የፋጤ የአፍሪካ ቅንብር ፣ ሐምሌ 2025
የፋጤ ወርሃዊ የኤልጂቢቲኪው+ ዜና ቅንብር፣ ከአህጉሪቱ ሀገራት ከሴኔጋል አነጋጋሪ፣ ከናይጄሪያ ሃይማኖት፣ ከማዳጋስካር ዲፕሎማሲ፣ ከጊኒ ስደተን እና ከኡጋንዳ፣ ኮትዲ ቯር፣ ጋና፣ ኬንያ፣ ቱኒዚያ፣ ሞሮኮ እና ደቡብ አፍሪካ ያሉ ታሪኮችን ይዟል።
በቤዛ ለዓለም
ወሩ በአህጉሪቷ ውስጥ ላሉ የኤልጂቢቲኪው+ ማህበረሰብ አስጨናቂ እና ንዴት የተሞሉ ክስተቶች የተሞላበት፣ ነገር ግን የተስፋ ጭላንጭልም የታየበት ነበር።
እስከ ሐምሌ ባለው ጊዜ ውስጥ ፋጤ አነቃቂ እና አርዓያ ስለሆኑ ጌይ እና ሌዝቢያን ሰዎች ታሪኮችን ያጋራን ነበር። ለምሳሌ፣ የደቡብ አፍሪካ አዲስ የፓርላማ አባል ፓሎሚኖ ጃማ እና ፍሪዴል ዳውሳብ፤ አወዛጋቢ የሆነችውን 'የካሜሩን ቀዳምዊት ሴት ልጅ' ብሬንዳ ቢያንየሚያሳይ ታሪኮችን አጋርተናል። እንዲሁም ስለ ኢትዮጵያ ፀረ-ኤልጂቢቲኪው+ ድምፅ መስጠት፣, የአንጎላ ኤልጂቢቲኪው+ ሚዲያ ክልከላ ስጋትን እና ቡርኪናፋሶ በተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያንን ለመወንጀል ስለወሰደችው እርምጃ ዘግበናል።.
በሐምሌ ወር ራሱ፣ በአህጉሪቱ ባሉ የኤልጂቢቲኪው+ ሰዎች ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ሌሎች ጠቃሚ ታሪኮች ነበሩ። የፋጤ የአርእስተ ዜናዎች ስብስብ የሚከተልውን ይመስላል፡
የሴኔጋል ኤልጂቢቲኪው+ ፕሮግራም ከመንግስት ማስጠንቀቂያ በኋላ በተባበሩት መንግስታት ተሰርዟል
የሞሮኮ ኩዊር እንቅስቃሴ በሀይማኖት እና ባህላዊ እሴቶች የተነሳ ተቃውሞ ቀስቅሷል
የናይጄሪያ አንጄሊካን ቤተ ክርስቲያን የኤልጂቢቲኪው+ ልማዶችን እንደማትቀበል ዳግም አረጋገጠች
የደቡብ አፍሪካ ኤልጂቢቲኪው+ ማህበረሰብ በኩዊር ኢማም መገደል የተነሳ ሰልፍ አድርገዋል
ከዩጋንዳ ፀረ-ጌይ ህጎች የተሰደዱ ሰዎች አሁን "የሞራል ሽብር" ሕግን ሰግተዋል
ከጊኒ የመጣ ሰው በአሜሪካ የኢሚግሬሽን ፍርድ ቤት ፊት ለፊት በ አይሲኢ ወኪሎች ተያዘ
ማዳጋስካር የኤልጂቢቲአይ+ መድሎን ለመከላከል የቀረቡ ምክሮችን ውድቅ አደረገች
ኬንያ በተባበሩት መንግሥታት ለኤልጂቢቲ መብቶች ጥበቃ ድምፅ መስጠቷ ውዝግብ አስነሳ
ሙዚቀኛው የጋና ፀረ-ኤልጂቢቲኪው+ ሕግ ሁሉንም ዜጐች አደጋ ላይ እንደሚጥል አስጠነቀቀ
የኮትዲቯር ሴቶች እና የኤልጂቢቲ ሰዎች በአሜሪካ የእርዳታ እገዳ ለጉዳት ተጋላጭ ሆኑ

