለፍርድ እንዲቀርቡ እንዲሁም ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ ግለሰቦች አፋጣኝ ጥበቃ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

መንግስት ለጉዳዩ ጆሮ ዳባ ልበስ ማለት

የኢትዮጵያ መንግስት በሀገሪቱ በኤልጂቢቲኪው+ ሰዎች ላይ የሚደርሰውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በይፋ አውግዞ አያውቅም ይላሉ ባህሩ። በተቃራኒው “ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ያየነው እንደ አዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ያሉ የመንግስት ባለስልጣናት ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በመተባበር፣ ሰዎች የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያንን እና እንቅስቃሴዎቻቸውን ሪፖርት እንዲያደርጉ ነፃ የስልክ መስመር ማበጀታቸውን ነው” ብለዋል።

እ.ኤ.አ በ 2019 የቀድሞ የካቢኔ ሚኒስትር እና የወቅቱ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ከንቲባ የነበሩት ታከለ ኡማ ባንቲ ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ የሆኑ ቱሪስቶች በከተማዋ አይገቡም እንዳሉ አዲስ ኢንሳይት ዘግቧል። የፌደራል መንግስት፣ ያለውን አቋም በግዳጅ ቢሆንም በዓለም መድረክ በግለፅ አሳይቷል። ለምሳሌ፣ በዚህ ዓመት የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች የተባበሩት መንግስታት የኤልጂቢቲኪው+ ሰብዓዊ መብት ኤክስፐርት ስልጣንን ለማደስ በመቃወም ድምፅ ሰጥተዋል። በአብዛኛው ግን፣ የፖለቲካ ተቋሙ የዝምታ ግድግዳ በመካብ ለኤልጂቢቲኪው+ ማህበረሰብ ተቃውሞውን ይገልፃል።

ህግ በጉዳዩ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። የኢትዮጵያ መንግስት በወንዶች እና በሴቶች መካከል የሚፈፀመውን የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ወንጀል እንደሆነ ይደነግጋል። መቀመጫውን ዩናይትድ ስቴትስ ያደረገው አድቮኬትስ ፎር ሁይማን ራይትስ እና የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ቤተ ጉራማይሌ ያዘጋጁት፣ የ 2024‘የኢትዮጵያ ባለድርሻ አካላት ሪፖርት ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሁለንተናዊ ግምገማ’እንደገለጸው፣ የእ.ኤ.አ. 2004 የፌደራል የወንጀል መቅጫ ህግ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ድርጊቶችን “ሥነምግባር የለሽ” ተብለው የተገለፁ እና ቢያንስ ለአንድ አመት “በፅኑ” እስራት የሚያስቀጡ ናቸው። “ከባድ” በሚባሉ ጉዳዮች ላይ ቅጣቱ እስከ 10 ዓመት የሚደርስ ሲሆን ሌሎች ጉዳዮች ደግሞ እስከ 15 ዓመት እስራት ሊደርሱ ይችላሉ።

የኢትዮጵያ ኤልጂቢቲኪው+ ማህበረሰብ እንደ ሰይጣን እንዲሁም እንደ ኢሰብአዊ ፍጡር ሲታዩ ለረዥም ዘመናት ቆይተዋል። የመንግስት ተዋናዮች እና የሃይማኖት መሪዎች ሲያወግዟቸው እና በእነሱ ላይ ጥቃት እንዲደረግ የሚያበረታቱ ጥሪዎችን ያደርጋሉ። ከ2023 ጀምሮ እነዚህ ዘመቻዎች ተጠናክረው እየቀጠሉ እና የሚረብሹ አዳዲስ ቅርጾችን እየወሰዱ ይገኛሉ። 

የተቀናጁ ጥቃቶችን ማነሳሳት

ባለፈው ዓመት፣ የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች ተቋማት ጉባኤ መንግስት ከሳሞዓ ስምምነት እንዲወጣ ጠይቋል። ይህ ስምምነት በአውሮፓ ህብረት እና በአፍሪካ፣ በካሪቢያን እና በፓሲፊክ መንግስታት ድርጅት የተደረገ ሲሆን፣ ኢትዮጵያም የስምምነቱ ፈራሚ ናት። ፈራሚ አገራት የኤልጂቢቲኪው+ ሰብዓዊ መብቶችን እንዲያራምዱ የሚደግፍ እና የሚያበረታ እንደሆነ በመግለጽ ምክር ቤቱ ስምምነቱን አጥብቆ ተቃውሟል።

ባህሩ የወቅቱን ሁኔታ አስመልክቶ ለዋሽንግተን ብሌድ በሰጠው ቃለ ምልልስ ሲገልጽ፣ “በ[በኤልጂቢቲኪው+ ኢትዮጵያውያን] ላይ፣ በሃይማኖት ተቋማት እና በተዛማጅ የሞት መሣሪያዎቻቸው ቆስቋሽነት ሆን ተብሎ የሚፈፀም ማስፈራሪያ ነው” ብሏል።.

የሃይማኖቶቹ ምክር ቤት በሰባት አባላቶቹ ማለትም፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት፣ የኢትዮጵያ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን፣ የወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ እና የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ባጠቃላይ “97 በመቶ የሚሆነውን የአገሪቱን ህዝብ አካቶ እንደሚይዝ” ይናገራል።

ከሃይማኖታዊ ተቋማት ቀናተኛ ተቃውሞ በተጨማሪ አዳዲስ የማዋከብ፣ የዛቻ እና የአመፅ መቀስቀሻ ምንጮች አሉ። 

በቅርብ ወራት ውስጥ፣ ተቃዋሚዎች ሆን ብለው ፌሚኒዝምን ከኤልጂቢቲኪው+ መብቶች ጋር የማጣመር ዘመቻ ጀምረዋል። ፀረ-ሴት ተዋናዮችን እንደመሳሪያ በመጠቀም፣ የሴቶች መብት ተሟጋቾችን እና ኤልጂቢቲኪው+ ሰዎችን ለማጣጣል እየሰሩ ይገኛሉ። “በተጨማሪም በፌሚኒስት እንቅስቃሴ ውስጥ ያሉ አንዳንድ ግለሰቦች ኤልጂቢቲኪውአይኤ+ ን ዒላማ እና ተወቃሽ እንዲያደርጉ ደፍረትን ስጥቷቸዋል” ሲሉ ቤተ ጉራማይሌ ተናግሯል።

ይህ አዝማሚያ ከመስፋፋቱ በፊት እንኳን፣ በበይነ መረብ ላይ የጥላቻ ንግግሮች፣ ሰዎችን ያለፍቃዳቸው ማጋለጥ እና የኤልጂቢቲኪው+ ሰዎችን የመግደል እና የማጥቃት ጥሪን ጨምሮ ማህበረሰቡን ያነጣጠሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ጎጂ ልጥፎች እና ቪዲዮዎች ተዘግበዋል። እንደ ፌስቡክ፣ ቲክቶክ እና ቴሌግራም ባሉ መድረኮች ላይ ያሉ አንዳንድ ልጥፎች በግለሰቦች ላይ አካላዊ ጥቃት እንዲደርስ መንስኤ ሆነዋል። 

“ሁሉም የማህበራዊ ሚዲያ መድረኰች የተሻለ ማድረግ አለባቸው” ሲሉ የገለጹት ባህሩ፣ ነሐሴ ወር ላይ ቢያንስ አንድ በተለይ አሰቃቂ ቪዲዮ ከመወገድ መዘግየቱ ምክንያት ሊሆን ይችላል ብለው ያመኑትን “በሜታ ላይ ስለተደረገ አንድ አይነት የፖሊሲ ለውጥ” ጠቅሰዋል። 

የቤተ ጉራማይሌ የቅርብ ጊዜ መግለጫ ማህበራዊ ሚዲያዎች እና የመልዕክት ማስተላላፊያ መድረኰች በ24 ሰዓታት ውስጥ ዓመፅ እና ትንኮሳ የሚፈጥሩ ይዘት ያላቸውን ልጥፎች/ይዘቶች እንዲያስወግዱ እና የጥላቻ ንግግርን በኢትዮጵያ ቋንቋ የመለየት ስራን እንዲያጠነክሩ፣ በተጨማሪም በተደጋጋሚ የዓመፅ ይዘቶችን የሚለጥፉ አይፒ አድራሻዎችን እንዲያግዱ ጥሪ አቅርቧል።

የባህሩ ባልደረባ እና የቤተ ጉራማይሌ ተባባሪ መስራች ፋሪስ ኩቺ ገዛኸኝ ግን በቅርቡ በቲክቶክ የተገኘውን እድገት አስታውሰው፣ “ጥያቄዎቻችን ተሰምተው ጐጂ ልጥፎችን ለማስወገድ እርምጃዎች ተወስዷል” ብለዋል። 

እያንዣበበ ያለው የወንጀለኝነት ስጋት 

ለዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ መድረኮች እና ለኢትዮጵያ መንግስት ከቀርበው ጥሪ ባሻገር፣ የቤተ ጉራማይሌ መሪዎች ሰፊው የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ እርምጃ እንዲወስድ እያበረታቱ ይገኛል። በኢትዮጵያ በኤልጂቢቲኪው+ ሰዎች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት የሚያወግዙ ህዝባዊ መግለጫዎችን በማውጣት እና ጉዳዩ በቀጥታ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት እና ከተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት አያያዝ ዘዴዎች ጋር እንዲነሳ ጠይቀዋል። አበክረውም ጥበቃን፣ የህግ ድጋፍን እና ሰነዶችን ለመደገፍ ግብዓት እንደሚያስፈልግም አሳስበዋል።

ነገር ግን በዚህ አጋጣሚ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የቀረበው ጥሪ ጆሮ ዳባ የተባለ ይመስላል። እስካሁን ድረስ በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በኤልጂቢቲኪው+ ኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት ለመቃወም ጥሪውን ሲመልሱ የሚያሳይ ምንም አይነት መረጃ የለም። የሰብዓዊ መብት ጥሰት ማስረጃዎች ከወጡ አንድ ሳምንት በኋላ እንኳ በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ምንም አይነት ሽፋን አልተሰጠበትም።

የቤተ ጉራማይሌ የቅርብ ጊዜ ዘመቻ አዳዲስ ጥሰቶችን ማውገዝ፣ ደህንነትን ማሻሻል እና ግጭቶችን የመቀነስ እርምጃዎች ላይ ያተኮረ መሆኑን መረዳት አያዳግትም። ነገር ግን የረጅም ጊዜ ለውጥ ላይ እኩል ትኩረት ካልተሰጠ፣ ንቅናቄው በመሰናክል ወጥመድ ውስጥ የመውደቅ አደጋ ሊገጥመው እንደሚችል ባለሙያዎች ያስጠነቅቃሉ። በሌላ አነጋገር፣ ይህን የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያንን ጠልነት የሚያሽከረክሩ ኃይላትን እና መዋቅሮችን በግልፅ እስካልተጋፈጡ ድረስ የኢትዮጵያ ኤልጂቢቲኪው+ ማህበረሰብ ለከፍተኛ ተጠቂነት ሊጋለጡ ይችላሉ።

“[የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪነትን] ህጋዊ ማድረግ የተሟላ ምላሽ አይደለም፤ ነገር ግን [የኤልጂቢቲኪው] ሰዎችን ሰብዓዊ መብቶች ለማክበር፣ ለመጠበቅ እና ለማሟላት ቁልፍ እርምጃ ነው” በማለት በ2008 ‘ፍቅር፣ ጥላቻ እና ህግ’ የተሰኘ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ዘገባ አዘጋጆች ጽፈዋል።

“ህጋዊ ማድረግ [የኤልጂቢቲኪው] ሰዎች በወንጀል መከሰስን ሳይፈሩ ስለ ፆታ ተማርኳቸው፣ ፆታ ማንነታቸው ወይም መገለጫዎቻቸው በግልጽ የመናገር መብታቸው እንዲከበር እና ማህበራዊ ተቀባይነት እንዲያገኝ የመጀመሪያው እርምጃ ሲሆን፤ በሌሎች ግለሰቦች የጥቃት ሰለባ በሚሆኑበት ጊዜም የህግ ከለላ እና ፍትህ ማግኘት እንደሚችሉ እንዲያውቁ ይረዳል።”

የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪነት ወንጀል ሆኖ እስከቀጠለ ጊዜ ድረስ፣ ኤልጂቢቲኪው+ ኢትዮጵያውያን ተከታታይ ስደት ይደርስባቸዋል፤ ሕጉም ጥቃትን የሚያበረታታ እና ለሚፈጽሙትም ጋሻ ሆኖ ይቀጥላል። ወይም አምነስቲ እቅጩን እንዳስቀመጠው፣ “ሆምፎቢክ እና ትራንስፎቢክ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች እነዚህን ህጎች [ኤልጂቢቲኪው] ሰዎችን፣ ድርጅቶችን እና ዝግጅቶችን ለማጥቃት እንደ ፍቃድ ወስዱታል።”  

ለኤልጂቢቲኪው+ ማህበረሰብ ተሟጋቾች እና ለማንኛውም እውነተኛ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የህግ ማሻሻያ ከመቼውም በላይ አስፈላጊ መሆኑ አያጠራጥርም። ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪነት ህጋዊ ከሆነም በኋላ፣ ወደ እኩልነት የሚወስደው መንገድ ረዥም እና በአብዛኛው ተራራማ ይሆናል። ነገር ግን ለእዚህ በጣም ለተገለሉ ማህበረሰቦች እንዲህ ዓይነቱ እርምጃ ሕይወትን ከመቀየር የማይተናነስ ነው።

Scroll to Top